የመቅመቆ ጥቅሞች
Author: solomon
Date: 2023-08-05
የመቅመቆ ጥቅሞች
🌵ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌵
፨መቅመቆ ከትሮፒካል ክልል እፅዋት ወስጥ የሚመደብና ወቅትን ሳይጠብቅ አመቱን ሙሉ ሊበቅል የሚችል የዛፍ ዝርያ ሲሆን ፤ ቁመቱ ከ 3 እስከ 4 ሜትር ድረስ ይረዝማል፡፡ ይኽ የዕፅዋት ዝርያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅና በመካከለኛው የአፍሪካ ክፍል ይበቅላል፡፡መረጃዎች እንደ ሚያመላክቱት ለሰው ልጆች ከፍተኛ ጥቅም በመስጠት የሚታወቀው የዛፉ የሥርኛው ክፍል ወይም ስሩ ሲሆን፤በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ አካባቢ በስፋት ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፡፡የመቅመቆ ስር በሻይ መልክ ተፈልቶ ሲጠጣ ለብዙ በሽታዎች በመድሃኒትነት ሲያገለግል በዋነኛነት ለደም ብዛት አይነተኛ ፈውስ እንደሚሰጥ ብዙዎች ይመሰክሩለታል፡፡ መቅመቆ በሲዳማ ብሔረሰብ ውስጥም በስፋት የሚታወቅ ሲሆን ፤ በሻይ መልክ ከማዘጋጀት በተጨማሪ ለጋ የሆነውን ስር በማኘክ የሌሊት ወፍ በሽታን ለማከም እንደሚጠቀሙበት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በ18ኛው ክ/ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ስኮትላንዳዊው አሳሽ ጀምስ ብሩስ እንደዘገበው የአገው አካባቢሰዎችም ይህንን ተክል ለመዋቢያነት ይጠቀሙበት እንደነበረና የሙሽሮች እጆችንና እግሮቻቸውን ጥፍሮች በማቅለም ይዋቡበት እንደነበር ተመልክቷል፡፡
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/