☘️ስለ ነስር☘️
በ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
ነስር ወይም የአፍንጫ መድማት (ኤፒስታክሲስ) አብዛኛውን ጊዜ የአፍንጫችንን የውስጥ ግድግዳ በ አንድም ሆነ በ ሌላ ምክንያት ምቾት ስንነሳው የሚከሰት ነው፡፡

መንስኤው
ከፍተኛ ሙቀት ፤ጉንፋን፤አለርጂ፤ሽታ፤ መድሃኒት መውሰድ በተለይ አስፕሪን ፤ከ ባህር ጠለል በላይ ያሉ ቦታዎች፤ የደም ግፊት፤አፍንጫን ከ ልክ በላይ መጭመቅ የመሳሰሉት ዋና ዋና የነስር መንስኤዎች ተብለው ይታወቃሉ፡፡
ነስርን እንዴት እንከላከላለን
1 ቤትዎ በተለይ መተኛ ቤት ውስጥ በቂ አየር እንዲያኖር ያድርጉ፤ያናፍሱ፤ሙቀት አምጪ የሆኑ ቁሶችን መተጠቀም ይቀንሱ አልያም የሙቀት መጠናቸውን ዝቅ ያድርጉ፡፡
2 የአፍንጫዎን የውስጥ ልስላሴን ይጠብቁ
3 አፍንጫዎን ከልክ በላይ መጭመቅ ያቁሙ
4 ከ አለርጂ ጋ በተያያዘ ምክንያት በተያያዘ የሚወስዱዋቸውን መድሃኒት ይቀንሱ
5 የተለያዩ ሱሶችን ያቁሙ ሲጋራ በ ከፍተኛ ደረጃ የአፍንጫን የውስጥ ልስላሴ በማሳጣት አፍንጫ በማድረቅ ለነስር ያጋልጣል
6 በየጊዜው ሃኪም ማማከርዎን አይዘንጉ
ነስር ቢከሰትስ
በተለምዶ ነስር ሲከሰት ብዙዎች ወደላይ አንጋጠለን መታጠቢያ ቤት መሮጣችን የተለመደ ነው ፤ይህ ታዲያ ፈጽሞ ስህተት ነው፡፡ በመሆኑም ራሳችን የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ ለራሳችን እናድርግ
1 ነስር ከተከሰተ ወደ ፊት ዘንበል ለማለት እንሞክር
2 በ አፋችን የመጣም ካለ መትፋት ይኖርብናል
3 ያገኘነውን ነገር አንስተን ወደ አፍንጫ ማደረግ መጥፎ ስለሆነ እንቆጠብ
4 ከባባድ እቃ ማንሳት አይከርም
5 ነስርዎ 12 ደቂቃ በላይ ከዘለለ ወድያው ወደ ህክምና ይሂዱ
📚📚ጥበብን በማንኪያ የምትል መፀሐፉ በሀኪም ስለሞን አዳሙ የተዘጋጀ በማንኛውም መፀሐፉ መደብር ያገኛሉ📚📚📚
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌱🌱ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችለሉ🌱🌱🌱
"ለበለጠ መረጃ፦ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
"አድራሻ፦ቦሌሚካኤል የቤተ ክርስቲያኑ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
"ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736

Telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna