የትርፍ አንጀት ሕመም
   🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀    
              ምክንያቱ
፧የትርፍ አንጀት በሽታ ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው የትርፍ አንጀቱ በሰገራ፥ በሌላ እንግዳ አካል ወይም በካንሰር ስዘጋ ነው። የትርፍ አንጀት ሲቆስል ስለሚያብጥ የሚዘጋው በቁስለትም ሊሆን ይችላል።
በሽታው የሚከሰተው ባክተሪያዎች የትርፍ አንጀትን ግድግዳ ሲወሩትና ሲያቆስሉት ነው።
                       ምልክቶቹ
፧የትርፍ አንጀት በሽታ ምልክቶች በእርግጥ የህመሙን ስሜት ቦታ ለማመልከት አስቸጋር ቢሆንም በእምብርት አከባቢ የህመም ስሜት መሰማት፥ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፥ የሆድ ህመም እንደጀመረ ማቅለሽለሽና ማስታወክ፥ ከ38 እስከ 39.2 ድግር ሲሸልስ የሚደርስ የሰውነት ሙቀት መጨመር፥ ሽንት በሚሸናበት ጊዜ የህመም ስሜት መሰማት፥ እና ተቅማጥ ጥቅቶቹ ናቸው።
                    መከላከያው
፨በአብዛኛው ከፍተኛ የሆነ ቃጫነት ያለበትን ምግብ በብዛት በማይመገቡ አገሮች ውስጥ የትርፍ አንጀት በሽታ አናሳ እንደሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ። ይህ ለምን እንደሆነ በእርግጥ አይታወቅም፤ ሆኖም ግን እንደ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉት ከፍተኛ ቃጫነት ያለበት ምግብ ሰገራችንን ስለሚያለሰልሰው፥ በትርፍ እንጀት ሄደው መወተፍን ስለሚቀንስ ሊሆን ይችላል። ቃጫነት ያለባቸው ምግቦችም ሁሉም የአገዳ እህሎች፥ ስንዴ፥ ሩዝ እና ፓስታ፥ እንደ ካሮት ያሉ የሥራሥር አትክልቶች፥ እና ፍራፍሬዎች ናቸው። እነዚህን ምግቦች ማዘውተር የትርፍ አንጀት በሽታን ለመከላከል ይጠቅማል::
📚📚ጥበብን በማንኪያ የምትል መፀሐፉ በሀኪም ስለሞን አዳሙ የተዘጋጀ  በማንኛውም መፀሐፉ መደብር ያገኛሉ📚📚📚
           እናመሰግናለን
           መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/