ማስቲካን በማኘክ የሚገኙ የጤና ጥቅሞች
Author: solomon
Date: 2023-10-13
ማስቲካን በማኘክ የሚገኙ የጤና
ጥቅሞች
🌱 ከሀኪም ስለሞን አዳሙ🌱
ሁላችንም ልጅ እያለን ማስቲካ ሳናኝክና እየነፋን ሳንጫወት አላደግንም ይህ ልጅ እያለን እያኘክን ብሎም እየነፋን ስንደሰትበት የነበረው ማስቲካ ለሰውነታችን 10 የተለያዩ የጤና ጥቅሞችን ይሰጠናል፤ እነዚህን ጥቅሞች ሳናውቅ ማስቲካን ያኘክንበት አያሌ ዘመናትን ወደኋላ ትተን አሁን ለእኛ ያለውን ጥቅም አውቀን ማስቲካ ማኘክ እንድንጀምር ጥቅሞቹን ልናሳውቅዎ ወደናል።
የምናገኛቸው ጥቅሞች እነሆ፦
1. ጭንቀትን ያስወግዳል!
በተለያዩ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማስቲካ የሚያኝኩ ሰዎች ከማያኝኩት/ከማይጠቀሙት በተሻለ ሁኔታ ከገቡበት ጭንቀት በፍጥነት ይወጣሉ፡፡
2. ክብደትን ይቀንሳል!
የተለያዩ ጣዕም ያላቸው ማስቲካዎችን ለማኝክ ከፍተኛ ካሎሪ/ጉልበት እንድናወጣ ስለሚያደርገን ክብደትን ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡
3. የምግብ ስልቀጣን ያፋጥናል!
ማስቲካ ማኝክ በአፋችን ውስጥ የምራቅ መጠን እንዲጨምር/እንዲበዛ ያደርጋል ይህ ሁኔታ የምግብ ስልቀጣን/መፈጨትን የማፋጠን ከፍተኛ ሀይል አለው፡፡
4. ሀሳብን ለመሰብሰብ ይረዳል!
ማስቲካ ማኝክ ከማንኛውም ጊዜ በላይ እንድንነቃቃ እና ሃሳባችንን እንድንሰበስብ ያደርጋል፡፡ በተለይ በስብሰባ እና በመማሪያ ክፍል ውስጥ (ምንም እንኳን መምህሮች ፈቃደኛ ባይሆኑም) ማስቲካ ማኝክ ነቃ ብለንና ሃሳባችንን ሰብሰብ አድርገን እንድንከታተል ይረዳናል፡፡
5. የትውስታ አቅምን ይጨምራል!
ማስቲካ በምናኝክበት ጊዜ አማካይ የልብ ምታችን ይጨምራል ይህ ሁኔታ ወደ አእምሮአችን የሚገናውን የኦክስጂን መጠን ይጨምረዋል፡፡ ስለዚህ አእምሮአችን በብቃትና በትኩረት ስራውን እንዲወጣ/እንዲሰራ ያደርገዋል፡፡
6. መጥፎ የአፍ ጠረንን ይከላከላል!
ማስቲካ ማኝክ መጥፎ የአፍ ጠረንን ከመከላከሉም በላይ ጥርሳችን እንዳይበሰብስ ይረዳል፡፡
7. የሲጋራ ሱስን ለማቆም ይረዳል!
የተለያዩ የሲጋራን ሱስ ለማቆም የሚረዱ ማስቲካዎች በውስጣቸው ኒኮቲን የያዙ በገበያ ላይ ይገኛሉ እነዚህን ማስቲካዎችን በማኝክ የሲጋራ ሱስን ማቆም ይቻላል፡፡
8. ካሎሪን ለማቃጠል ይረዳል!
ማስቲካ በምናኝክበት ወቅት በመንጋጋ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች ስራ ይሰራሉ፡፡ እንደሚታወቀው ስራ ለመስራት ሀይል ያስፈልጋል ስለዚህ የመንጋጋ ጡንቻዎች በሠዓት 10 ካሎሪ ያህል ይቀንሳሉ ይህ ደግሞ ክብደትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያበረክታል፡፡
9. የገርድ በሽታን ይከላከላል!
ይህ የበሽታ አይነት በጨጓራችን ውስጥ ያለው አሲድ(HCL) በጉሮሮ/የምግብ ቧንቧዎች ወደ ላይ ሲመለስ ልባችን አካባቢ የማቃጠል ስሜት የሚፈጥርብን በሽታ ነው፡፡ ይህን በሽታ በቀላሉ ለመከላከል ማስቲካ በማኝክ በምራቅ አማካኝነት ወደ ላይ የሚመጣውን አሲድ ጨጓራ ውስጥ ማስቀረት ይቻላል፡፡
10. የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን ለማግኝት!
ማስቲካ በውስጡ የተለያዩ ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ለምሳሌ እንደ ቫይታሚን ሲ በውስጡ ይዟል፡፡
📚📚📚ጥበብን በማንኪያ የምትል መፀሐፉ በሀኪም ስለሞን አዳሙ የተዘጋጀ በማንኛውም መፀሐፉ መደብር ያገኛሉ📚📚📚
እናመስግናለን
መልካም ጤንነት
🌱🌱ማንኛውም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌱🌱🌱
"ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
"አድራሻ፦ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
"ስልክ፦0989020202 ወይም0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
Telegram፦https://t.me/