የእግር ህመም መንስኤዎች
     🍀 ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
፨አብዛኛው የእግር ህመም
በመገጣጠሚያዎች ፣ በአጥንቶች ፣ በጡንቻዎች ፣ በጅማቶች ወይም ሌሎች ህብረ ህዋስ በመዳከም እና ከመጠን በላይ በመጠቀም ወይም በአደጋ ምክንያት ሊከሰት ይችላል። አንዳንድ የእግር ህመም ዓይነቶች በታችኛው አከርካሪ ላይ ባሉ ችግሮች ጋር ሊያያዙ ይችላሉ፡፡ የእግር ህመምም በደም መርጋት ፣ ቫሪኮስ ቬን ወይም በቂ የደም ዝውውር ባለመኖሩ ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡፡
         የእግር ህመም ምክንያቶች
🌵የሪህ በሽታ
🌵የደም መርጋት ችግር
🌵የአከርካሪ ችግር
🌵የሳያቲካ ችገር
🌵የአጥንት ኢንፌክሽን 
🌵ውልቃት
🌵የኩላሊት በሽታ
🌵የነርቭ ችግር
🌵በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ አደጋዎች
      ኢንፌክሽኖች
       የእግር ህመም አይነቶች
፨ ፊት እግርዎ ወይም ቁርጭምጭሚትዎ ላይ ህመም ከጀመረዎ ብዙ ጊዜ የሺን ስፕሊንት ምልክት ነው ። ይህ ህመም የሚፈጠረው በእንቅስቃሴ እግራችን ላይ ጫና ስንፈጥር ነው። ሰውነታችን ከለመደው ደረጃ በላይ እንቅስቃሴ ስናደርግ ስሜቱ ይፈጠራል።
፨ የእግር እስትራፖ፡- ከፍተኛ እንቅስቃሴ ወይም የውሃ ጥማት እግር ላይ የጡንቻ መሳሳብ ወይም እስትራፖ እንዲፈጠር ያደርጋል አንዳንድ ግዜ ከተለመዱ ነገሮች ወጣ ያሉ ነገሮችን ስናደርግ ለእንደዚህ አይነት ችግር እንድንጋለጥ ያደርገናል ፡፡
፨ የቁርጭምጭሚት ህመም፡- ሲንቀሳቀሱ ወይም ቁርጭምጭሚትን ሲጫኑ የህመም ስሜቱ የሚጨምር ወይም እብጠት ካለው እና ቀላ ህመም ሊኖርብዎ ይችላል ።
፨ የታፋ ህመም፡- የቀን ሰራተኞች እና ሌሎች ከፍተኛ ጭነት የሚሸከሙ ሰዎች በታፋ ህመም በመጠቃት ይታወቃሉ ። የዚህ ምክንያት ዳሌ ዙሪያ የሚገኝ ነርቭ ላይ ጫና በመፈጠሩ ነው ።
                👉 መፍትሄ
፨ለእግር ህመም የሚሰጡት የህክምና ዓይነቶች ከቀላል የነርቭ ህክምና እስከ ቀዶ ህክምና ድረስ የሚዘልቁ ሲሆን በደም ዝውውር መዘጋት ሳቢያ የተከሰተ የእግር ህመም የተዘጋውን የደም ዝውውር በመክፈት የታማሚውን ጤና ወደነበረበት ለመመለስ የሚያስችል የህክምና ዘዴ አለ፡፡
፨ የእግር ህመም ከመከሰቱ በፊት በእነዚህ መንገዶች መከላከል እንችላለን፡-
ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል፣
የሰውነት ክብደትን መቀነስ
ቀለል ያሉና ምቾት የሚሰጡ ጫማዎችን መጠቀም፣
የኩላሊት የጉበት፣ የልብና የደም ግፊት በሽታዎችን በወቅቱ መታከም ዋንኞቹ የእግራችንን ጤና መጠበቂያ መንገዶች ናቸው፡፡
📚📚ጥበብን በማንኪያ የምትል መፀሐፉ በሀኪም ስለሞን አዳሙ የተዘጋጀ በማንኛውም መፀሐፉ መደብር ያገኛሉ📚📚📚
እናመሰግናለን
           መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/