የቴምር ጥቅሞች
Author: solomon
Date: 2023-09-06
ቴምር መብላት ያለው 8 ጥቅሞች
🌵ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌵
፨ቴምር በውስጡ ለሰውነት ጠቃሚ የሆኑ ብዙ ንጥረ ነገሮችን ይዟል።
ቴምር ከፍተኛ የስኳር መጠን ስላለው አብዝቶ መብላት አይመከረም። በቀን ውስጥ የተወሰኑ ቴምሮችን መብላት ጥቅሞቹን ለማግኘት በቂ ነው።
ቴምርን አስፈላጊ የሚያደርጉት 8 ጥቅሞች እነሆ
1) ሃይል ይጨምራል
ፈጣን ሃይል ለማግኘት ከፈለጉ ቴምርን መብላት ይጠቅመዎታል።
2) የሆድ ድርቀትን ይከላከላል
ቴምር ሆድን በማለስለስ የሆድ ድርቀት ያለባቸውን ሰዎች ይረዳል። ቴምር የሚሟሟ ፋይበር አለው። ምግብ ገብቶ በተለሳለሰ ሁኔታ እንዲወጣ ያስችላል።
3) የደም ማነስን መከላከል
የደም ማነስ የሚከሰትበት አንደኛ ምክንያት የአይረን እጥረት ነው።
ቴምር ውስጥ ያለው አይረን የሄሞግሎቢን ምርት በመጨመር የደም ማነስ ወይም አኒሚያን ይከላከላል። በተጨማሪም ቴምር ውስጥ ያለው ቫይታሚን ሲ አይረኑ ከሰውነታችን ጋር እንዲዋሃድ አስተዋጾ ያደርጋል።
4) ለእርግዝና
ቴምር እርግዝናን የሚጠቅሙ በርካታ ንጥረ ነገሮች አሉት። ጥቅሙ ለእናትም ለተጸነሰውም ልጅ ሲሆን በእርግዝና ግዜ የተለመደውን የሆድ ድርቀት ይከላከላል።
ከዛም አልፎ የማህጸን ጡንቻን በማጠንከር ልጅ መውለድ እንዲቀል ይረዳል። በ2011 የታተመ ጥናት ሊወልዱ በቀረቡበት ወቅት ቴምር የሚበሉ ሴቶች የሌላውን ያህል የወሊድ እገዛ እንደማያስፈልጋቸው ይናገራል።
5) የሃንግኦቨር ስሜት ያጠፋል
ቴምርን በመብላት የሃንግኦቨርን ስሜትን መዋጋት ይቻላል። ቴምር በጉበታችን የሚፈጠርን መርዛማ ነገር በማጽዳት ይታወቃል።
6) የልብ ጤናን ለመጠበቅ
ቴምር በጸረሃይፐርሊፒዴሚክ ባህሪው ምክንያት ለልብዎ ጤና ጥሩ ነው። ውስጡ ያለው ዝግተኛ ሶዲየም መጠን እና ከፍተኛ የፖታሲየም መጠን ልባችን የተስተካከለ ምት እንዲኖረውና የደም ግፊታችን በቁጥጥር ስር እንዲውል ይረዳል። ፖታሲየም የስትሮክ እና ሌሎች የልብ ህመሞችን በመከላከል ይታወቃል።
7) የነርቭ ግንድን ማጠናከር
ቴምር ውስጥ ያሉት ቫይታሚኖች የነርቮቻችን ጤና ለመጠበቅ ይረዳሉ። ጤነኛ የነርቮች ስብስብ ሁሉም ያካላችን ክፍል እንዲግባቡ ያደርጋል።
8) የአንጓ ብግነት(አርትራይትስ) ቃጠሎን ያስታግሳል
ቴምር የአንጓ ብግነት በሽታ ያለባቸው ሰዎች መገጣጠሚያቸው ላይ የሚሰማቸውን ህመም እና የቃጠሎ ስሜት የሚያስታግስ የጸረኦክሲዳንት እና የጸረቃጠሎ ባህሪዎች አሉት
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
📚📚ጥበብን በማንኪያ የምትል መፀሐፉ በሀኪም ስለሞን አዳሙ የተዘጋጀ በማንኛውም መፀሐፉ መደብር📚📚📚
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/