አይነጥላ
🌵 ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌵

ገርጋሪ መንፈስ ምንድን ነው
የሚገረግር መንፈስ እና የዓይነ ጥላ መንፈስ ነገዳቸው ምድራውያን አጋንንት
ሲሆኑ ተግባራቸው የሰው ልጅ ዕድል መስበር እንዲሁም የታሰበ መልካም ስራ
ማሰነካከል ነው።
የገርጋሪ መንፈስት ማለት፦እጅግ በጣም ብዙ እና አዳጋች እንዲሁም የረቀቀ
የሕይወት መሰናክል ይዘው የሰው ልጅ አእምሮን የሚቆጣጠሩ ከዘመናዊ
ሕክምና ጋር የተላመዱ የወደቁ መናፍስት ናቸው።
የሚገረግሩ መናፍስት፦ ከልጅነት እስከ አዋቂነት ዕድሜ ድረስ ዕድልን
የሚሰልቡ ከራሳችን ባህሪ ጋር በመመሳሰል የራሳቸውን ዓላማ የሚያስፈጽሙ
ተንኮለኞች መናፍስት ናቸው።
የሚገረግሩ መናፍስት ስራ፦ ሰዎች በተለያዩ ምክንያት የውጭ ሀገር ዕድል
አግኝተው ምክንያቱ ሳይታወቅ ጉዳዩን ማስተጓጎል፣እንቅፋት መፍጠር፣በፈተና
ሰዓት ማሸበር፣በበሽታ ማስተጓጎል የመሳሰሉት እንቅፋት እንዲከሰት ዋነኛ
ተዋናዮች የገርጋሪ መናፍስት ናቸው።
የገርጋሪ መናፍስቶች፦ማንኛውም የታቀደ ስራ፣ ይሁን የሕይወት መሰረትን
የሚገረግሩ፣የሚያናጉ፣ ወደ ቤተ እግዚአብሔር እንዳንጠጋ የሚገረግሩ፣የራስ
ማንነታችን እንዳንመስል አስከፊ ባሕሪ የሚያጎናጽፉ፣ሞት የሚደግሱ፣የጥፋት
ነገድ ናቸው።
የሚገረግሩ መናፍስት፦የማይገረግሩት የሕይወት ዘይቤ የለም:: ትዳር
እንዳንይዝ፣ልጅ እንዳንወልድ፣ሃብት እንዳናፈራ፣ቤተሰብ ሰላም እንዳይሆን፣ሀገር
ሰላም እንዳይፈጠር፣ግልፍተኝነት ባህሪ እንዲኖረን ያደርጋሉ።

እናመስግናለን
          መልካም ጤንነት
🌱🌱ማንኛውም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌱🌱🌱
"ለበለጠ መረጃ፦ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
"አድራሻ፦ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
"ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website ፦www.hakimsolomon.com
Telegram፦https://t.me/