የሽንብራ ጥቅም
🌿 ከ ሀኪም ስለሞን አዳሙ🌿
ሽንብራ ከፍተኛ ፋይበር ፣ ፖታሲየም ፣ ቫይታሚን ሲ እና ቫይታሚን ቢ-6 ይይዛል ፣ ሁሉም የልብ ጤንነትን ይደግፋሉ። የእፅዋት ፕሮቲኖችንም ፣ አብዛኛዎቹን አስፈላጊ አሚኖ አሲዶችን ይይዛል።

አንዳንድ ጥናታዊ ዘገባዎች እንደሚያስረዱት ሽምብራ ለአንዳንድ ሥር የሰደዱ (Chronic) በሽታዎች እንደ የልብ ሕመም ፣ የስኳር በሽታንና አንዳንድ የካንሰር ዓይነቶችን ለመከላከል የሚረዱ እንደ ፎሌትስ (Foliates) ፣ ጥሩ ፋቲ አሲድ (Good Fatty Acid) እና ኩኤርሰቲን (Quercetin - a plant pigment) ያሉትን ያዘለ ነው።

ሽምብራ ከእጸዋት በሚገኙ ፊቶስትሮሎች (Phytosterols) የበለፀገ ስለሆነ
በደም ውስጥ የሚዘዋወረውን 'የመጥፎውን' LDL (Low Density Lipid) 'ስብ' መጠንን ለመቀነስ ይረዳል።

ሽምብራ ውስጥ የሚገኘው ከፍተኛ ፋይበር (Fiber) በደም ውስጥ ያለውን አጠቃላይ የኮሌስትሮል (Cholesterol) 'ስብ' መጠንን በመቀነስ ስብ ሊያስከትል ከሚችለው የልብ በሽታ የመጠቃት እድልን ለመቀነስ ይረዳል። ለዚህም ነው ፋይበር አዘል ምግቦችን አዘውትሮ መመገብ የኮሌስትሮልን መጠን ለመቀነስ በጣም የሚረዳው። ይህም የሚሆነው
፣ የተመገብነው ፋይበር በትንሹ አንጀታችን ውስጥ እንደ thick gel ይሆንና በቀላሉ ስለማይሟሟ የምግብ መፈጨትን ያዘገያል (ያ ደግሞ ስኳር በደም ውስጥ በብዛት እንዳይወጣም ይከላከላል) እንዲሁም ኮሌስትሮልን (ስብ- fat) በማጥመድና ከእሱ ጋር በመጣበቅ (binding) ኮሌስትሮል በደማችን (blood stream) ውስጥ ገብቶ ወደ ሌሎች የሰውነታችን ክፍሎችም እንዳይጓዝ ይከላከላል
በአጠቃላይ የኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል ፣ ብሎም ያስወግደዋልም)። እንደ ጥናቶች ዘገባ ፣ በቀን ከ5 እስከ 10 ግራም ፋይበር መመገብ LDL- ኮሌስትሮልን ከ5 እስከ 11 ነጥብ (አንዳንዴም በይበልጥ) ዝቅ ለማድረግ ያስችላል።

በተጨማሪም ሽምብራ በፖሊፊኖሎችም የበለፀገ በመሆኑ እንደ አንቲኦክሲዳንትስ እና እንደ Antiinflammatory ሁኖ ለሰውነታችን ይጠቅማል።

ሽምብራ በውስጡ በያዘው ኦሊጎሳካራይዶች ምክንያት የሆድ መታወክንና ድርቀትን ሊያስከትል ይችላል ፤ ይህ ደግሞ በትልቁ አንጀት ውስጥ ጋስ እንዲከማች ያደርጋል። ይህን ለመከላከል ፣ ሽምብራን ከማብሰል በፊት በደንብ በውኃ በመዘፍዘፍ ሊፈጠር የሚችለውን የጋዝ መጠን መቀነስ ይቻላል። ሽምብራን በመዘፍዘፍ የማይፈለጉ ኤንዛይሞችም ይወገዳሉ።

እንደ አንዳንድ ጥናታዊ ዘገባዎች ሽንብራ (ብዙ ፋይበር ስላለው) ለክብደት መቀነስ ጠቃሚ እንደሆነ ነው (ክብደትን ለመቆጣጠር ሊረዳ ይችላል)።

ስጋን ወይም የእንስሳት ተዋጽኦዎችን ለማይበሉ ሰዎች ሽምብራ ጥሩ ምግብ ነው። አረንጓዴው ሽምብራ በይበልጥ ነው።
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴የማንኛውም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግነት ይችለሉ🌴🌴🌴
፨ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
፨አድራሻ፦ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
፨ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
፨website፦www.hakimsolomon.com
፨ስልክ፦ 0989020202 ወይም0911810736
፨ Telegram፦https፡//t.me/