7ቱ የሙዝ ጥቅሞች ለውበታችን
Author: admin
Date: 2023-05-04
7ቱ የሙዝ ጥቅሞች ለውበታችን
🍀 ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
1. ሙዝ ደረቅ የፊት ቆዳን ወዝ እንዲኖረው ያደርጋል
ሙዝ ቫይታሚን ኤ ስላለው የፊታችን ቆዳ ወዝ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡እንዲሁም በድርቀት የተጎዳን ቆዳ ይጠግናል፡፡
🌵አንድ የበሰለ ሙዝ መፍጨት
🌵አንድ የሾርባ ማንኪያ ማር ሙዙ ላይ መጨመር እና በደንብ መቀላቀል
🌵ውህዱን ንፁህ ፊት ላይ መቀባት እና ለ 30 ደቂቃ መጠበቅ
🌵 ከ30 ደቂቃ በኋላ ፊታችንን ለብ ባለ ውሃ ብቻ መታጠብ
2. ሙዝ የተሰነጣጠቀ ተረከዘን ያስተካክላል
🌵መጀመሪያ እግራችንን ሞቅ ባለ ውሃ ውስጥ ለ10 ደቂቃ መዘፍዘፍ (ከተቻለ ሁለት የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ ጨምሮ እግራችንን መዘፍዘፍ)
🌵ከዛ በኋላ እግራችንን ማድረቅ
🌵ሁለት የበሰለ ሙዝ መፍጨት
🌵 የተፈጨውን ሙዝ ንፁህ ተረከዝ ላይ መቀባት
🌵 ሙዙ ተረከዛችን ላይ እንዲቆይ እግራችንን በላስቲክ መጠቅለል እንችላለን
🌵ከ20 ደቂቃ በኋላ በቀዝቃዛ ውሃ እግራችንን መታጠብ
3. ሙዝ የፊታችን ቆዳ እንዳይሸበሸብ እና እንዳያረጅ ይረዳዋል
ሙዝ ቫይታሚን ኤ እና ኢ ስላለው ቆዳችን እንዳይሸበሸብ እና በቀላሉ መለጠጥ እንዲችል ይረዳዋል፡፡
🌵አንድ የበሰለ ሙዝ መፍጨት
🌵ሁለት የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ አቮካዶ ሙዙ ላይ መጨመር እና በደንብ መቀላቀል
🌵 ውህዱን ንፁህ ፊት ላይ መቀባት እና ለ 30 ደቂቃ መጠበቅ
🌵ከ30 ደቂቃ በኋላ ፊታችንን ለብ ባለ ውሃ ብቻ መታጠብ
4. ሙዝ የተጎዳ እና የተሰባባረን ፀጉር ይጠግናል
🌵አንድ የበሰለ ሙዝ መፍጨት (ሙዝ ለፀጉር ስንጠቀም በደንብ ላም ብሎ መፈጨት አለበት)
🌵ሶስት የሾርባ ማንኪያ አቮካዶ እና ግማሽ ኩባያ እርጎ ከሙዙ ጋር በደንብ ማቀላቀል
🌵ውህዱን ፀጉራችንን ላይ መቀባት እና ለ 30 ደቂቃ መተው
🌵 ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ ፀጉራችንን ለብ ባለ ውሃ እና በሳሙና/በሻምፖ በደንብ መታጠብ
ለውበት የሚጠቅሙ ፅሁፎችን ለማንበብ ገፃችን ላይክ ያድረጉ፡፡
ለአንቺ
5. ሙዝ ብጉርን ያጠፋል
🌵 አንድ የበሰለ ሙዝ መፍጨት
🌵 አንድ የሾርባ ማንኪያ ማር፤ አንድ የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ ሙዙ ላይ መጨመር እና በደንብ መቀላቀል
🌵ውህዱን ንፁህ ፊት ላይ መቀባት እና ለ 30 ደቂቃ መጠበቅ
🌵ከ30 ደቂቃ በኋላ ፊታችንን በቀዝቃዛ ውሃ ብቻ መታጠብ
ሌላው መንገድ ደግሞ የሙዝ ልጣጩን በውስጠኛው በኩል አድርገን ብጉር የሚወጣበትን አካባቢ ላይ መለጠፍ ወይም ማሸት (ቀስ ብለን ብጉሩን ሳናፈርጠው ነው መቀባት ያለብን) እና ከ 20 ደቂቃ በኋላ ፊታችንን በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ፡፡
6. ሙዝ ጥሩ እንቅልፍ እንድንተኛ ያስችለናል
ውበታችንን ለመጠበቅ ከሚያስፈልጉን ነገሮች አንዱ እና ዋነኛው በቂ እንቅልፍ ማግኘት ነው፡፡ሙዝ ጥሩ እንቅልፍ እንድንተኛ ይረዳናል፡፡
🌵አንድ ሙዝ መቆራረጥ
🌵 ሙዙን በአንድ ስኒ ውሃ አድርጎ እሳት ላይ መጣድ
🌵 ግማሽ የቡና ማንኪያ ቀረፋ መጨመር (ቀረፋው በጣም ትንሽ ነው መሆን ያለበት) እና ከ 5 ደቂቃ በኋላ ማውጣት
🌵 ውህዱን መብላት
🌵ይሄንን የምናደርገው ወደ አልጋ ከመሄዳችን ከ 30 ደቂቃ በፊት ቢሆን ይመረጣል፡፡
7. ሙዝ ፀጉራችን ጥሩ ወዘና እንዲኖረው ያደርጋል
🌵አንድ የበሰለ ሙዝ መፍጨት (ሙዝ ለፀጉር ስንጠቀም በደንብ ላም ብሎ መፈጨት አለበት)
🌵ሁለት የሾርባ ማንኪያ የወይራ ዘይት እና አንድ የእንቁላል ነጩን ክፍል ብቻ ከሙዙ ጋር በደንብ መቀላቀል
🌵ውህዱን ፀጉራችንን ላይ መቀባት እና ለ 30 ደቂቃ መተው
🌵ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ ፀጉራችንን በቀዝቃዛ ውሃ እና በሳሙና/በሻምፖ በደንብ መታጠብ
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
መልካም ጤንነት
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna