የአቱች የጤና ጠቀሜታዎች 🌵ከ ሀኪም ሰለሞን አዳም
Author: admin
Date: 2024-04-03
የአቱች የጤና ጠቀሜታዎች
🌵ከ ሀኪም ሰለሞን አዳም
1.ጉሮሮውን ላመመው ሰው ቅጠሉን ከጥጥ ፍሬ ጋር አጥሚት ሰርቶ መጠጣት ነው።
2. ጆሮው አልሰማ ላለው የአቱች ቅጠልና የአንፋር ቅጠል በፍየል ቂቤ ለውሶ በፀሐይ አሙቆ ሲቀልጥ አጥልሎ በጀሮ በትንሹ መክተትና በጥጥ ወትፎ መተኛት ነው።
3. ጥርሱ ለተቦረበረና ለሚያመው ቅጠሉን ከከርቤና ከአልቴት ጋር ደቁሶ የታመመው ላይ ማድረግ ነው።
4. ምላሱ ለታመመ ሰው ቅጠሉን ቀቅሎ ውኃውን በትኩሱ መጉመጥመጥ ነው።
5. እጁ ለሚንቀጠቀጥበት ሥሩንና ቅጠሉን ከዕፀ ፍላጹት ሥርና ቅጠል ጋር ወቅጦ አድርቆ በጣዝማ ማር ጠዋትና ማታ መብላት ነው።
6. የበሉት አልስማማ ካለ ቅጠሉን ቀቅሎ ውኃውን መጠጣት ነው። ወዲያው ፈውስ ይገኛል።
7. ሆድ ሲያጥወለውል (የበሉት ልውጣ ልውጣ ሲል) ሥሩን ማላመጥና መዋጥ ነው።
8.ለልብ ህመም ሥሩንና ቅጠሉን ወቅጦ ከሱፍ ጭልቃ ጋር ጠዋት በባዶ ሆድና ከራት በኋላ ጠጥቶ መተኛት ነው።
9. ለልብ ድካም ሥሩን ከሁለገብና ከእንጭብር ሥር ጋር ደቁሶ በቄቤ አንጥሮ አጥልሎ መጠጣት ነው።
10. ለተቅማጥና ለአሜባ ቅጠሉንና ሥሩን አጅንጅብል ጋር ቀቅሎ መጠጣት ነው። ከሩዝ ጋርም ይቻላል።
11. የምትበሉት ነገር ሆዳችሁ ውስጥ ቁጭ ለሚልባችሁ (ስርአተ ልመት አነስተኛ ለሆነባችሁ) ቅጠሉን ከእጆሪ ቅጠል ጋር ወቅጣችሁ የሎሚ ውኃ ጨምራችሁ ከምትበሉት ምግብ ላይ ጨምራችሁ መመገብ ነው።
12. አፋችሁ እየሸተተ ላስቸገራችሁ ቅጠሉን ከከርቤና ከአልቴት ጋር ወቅጣችሁ ለተወሰነ ጊዜ በአፋችሁ መያዝ ነው። ሽታው ድራሹ ይጠፋል። በተጓዳኝ የጤና ችግሮች ምክንያት የሚከሰተውን አይጨምርም (ለምሳሌ በጨጓራ)።
13. ለስኳር ሕመም ሥሩን ከምድር እንቧይና ከቀጠጢና ሥር ጋር ወቅጦ በማር ልክ እንደሻይ እያፈሉ መጠጣት ነው።
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌱🌱ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችለሉ🌱🌱🌱
"ለበለጠ መረጃ፦ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
"አድራሻ፦ቦሌሚካኤል የቤተ ክርስቲያኑ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
"ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
Telegram:- https://t.me/kidusmikaelhikmna