ስለ ሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ግንዛቤ
Author: solomon
Date: 2023-09-03
ስለ ሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ግንዛቤ
🌵 ከሀኪም ስለሞን አዳሙ🌵
የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን (Urinary Tract Infection (UTI)):- ማለት ሽንት ከሰውነታችን ለማስወገድ የሚጠቅሙ የሰውነት ክፍሎች፤ ማለትም:- ኩላሊት፣ የሽንት ፊኛ፣ ዪሬትራ እና ዩሬተር (የሽንት ቱቦዎች) በባክቴሪያዎች ሲጠቁ የሚፈጠር ኢንፌክሽን ነው።
🌵የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ምልክቶች
📌 ሽንት ሲሸኑ ማቃጠል
📌 ከእንብርት በታች ህመም
📌 የጎን ህመም
📌 የሽንት ቀለም መቀየር
📌 መጥፎ ጠረን ያለው ሽንት
📌 የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት እና ለመሽናት መጣደፍ
📌 የሽንት መጠን መቀነስ እና ከሸኑ በኋላ ያለመጨረስ ወይም የሽንት መንጠባጠብ
📌 ትኩሳት
📌 ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
🌵ለሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን አጋላጭ ሁኔታዎች
📌 የኩላሊት ጠጠር በሽታ
📌 በሽታን የመከላከያ ሥርዓታችንን የሚያጠቁ ወይም አቅሙን የሚቀንሱ በሽታዎች (የስኳር በሽታ፣ ኤች.አይ.ቪ እና የሚጥል በሽታ)
📌 እርግዝና
📌 በሰው ሰራሽ የሽንት ቱቦ መጠቀም
📌 በማህፀን የሚቀበሩ አንዳንድ የወሊድ መከላከያዎች
📌 ያልተገረዘ ወንድ
📌 የፕሮስቴት እጢ ማደግ
🌵 የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን መከላከል ዘዴዎች
📌 ሽንት በሚሸኑበት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ወጥቶ እስኪያልቅ መጠበቅ ወይም አለማቋረጥ
📌 ከግብረ-ሥጋ ግንኙነት በኋላ ቶሎ መታጠብ
📌 በምንጸዳዳበት ወቅት ከፊት ወደ ኋላ መታጠብ
📌 በቀን ውስጥ ከ ሁለት ሊትር በላይ ውሃ መጠጣት
📌 አትክልትና ፍራፍሬ በደንብ መመገብ
📌በቀን ውስጥ በጣም በተደጋጋሚ አለመታጠብ
📌 ሽንታችን ሲመጣ ቶሎ መሽናት ወይም ይዞ አለመቆየት (አለመቋጠር)
🌵ለሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን የሚደረግ ህክምና
📌ውሃ በደንብ መጠጣት ቢያንስ በቀን ከሁለት ሊትር በላይ
📌 በቂ እረፍት ማድረግ
📌 ሽንት ሲመጣ ወዲያዉኑ መሽናት
📌 የሽንት ቱቦ መቆጣትን የሚያባብሱ ነገሮችን እንደ አልኮል እና ቡና መቀነስ በምትኩ የእንጆሪ እና አናናስ ጭማቂ እንዲወስዱ ይመከራል፡፡
📌 ከሽንት ምርመራ በኋላ ጸረ ባክቴሪያ መድሐኒት መውሰድ።
📚📚 ጥበብን በማንኪያ የምትል መፀሐፍ በሀኪም ስለሞን አዳሙ የተወጋጀ በማንኛውም መፀሐፍ መደበር ያገኛሉ📚📚
እናመስግናለን
መልካም ጤንነት
🌵🌵 የማንኛውም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶች እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግነት ይችላሉ🌵🌵🌵
"ለበለጠ መረጃ ፦ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
"አድራሻ፦ባሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
"ስልክ፦0989020202 ወይም0911810736
"website፦www.hakimsolomon.com
"Telegram፦https፡//t.me/