የብሳና ዛፍ አስገራሚውጥቅሞች
Author: solomon
Date: 2023-09-19
የብሳና ዛፍ አስገራሚው ጥቅሞች
🌴ከሀኪም ስለሞን አዳሙ🌴
🌴የብሳና ዛፍ አስገራሚ ጥቅሞች🌴 ተአምረኛው ዛፍ ብሳና ከዕፀዋት ሁሉ ይለያል
የብሳና ዛፍ ሳይንሣዊ መጠሪያ ስሙ
🏝️🏝️🏝️🏝️🏝️🏝️🏝️🏝️🏝️🏝️🏝️
በእንግሊዘኛው (croton macrostachyus tree )ተብሎ ይጠራል
ይህ ዕፅ ከሌሎች ዕፀዋቶች በተለየ ሁኔታ ዕጅግ አስገራሚ ጥቅሞች አሉት
🌴ብሳና ኢትዮጵያ ሐገራችን ጨምሮ በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኝ የዛፍ ዓይነት ነው
🌴🌴 በባህላዊ ህክምና የተለመደና ለተለያዩ መድኃኒቶች ግብዓት በመሆንም ያገለግላል
የብሳና ቅጠሉ ልጡ ሥሩ ፍሬውና ግንዱ ለተለያዩ ጥቅሞች ይውላል ;:
🌴🌴ከዚህ በመቀጠል የብሳና ዛፍ ጥቅሞች
በዝርዝር ዕንደሚከተለው አቀርብላችኋለሁ
👉👉👉አጠቃቀም
፨1ኛ ለሆድ ውስጥ ሥራይ የብሣናውን የሥሩን ልጣጭ
ልጦ በመጥረቢያ ከትክቶ አፈሩን በማጠብ ወቅጦ በንጹህ ውሃ ዘፍዝፎ ጧት ጧት ከምግብ በፊት እያጠለሉ በውሃ ብርጭቆ ከ1-- 5 ቀን መጠጣት ነው
፨2ኛ ለሣል በሽታ ቅጠሉን እየቀቀሉ ማታ በመኝታ ሰዓት እየታጠኑ መተኛት ነውከ። 1---10 ቀን ቢሆን ሣሉን ነቅሎ ይጥለዋል
፨3ኛ ለውሻ ልክፍት በሽታ የሥሩን ቅርፊት
ከመካን ዕንዶድ ሥር ገር ወቅጦ አድርቆ ዱቄቱን ከጥቁር ጤፍ ዱቄት ቀላቅሎ ሃምሣ ሳንቲም የሚያክል እየጋገሩ በባዶ ሆድ ለ3 ቀን መብላት
፨4ኛ ለወፍ በሽታ የብሳና ቀንበጡን ከሰንሰል/ከስሚዛ ቀንበጥ ጋር ወቅጦ ዕንደሽሮ በመስራት ቅቤ ጨምሮ በባዶ ሆድ መብላት ነው
፨ 5ኛ አንገት ላይ ለሚወጣ ጭርት ፍሬውን ብቻ አሽቶ መቀባት ነው
፨6ኛ ለቋቁቻና ለችፌ ፍሬውንና ቀንበጡን ከነጭ ሽንኩርት ጋር ወቅጦ መቀባት ነው
፨7ኛ ለማንኛውም ቁስል ልጡን አድርቆ ወቅጦ በቁስሉ ላይ መነስነስ ነው ፈፅሞ ይድናል
፨8ኛ ለምች ህመም ቅጠሉን ከነጭ ባህሕርዛፍ ጋር ቀቅሎ መታጠን ይበጃል ፨ 9ኛ ለኪንታሮት በሽታ ሥሩን በመጥረቢያ ላፍ ላፍ አድርጐ በትንሹ ወቅጦ እየቆሰለና ዕየደማ ለሚያስቸግር ኪንታሮት ማታ ኪንታሮቱ ላይ ደምድሞ መተኛት ሁነኛ መፍትሔ ነው
፨ 10ኛ ለሆድ ትላትልና ለወስፋት በውሃ በጥብጦ አሳድሮ
ከምግብ በፊት አጥልሎ መጠጣት ነው።
📚📚📚ጥበብን በማንኪያ የምትል መፀሐፉ በሀኪም ስለሞን የተዘጋጀ በማንኛውም መፀሐፉ መደብር ያገኛሉ 📚📚📚
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴ለማንኛውም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
፤ ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
፤አድራሻ፦ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
፤ስልክ፦ 0989020202 ወይም 0911810736
website ፦www.hakimsolomon.com
Telegram፦https፡//t.me/