የፌጦ አስገራሚ ጠቀሜታ
Author: admin
Date: 2023-04-26
የፌጦ አስገራሚ ጠቀሜታ
🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
1. ለመተንፈሻ አካል ችግር
-ለጉንፋን፣ አስም፣ ሳል፣ ራስ ምታት፣ ለጉሮሮ ቁስል ሁለት ማንኪያ ፌጦ ፈጨት አድርገው ከማር ጋር በመለወስ ይዋጡት፡፡
2.ለ አይረን ማነስ ምክንያት የሚከሰትን አኒሚያ የተሰኘ በሽታን ለማቃለል
ከፍተኛ የብረት ማዕድን የያዘው ፌጦ በአንጀታችን ውስጥ በቀላሉ ስለሚመጠጥ በደም ውስጥ የሚገኘውን የሂሞግሎቢን መጠን ይጨምራል፡፡
3.የቆዳ ችግርን ለማስተካከል
በፀሐይ የተቃጠለ ቆዳ፣ የተቆጣ ቆዳ፣ ደረቅ ቆዳ ካሎት የተፈጨ ፌጦ ከማር ጋር ቀላቅለው ይቀቡት ችግሩን ለማባረር ይረዳዎታል፡፡
4.ለአንጀትና ለሆድ ዕቃ ሕክምና
ለተቅማጥ፣ ለሆድ ድርቀት እና ለምግብ ያለመንሸራሸር ወይም የመፈጨት ችግር ሁነኛ መፍትሔ ነው፡፡ በተላይ የፌጦ ፍትፍት ምርጥ ነው፡፡
5. ደም ግፊትን ይቀንሳል፣ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅምን ያጠናክራል
ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ አሲዶችን ማለትም ፋቲ አሲድ፣ አስፓርቲክ አሲድ፣ ግሉታሚክ አሲድ፣ ሊኖሊክ አሲድ፣ ኦሊክ አሲድ፣ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ ያሉት በመሆኑ ደም ግፊትን ይቀንሳል፣ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅምን ያጠናክራል፣ የደም ስኳር መጠንን ይቀንሳል፣ ለአእምሮ እና የልብ ጤናን ከመጠበቅ በተጨማሪ ድባቴንና ጭንቀት አዲዮስ ያሰኛል፡፡
6.በአየርና በኬሚካል ሳቢያ የሚከሰትን የካንሰር ዓይነት ነጥሎ ይዋጋል
ፀረ-ብግነት እና ቫይታሚን ኢ ስለያዘ በአየርና በኬሚካል ሳቢያ የሚከሰትን የካንሰር ዓይነት ነጥሎ ይዋጋል፡፡ የሕዋሳትን ውድመት በመከላከሉም ያለዕድሜ ማርጀትን ይከላከላል፡፡
7. የወር አበባ አመጣጥን ያስተካክላል
ፌጦ የወር አበባ አመጣጥን ያስተካክላል፡፡ እንዲሁም ለምታጠባ እናት የጡት ወተቷን ይጨምራል፡፡
8. የፀጉር መነቀልን ይከላከላል
መጥፎ የሰውነትን ጠረን ከማስወገዱ በተጨማሪ የፀጉር መነቀልን ይከላከላል፡፡
9. የአይን ጤንና ያሻሽላል
ምን ያህል መወሰድ እንዳለበት በሳይንስ የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም የመድሐኒት ያህል በትንሹ ብቻ መጠቀም ይመከራል።
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna