ሮዝመሪ (የጥብስ ቅጠል)
🌵ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌵

፨ሮዝመሪ በደማቅ አረንጓዴ ቀለሙ፣መርፌ በሚመስል ቅጠሉ እና ለየት ባለው ማዕዛው ይታወቃል፡፡ ሮዝመሪ በመላው ዓለም ለምግብ በሚሰጠው ጥፍጥና በእጅጉ የታወቀ ቢሆንም ያዛኑ ያህል ለሕክምና አገልግሎት ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚሰጥ የቅመም አይነት ነው፡፡ ሮዝመሪ ቅጠሉ ደርቆና ተወቅጦ በየትኛውም የምግብ አይነት ውስጥ መጨመር ሲቻል እርጥቡንም እንደዚሁ በተለያዩ ምግቦች ውስጥ ጨምሮ መመገብ ይቻላል፡፡ አልፎ አልፎ የተጨመቀ ዘይቱን ማግኘት ከተቻለ ደግሞ ሌላው ወሳኝ አማራጭ ነው፡፡ በመሆኑም ሮዝመሪ በሳይንስ የተረጋገጡ ቀጥሎ ያሉትን የጤና ጠቀሜታዎችን ይሰጣል፡፡

1. የአንጎል ተግባርን ያሻሽላል፡- ጥንታዊያን ግሪኮችና ሮማውያን ሮዝመሪ የማሰብ ብቃትን እንደሚያጎለበት ደርሰውበት የነበሩ የመጀመሪያ ሕዝቦች ናቸው፡፡ የሮዝመሪ ቅጠል ወይም ዘይት ማሽተት ለነገሮች ያለንን ጥኩረት ይጨምራል እንዲሁም መረጃዎችን የማስታወስ ብቃት እንደሚያሳድግ የዘመኑ ሳይንስ ቁልጭ አድርጎ አስቀምጦታል፡፡ በዕድሜ መግፋት ለሚከሰት መጃጀትና የመርሳት ዕክል መፍትሄ ሰጭ እንደሆነ ተመስክሮለታል፡፡

2. የፀጉር ዕድገትን ያፋጥናል፡- ሮዝመሪ ዘይት በውስጡ በያዘው ኬሚካላዊ ንጥረ ነገር የፀጉር መርገፍና መነቀል እንዲሁም ያለ ጊዜው የሚከሰት ራሰ በረሃነትን ይዋጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የራስ ማሳከክና ይከላከላል፡፡

3. ስቃይ ወይም ሕመምን ይቀንሳል፡- በባህላዊ ሕክምና ውስጥ ሮዝመሪ መለስተኛ ሕመምን በማስታገስ ረገድ የታወቀ ነው፡፡ አኩፓንቸር ለተሰኘ ባህላዊ የደረቅ መርፌ ሕክምናም ሆነ ለሌሎች ተመሳሳይ ሕመሞች ሮዝመሪ ዘይት በተወጋው መርፌ ላይ ማፍሰስ ወይም መቃባት ስቃይን ይቀንሳል፡፡ ሳይንስ እንዳረጋገጠው የሮዝመሪ ዘይት ሕመምን በተሰማን ቦታ ላይ መቀባት ዘማናዊ ከሆነው አሲታሚንኦፊን ከተሰኘ መድኃኒት የተሻለ እንደሆነ አረጋግጧል፡፡

4. ደም መጣጭ ነፍሳትን ይመክታል፡- ሮዝመሪ ዘይት ቤት ውስጥ ብንረጭ ደም መጣጭ የሆኑ አደገኛ ባክቴሪያና ቫይረስ የሚያሰራጩ የወባ ትንኝ፣ትኋን፣ቅማል፣መዥገር የመሳሰሉ ሌሎች ነፍሳትን ያባርራል፡፡ በነገራችን ላይ ዘመናዊ የተባይና ነፍሳት መርጫ ኬሚካሎች በተወሰነ መልኩ የሮዝመሪ ዘይት የተካተተባቸው ነው፡፡

5. ጭንቀት ያባርራል፡- ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ተማሪዎች ከፈተና በፊት የሮዝመሪ ዘይት ወይም ቅጠል ደጋግመው ቢያሸቱ ኮርትሶል የተሰኘ አደገኛ የሰውነታችንን ሆርሞን በመቀነስ ውጥረትና ጭንቀታቸውን ትርጉም ባለው ደረጃ ይቀንስላቸዋል፡፡

6. የደም ዝውውር ይጨምራል፡- የእግርና የእጅ ጣቶቻቸው የሚቀዘቅዝባቸው ሰዎች በሮዝመሪ ዘይት ወይም ቅጠል ቢያሹት ከችግራቸው እንደሚላቀቁ ሳይንስ አረጋግጧል፡፡

7. የአጥንት መገጣጠሚያ መቆጣትን ይቀንሳል፡- ሮዝመሪ ዘይት የአጥንት መገጣጠሚያዎች በመቀባት የአጥንት ብግነትና የአጥንት መገጣጠሚያ ሕመም ይቀንሳል፡፡

8. ካንሰር፣የምግብ መመረዝ፣የጉበትና የስርዓተ ልመትን ጤና በመጠበቅ ረገድ ሮዝመሪ ከፍተኛ አስተዋፆ አለው፡፡

እናመሰግናለን
           መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna