የሰውነት ከመጠን በላይ ማላብ
Author: solomon
Date: 2023-04-11
የሰውነት ከመጠን በላይ ማላብ
🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
፨ላብ የሰውነት መልስ መስጠት አንዱ ሂደት ሲሆን ሰውነት ራሱ ከመጠን በላይ የሆነ ሙቀትን ለመከላከል የሚያደርገው ነው፡፡ በዚህ ወቅት የማላብ ሒደት ህይወትን የመከላከል ሂደት ይሆናል፡፡ ከዚህ ውጪ ያለውና ከመጠን በላይ የሰውነት ማላብ ሂድት የነርቭ ስርዐት ለእጢዎች በሚያደርሰው የተሳሳተ መልዕክት የማስተላለፍ ሂደት ወቅት የሚመጣ ነው፡፡ይህ በሽታ በአብዛኛው መዳፍንና የእግር ስርን እና ብብትን ያጠቃል፡፡ የዕለት ተዕለት ስራን ከማወኩም በተጨማሪ ከባድ ላብ ማህበራዊ ጭንቀት እና የመሸማቀቅ ስሜት ብሎም ራስን ማግለል ሊያስከትል ይችላል፡፡
#የሰውነት ከመጠን በላይ ማላብ ምክንያቶች
ጭንቀት
በደም ውስጥ የስኳር መጠን መቀነስ
ከመጠን በላይ መወፈር
አንዳንድ በሽታዎች እንደ ቲቢ እና ኤች አይ ቪ
የታይሮይድ ሆርሞን መጠን መጨመር
አልኮል አዘውትሮ መጠጣት
#የሰውነት ከመጠን በላይ ማላብ መፍትሄዎች
በየቀኑ መታጠብ፡ ይህን ማድረግዎ በሰዉነትዎ ላይ ያሉትን የባክቴሪያ መጠን ይቀንሳል፡፡
ሻወር ከወሰዱ በኃላ እግሮትን በደንብ ማድረቅ፡ በጣትዎት መካከል በደንብ ማድረቅ፤ፓዉደር መጠቀም ፡፡
የሚጠቀሙትን ጫማና ካልሲ መምረጥ፡ ጫማዎትንና የጫማዎትን ሶል ከቆዳ የተሰራ ቢሆን ይመረጣል፡፡
ጫማዎትን መቀያየር፡ አንድን ጫማ ከሁለት ቀን በላይ ያለማድረግ፡፡
የሚጠቀሙት ካልሲ ጥጥነት ወይም ሱፍነት ያለዉ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ከጥጥ ወይም ከሱፍ የተሰሩ ካልሲዎች እርጥበትን የመምጠጥ ባህሪይ ያላቸዉ ሲሆን እንቅስቃሴ በጣም በሚያበዙበት ወቅት ደግሞ እርጥበትን በደንብ ሊመጡ የሚችሉ የአትሌት ካልሲ የሚባሉትን መጠቀም ይመረጣል፡፡
እግሮት አየር እንዲያገኝ ማድረግ፡ በሚመቾት ሰዓት እግሮትን ከጫማ ማዉጣትና ማናፈስ፤እቤት ዉስጥ ደግሞ ባዶ እግር ወይም ነጠላ ጫማ ማድረግ፡፡
ቅባት የበዛባቸዉ ምግቦች እና አልኮል ከመዉሰድ መቆጠብ ፡
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/