የበለስ ፍሬ የጤና በረከቶች
🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀

፨በለስ በአብዛኛው በሞቃታማ እንዲሁም በረሃማ አካባቢዎች ላይ የሚበቅል የፍራፍሬ አይነት ሲሆን፥ ፍሬውም ሆነ ቅጠሉ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይነገራል።
በአገራችንም በአብዛኛው የትግራይ ክልል ፣ በባሌ እንዲሁም በሌሎችም አንዳንድ አካባቢዎች በክረምት ወራት በይበልጥ ይበቅላል።
በመላው አለም በተለይም በላቲን አሜሪካ አገራትም የተለመደ የፍራፍሬ አይነት ነው።
የበለስ ፍሬ ለጤና ከሚሰጣቸው ጥቅሞች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
1.የማቃጠል ስሜትን ያጠፋል
በለስ ከአመጋጋብ ጋር በተያያዘ ጨጓራችን ላይ የሚከሰትን የማቃጠል ህመም የማጥፋት ተፈጥሯዊ አቅም አለው።በመሆኑም በለስን በመመገብ በጨጓራችን ላይ የሚከሰትን የማቃጠልና የምቾት ማጣት ስሜትን በቀላሉ ማስቀረት እንችላለን።

2.በአንቲ ኦክሲዳንትስ የበለፀገ ነው
በተጨማሪም በሰውነታችን የተለያዩ ውስጣዊ ክፍሎች ውስጥ አላስፈላጊ የስብ ክምችት እንዳይፈጠር ያግዛል።

3.በቫይታሚን ሲ የበለፀገ ነው
በአንድ ኩባያ የካክተስ ፍሬ ውስጥ ከ21 ሚሊግራም በላይ የቫይታሚን ሲ ይዘት እናገኛለን ።
ከዚህም በላይ በበለስ ውስጥ የምናገኘው የቫይትሚን ሲ ይዘት በተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅማችን በእጅጉ እንዲጎለብት ያደርጋል።
በበለስ ውስጥ የሚገኘው ኮላጅን የተሰኘው ንጥረ ነገርም ለጤነኛ ቆዳ፣ የአጥንት መገጣጠሚያ እና የሰውነት ህዋስ አመራረት በእጅጉ ያግዛል ነው የተባለው።

4.ጥሩ የካሎሪ ምንጭ ነው፣
በአንድ ኩባያ የካክተስ ፍሬ ውስጥ ከ61 ካሎሪ በላይ የምናገኝ ሲሆን፣ 5 ነጥብ 4 በመቶ ፋይበር፣ እጅግ አንስተኛ ፋት፣ 328 ሚሊ ግራም ፖታሲየም፣ 127 ሚሊ ግራም ማግኒዚየም ፣ ቫይታሚን ኤ ፣ ፎሊክ አሲድ ወይም ፎሌት (ለደም ማነስ ችግር መፍትሄ ነው) እንዲሁም የበርካታ ቫይታሚን ቢ አይነቶችንም በውስጡ ይዟል።

እናመሰግናለን
           መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/