ጦስኝ ለጤና 🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
Author: admin
Date: 2024-03-26
ጦስኝ ለጤና
🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
፨በሃገራችን በተመጣጣኝ ዋጋ እና በቀላሉ የሚገኘው ጦስኝ የመጀመሪያ መገኛው ሜዲትራኒያን አካባቢ ነው ተብሎ ይገመታል፡፡ ከነፈርኦን ዘመን ጀምሮ ለምግብነት፤ ለህክምና እና ለመልካም መአዛ የሰው ልጅ ሲጠቀምበት ኖሯል፡፡ ዛሬ ደግሞ ጦስኝ ለጤናችን የሚሰጠውን ጥቅም አብረን እናያለን፡፡
ጦስኝ ለምግብነት
1. ጦስኝ መልካም መአዛ እና ጣእም ስላለው የተለያዩ ምግቦችን ስንሰራ ለማጣፈጫነት መጠቀም እንችላለን፡፡ ለምሳሌ የአሳ፤የዶሮ እና የስጋ ምግቦችን ስናዘጋጅ (አሮስቶ፤ ግሪል) ከላይ ሳይበዛ በመጠኑ መነስነስ እንችላለን፡፡ እንዲሁም ከፓስታ፤ ከሩዝ እና ከፒዛ ጋር አብረን መብላት እንችላለን፡፡
2. የጦስኝ ሻይ
• አንድ ብርጭቆ ውሃ በደንብ እናፈላለን
• አንድ የሻይ ማንኪያ ጦስኝ እንጨምርበት እና ከእሳቱ ላይ እናወጣዋለን
• ለ10 ደቂቃ ከነቅጠሉ እናስቀምጠው እና አጥልለን እንጠጣዋለን
• ብቻውን መጠጣት ይችላል ነገር ግን ለጣእም ሎሚ ወይም ዝንጅብል ወይንም ትንሽ ቀረፋ መጨመር ይቻላል
ጦስኝ ጤና የሚሰጣቸው ጥቅሞች
1. የደም ግፊትን ለመቀነስ፡- በሀገራችን በሰፊው የሚታወቀው ጦስኝ የደም ግፊትን እንደሚቀነስ ነው፡፡ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ጦስኝ የደም ግፊትን ለመቀነስ ጠቃሚ ነው፡፡ በጦስኝ ውስጥ የሚገኘው ፖታሲየም የተባለ ንጥረ ነገር የደም ግፊትን እና የልብ ምትን ለማስተካከል ጠቃሚ ነው፡፡ የደም ግፊት ካለብን ከሃኪም ክትትል እና ከመድሃኒት በተጨማሪም ከሃኪማችን ጋር በመመካከር ጦስኝን ለምግብነት ብንጠቀም ጥሩ ነው፡፡
2. አንታይ ኦክሲዳንት ነው፡- አንታይ ኦክሲዳንት ማለት ሰውነታችን በመኖር ብዛት፤ በምንመገበው ነገሮች ምክንያት፤ ከአካባቢያችን የተነሳ እና በተለያየ ምክንያቶች ጎጂ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ያመርታል፡፡ እነዚህ ንጥረ ነገሮች ደግሞ ሴሎቻችንን ያዳክማሉ ወይም ይጎዳሉ፡፡ ይሄንን የሴሎችን ጉዳት የሚከላከል ንጥረ ነገር ደግሞ አንታይ ኦክሲዳንት ይባላል፡፡ ጦስኝ በውስጡ ብዙ አይነት አንታይ ኮክሲዳንቶችን ይዟል፡፡ ለምሳሌ ዚያዜንፊን እና ሉቲን የመሳሰሉ አንታይ ኦክሲዳንቶች ጦስኝ ውስጥ ይገኛሉ ስለዚህ ጦስኝን ለምግብነት መጠቀም ጤናችንን ለመጠበቅ ይረዳናል፡፡
3. የመተንፈሻ አካላትን ችግር ሊቀርፍ ይችላል፡- ለዘመናት የባህል ሃኪሞች ጦስኝን የመተንፈሻ አካላት ችግሮችን ለማከም ሲጠቀሙበት ኖረዋል፡፡ ብሮንካይተስ፤ ጉንፋን፤ ሳል፤ አለርጂክ እና ሳይነስ የመሳሰሉ ችግሮች ካሉብን ጦስኝ ፍቱን መድሃኒት ሊሆን ይችላል፡፡ በመተንፈሻ አካላችን ውስጥ ያለውን ንፍጥ እና ሀክታ በማስወገድ፤ ሰውነታችን እንዳይቆጣ በማድረግ እና ቫይረሶችን በመከላከል መተንፈሻ አካላችንን ጤናማ ያደርጋል፡፡
4. የደም ዝውውርን ጤናማ ያደርጋል፡- በጦስኝ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው አይረን የተባለ ንጥረ ነገር አለ፡፡ በተጨማሪም በጦስኝ ውስጥ እንደ ማግኒዚየም፤ ፖታሲየም፤ ፎስፈረስ እና ካልሲየም ያሉ የተለያዩ ሚኒራሎች አሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ጦስኝን ስንጠቀም ሰውነታችን የሚያመርተውን የቀይ የደም ሴል ብዛት ይጨምራል፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ የደም ዝውውራችን በጣም ጤናማ ይሆናል እንዲሁም ኦክስጅን ወደ ብልቶቻችን በቀላሉ ይዳረሳል፡፡ ይሄም የድካም ስሜትን ይቀንሳል ወይንም ቶሎ ቶሎ እንዳይደክመን ያደርጋል፡፡
5. የአይናችንን ጤና ይጠብቃል፡- በጦስኝ ውስጥ ካራቲኖይድ እና ቫይታሚን ኤ ይገኛሉ፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ ጦስኝ የአይናችንን እና የእይታችንን ጤና ይጠብቃል
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌱🌱ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችለሉ🌱🌱🌱
"ለበለጠ መረጃ፦ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
"አድራሻ፦ቦሌሚካኤል የቤተ ክርስቲያኑ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
"ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
Telegram:- https://t.me/kidusmikaelhikmna