ሳንባዉን ታሞ ሳል ለሆነበት
Author: admin
Date: 2024-03-13
ሳንባዉን ታሞ ሳል ለሆነበት
🌴ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌴
• የቆላ ጦስኝ ቅጠለ ከሬት ጋር በባዶ ሆድ አዘውትሮ መውሰድ።
• የአሚራ ፣የዶግ፣የድግጣ ስራቸውን የእንስላል ፍሬ የቆላ አባሎ ቅጠል የእፀመናሂ ስር ዝንጅብል ሁሉንም ወቅጦ እንደ ሲጋራ ጢሱን መሳብ እና መውሰድ።
• ጤናአዳም የእንስላል ቅጠል አፍልቶ መጠጣት
በብርድ ለሚነሳ ሳል
• የቀጋ እና የቀይ ጉመሮ ፣ የግሚ ሀረግ ስራቸውን የድንጋይ ሙጫ፣የጉሎ ፍሬ ሁሉንም ቀቅሎ በጣዝማ ማር በጥብጦ ጠዋትእና ማታ አንድ ማንኪያ መዋጥ ።
• የእንጭብር ፣የአሚራ ፣የቀበርቾ፣የኢንጆ፣የጦስኝ የቁንዶ በርበሬ ቅጠላቸውን ስራቸውን ሁሉንም ወቅጦ በጣዝማ ማር ለውሶ ግማሽ ማንኪያ መዋጥ ። ወይም ብርድ ሲሆን ለሚነሳው በአረቄ ውስጥ ዘፍዝፎ ጠዋት እና ማታ አንድ መለኪያ መጠጣት።
ስለ ሳንባ ህመም እና መንስኤው
• የሳንባ ህመም ወይም የሳንባ ነቀርሳ ህመም በተለያዩ ምክንያቶች የሚነሳ ነው። አብዛኛውጊዜ ከአንዱ ህመምተኛ ወደሌላኛው ግለሰብ በአክታ በትንፋሽ ወይም ዝናብ በዘነበ ጊዜ በፀሀይ ሙቀት ከመሬት የሚነሳው እንፋሎት ወይም የሚተን ብናኝ በአፍንጫ በአፍ ይገባ እና ወደሳንባ ይገባል በዛን ጊዜ በአፍ የገባው ያልተጣራ የብናኝ አየር የደም ስር ያላቸውን የሳንባ ወናፎችን እንዳይተነፍሱና የተበከለ አየር እንዳይወጡ ያደርጋሉ ።ሰውነቱ በተለያየ ምክንያት የተጎዳ ሰዉ በቀላሉ በሳንባ ነቀርሳ ይጠቃል
• የሳንባ ህመም ነቀርሳ መሆኑ የሚለየው አክታ ያበዛል አክታው ከቀን ወደ ቀን ይጨምራል። የእንቁላል አስኩዋል ይመስላል ህመሙ እየበረታ ሲሄድ ውጋት ይጀምራል ከአክታ ጋር ደም ይቀላቅላል ደምም ያስተፋል ።
• የሳንባ ህመም ነቀርሳ መሆኑ ከታወቀ ቀን ጀምሮ በፍጥነት ስለ ሳንባ ህመም ጥናት እና ህክምና ወደሚያደርጉ የህክምና ባለሙያዎች ጋር መሄድና የእነሱን ምክር መቀበል እና የተባሉትን ማድረግ የተሻለ ነው። ነገር ግን በግዴለሽነት ችላ ማለት በራስ ህይወት እና በቤተሰብ የሞት አደጋ ማምጣት ነው። አደጋው ከመፈጠሩ በፊት ምግቦችን በመመገብ ህክምና በማድረግ እራስን መጠበቅ ተገቢ ነው።
🍀በባህላዊ መንገድ የሚወሰዱ መድሀኒቶች በጥቂቱ እንሆ.....
1ኛ፦የበግ ወተት ወይም የአህያ ወተት ትኩሱን ወይም አሙቆ መጠጣት ።.
ደም ለሚያስተፋው የአህያውን ወተት ደጋግሞ በአፍንጫው ማድረግ የዘጋውን ጠራርጎ ያወጣዋል ወይም አቱች ቀቅሎ 2 ቀን አቆይቶ መጠጣት ።
2ኛ፦ደም ለሚያስተፋው እና ደም ለሚያስቀምጠው
የእንስላል፣የልት፣የዋጊኖስ ስራቸውን ወቅጦ በለጋ ቂቤ ከወለላ ማር እና ከእንቁላል ጋር አዋህዶ መጠጣት
3ኛ፦በንፋስ ግጭት ወደሳንባ ህመም የተላለፈ ግን ከዚህ የከፋ ሆኖ ትንፋሽ እያሳጠረ እንዳይናገር ይከለክለዋል ለዚህ የበግ ሳንባ ደጋግሞ መብላት ማር በባዶ ሆድ መዋጥ ፍቱን መፍትሔ ነው።
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌱🌱ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችለሉ🌱🌱🌱
"ለበለጠ መረጃ፦ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
"አድራሻ፦ቦሌሚካኤል የቤተ ክርስቲያኑ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
"ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
Telegram:- https://t.me/kidusmikaelhikmna