የሰይጣን መርፌ ጥቅሞች
Author: solomon
Date: 2023-10-01
የሰይጣን መርፌጥቅሞች
🌵ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌵
፨የሰይጣን መርፌ - የዲያብሎስ ፀጉር ፣ የፍቅር ወይን እና ዉድቢን ተብሎም ይጠራል። የሚረግፍ ወይን ነው፣ በአንድ ወቅት 15 ጫማ አካባቢ ያድጋል። ይህ ተክል እንደ አርቦር፣ ትሬሊስ፣ አጥር፣ ዛፍ ወይም ቁጥቋጦ ካሉ ደጋፊ መዋቅር አጠገብ ቢተከል በጣም ጥሩ ነው።
፨ይህን ተክል በጣም ማራኪ የሚያደርገው አመታዊ፣አስደናቂ ማሳያ 1 እና 1/4 ኢንች፣ በጣም ጥሩ መዓዛ ያለው፣ የኮከብ ቅርጽ ያለው፣ ንፁህ ነጭ አበባዎች በብዛት ያመርታሉ። ነጫጭ አበቦቹ የሚመረቱት በበልግ ወቅት ነው
፨ለተለያዩ መፍትሔዎችና ለመድኃኒትነት
ይጠማል።
የሚሰጣቸውን ጥቅሞች
1ኛ
ለጠነከረና ለቆየ የአስም በሽታ
አጠቃቀም
በደንብ በስሎ ቀይ የሆነውን
ቅጠል ለቅሞ አድርቆ አሥቀምጦ ዕየወቀጡ በማር ዕየለወሱ መውሰድ።
የሚከለከሉ ነገሮች
የሎሚ ውሃና ወተት መጠጣት ክልክል ነው ።
2ተኛ
ለፀጉር ማሳመሪያ
አጠቃቀም
ለተመለጠ በጣም ለሳሳና ለተነቃቀለ ፀጉርና በዓይነቱ ጥቁር ሐር የመሰለ
ፀጉር የሚፈልጉ ከሆነ ቅጠሉን ብቻ ወቅጦ
አድርቆ ነፍቶ በኑግ ዘይት ዕየለወሱ ለተከታታይ
2 ሳምንት ከቀቡት የተመኙትንና የፈለጉትን የፀጉር ዓይነት ያገኛሉ፡፡
3ተኛ
ዕብድ ውሻ ለለከፈው ወይም ለታመመ
ሰውና በሆዱ ዕንደሥራይ ለሆነበት ሰው
መፍትሔ ይሆናል።
አጠቃቀም
የቅጠሉን ዱቄት በሻይ ማንኪያ ግማሽ የሚሆን በማር ለዉሶ መብላት ነው።
በ5ቀን ልዩነት ለ3 ጊዜ የቅጠሉን ዱቄት ግማሽ የሻይ ማንኪያ የሚሆን በማር ለዉሶ መብላት ነው በ5 ቀን ልዩነት ለ3 ጊዜ ይጠቀሙ፡:
4ተኛ
ለተቅማጥና ለማንኛውም ተላላፊ በሽታ ይሖናል።
አጠቃቀም
3ቱን ቅጠል ወቅጦ በማር ለውሶ መዋጥ ነው ለ3ቀን በቂ ነው፡፡
5ኛ
ለጄርባ ህመም ወይም ጀርባው ዕየወጣ ለሚቸገር ሰው መፍትሔ ነው።
አጠቃቀም
ርጥቡን ቅጠል ከነጭ ሽንኩርት ጋር ወቅጦ በትኩስ ቅቤ ለውሶ መቀባት ነው ይፈውሳል፡፡
6ተኛ
በሆዷ ዕንደአጥንት ሠርቶ ልክ ዕንደርጉዝ
ሴት ሆዷን ነፍቶ ወይም አሳብጦ
ለሚያስጨንቃት ማንኛዋም ሴት መፍትሔ
አጠቃቀም
ቅጠሉን ወቅጣ በወተት አፍልቶ መጠጣት
ለ2 ጊዜ በቂ ነው።
በ1ጊዜ ካልወጣ ግን ለ2ኛ ጊዜ መድገም ይቻላል፡፡
📚📚ጥበብን በማንኪያ የምትል መፀሐፉ በሀኪም ስለሞን አዳሙ የተዘጋጀ በማንኛውም መፀሐፉ መደብር ያገኛሉ📚📚📚
እናመስግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/