የናና ቅጠል ጥቅሞች
            🌴 ከሀኪም ስለሞን አዳሙ 🌴
ወደ ገጠራማው የሀገራችን ክፍል ወጣ ስንል በየተራራው እና በየመንገዱ ዳር የሚበቅል እጅግ የሚማርክ መአዛ ያለው ተክል ነው፡፡ ይህ የቅመም ዘር ደርቆና በርጥብነቱ ልንጠቀመው እንችላለን፡፡ የሚንት ዘይት ለጥርስ ሳሙና፣ ለመስቲካ፣ ለከረሜላ እና የውበት መጠበቂያ ምርቶችን ለማምረት በግብአትነት ያገለግላል፡፡ እስከ 20 የሚደርሱ የተለያዩ የሚንት ዝርያወች አሉ፡፡ የናና ቅጠል በቀላሉ መብቀል ሲችል በምግብ እና ሻይ ውስጥ በመጨመር የተሻለ ጣእም እንዲሰጠን ያደርጋል፡፡ ከፍተኛ የሆነ የአንቲ ኦክሲደንት ይዘት ያለው እጽዋትም ነው፡፡

ይዘት፡ 100 ግራም የጦስኝ ቅጠል
፨ ሀይል----------44ኪሎ ካሎሪ
፨ ካርቦ ሀይድሬት----8.41 ግራም
፨ ስብ--------------0.73 ግራም
፨ ፕሮቲን----------3.29 ግራም
፨ አይረን------11.87ሚሊ ግራም
፨ ኮፐር-------0.240 ሚሊ ግራም
፨ ፖታሺየም---458 ሚሊ ግራም
፨ ቫይታሚን ሲ--13.3ሚሊ ግራም እና ሌሎችም

ይህ ቅጠል በራካታ ጠቀሜታወች ቢኖሩትም የተወሰኑት ለማየት ያክል፡-
1፦ለቆዳ መቆጣት (ለአለርጂ)፡- የሚንት ቅጠል በውስጡ የሚይዘው ሮዝማርኒክ አሲድ ወቅታዊ የሆነ የቆዳ መቆጣትን (አለርጂክን ) ተፈጥሮአዊ በሆነ መልኩ ለማከም ያስችላል፡፡
2፦ጡት ለማጥባት፡- የሚንት ቅጠል ጡት ለምታጠባ እናት እና ለጨቅላው ጠቃሚ ነው፡፤በውስጡ የሚይዘው ንጥረ ነገር የጡት ጫፍ ህመሞችንና መሰንጠቅን ይከላከላል፡፡
3፦ ጉንፋንን ለማከም ፡- የጦስኝ ሻይ በተለይ በጉንፍን ምክንያት የተዘጋን ጉሮሮ በመክፈት ያለው ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡
4፦ለሆድ ህመም፡- የናና ቅጠል ለረዥም ዘመን የሆድ ህመም እና የምግብ አለመፈጨትን እንደ መፍትሄ ሆኖ ሲያገለግል ኖሯል፡፡ የሆድ ህመም የሚያስቸግራቸው ሰዎች ከሱፐር ሚንት የሚዘጋጅ መድሃኒት ለአራት ሳምንት በቀን ሁለት ግዜ በመውሰድ ህመማቸውን ከ50 በመቶ በላይ መቀነስ ይችላል፡፡
5፦የህመም ማስታገሻ፡- የቡሽሜን ማህበረሰብ የብራዚል ሜንትን ልክ እንደ አስፕሪንኪኒን በመጠቀም ከህመማቸው ማረፍ(ማስታገስ) እንደሚችሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
6፦ለቆዳ፡- ብዙን ግዜ ቆዳችን በትንኝ ንክሻ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ሊጎዳ ይችላል፡፡ከናና የሚዘጋጅ የውበት መጠበቂያ ሎሽኖች ፍቱን መፍትሆ መሆናቸው ተደርሶበታል፡፡
7፦ለአፍ ውስጥ ጤንነት፡- የናና ቅጠል ተፈጥሮአዊ ጸረ-ተህዋሲያን ንጥረ ነገር በውስጡ በመያዙ ለአፍ ውስጥ ጤንነት እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ በተጨማሪም መልካም የአፍ ጠረን እንዲኖር ያደርጋለል፡፡

የናና ቅጠል የጎንዮሽ ጉዳት ሊኖረው ስለሚችል ስንጠቀም በጥንቃቄ መሆን ይኖርብናል
🌿እጅግ መጠኑ የበዛ ጦስኝ መጠቀም አይመከርም
🌿ለህጻናትና ለጨቅላዎች የሚንት ዘይት መቀባት አደገኛ ነው
🌿 የሀሞት ጠጠር ያለበት ሰው ናና(ሚንት) መጠቀም አይኖርበትም
🌿ነፍሰጡር ለሆኑ ሴቶች  እንዲጠቀሙ አይመከርም፡፡
           እናመሰግናለን
       መልካም ጤንነት
🌴🌴 የማንኛውም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ይችላሉ🌴🌴🌴
፣ ለበለጠ መረጃ፦ ወደ  ቅዱስ ሚካኤል  የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
፣ አድራሻ፦ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
፣ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችለሉ።
፣website፦ www.hakimsolomon.com
፣ስልክ ፦ 0989020202 ወይም 0911810736
፣Telegram፦https፡//t.me/