የቃሪያ ጥቅሞች
🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀

1. ጉንፋን ወይም ሳይነስ ይከላለላ፡- በተለምዶ ጉንፋን የያዘውን ሰው ቃሪያ ብላ ወይም የሚያቃጥል ነገር ብላ ይባላል፡፡ይሄ ነገር ሳይንስም ይደግፈዋል፡፡ ቃሪያ ውስጥ ያለው ካፕሲን አፍንጫችን ውስጥ ያለውን ሚውከስ ሜምብሬን ያነቃቃዋል፡፡አፍንጫችን ውስጥ ያለው የደም ዝውውር በማፋጠን ከአፍንጫችን የሚወጣው ፈሳሽ አንዲቀጥን ያደርገዋል፡፡ ይሄ ማለት ከጉንፋን ወይም ሳይነስ በሽታ ቶሎ እንድናገግም ይረዳናል ማለት ነው፡፡

2. የበሽታ መከላከል አቅማችንን ያሳድጋል፡- ቃሪያ በውስጡ ከያዛቸው ቫይታሚኖች ዋነኛው ቫይታሚን ሲ ነው፡፡ ቫይታሚን ሲ ሰውነታችን ራሱን ከበሽታ እንዲከላከል እና ጤነኛ ሆነን እንድንቆይ ይረዳናል፡፡ በተጨማሪም ቃሪያ ፀረ-ባክቴሪያ የመሆን ባህሪ አለው፡፡ በዚህ ምክንያት በሰውነታችን ውስጥ በተለያየ ምክንያት የተፈጠሩ ፍሪ ራዲካል የሚባሉትን ጎጂ ነገሮችን ያፀዳል፡፡

3. ቃሪያ መብላት ያነቃቃል፡- ቃሪያ ውስጥ ያለው ካፕሲን የተባለው ንጥረ ነገር ሰውነታቸን ኢንዶርፊን የተባለውን ሆርሞን እንዲያመነጭ ያደርገዋል፡፡ ይሄ ሆርሞን ጥሩ ስሜት እንዲሰማን እና ደስተኛ እንድንሆን ያደርገናል፡፡

4. እይታችንን ያስተካክላል፡- ቃሪያ ቫይታሚን ኤ እና ሲ በውስጡ ይዟል፡፡ እነዚህ

ቫይታሚኖች የአይናችን ጤና ይጠብቃሉ በተጨማሪም እንደ ሞራ ያሉ የአይን ችግሮችን ይከላከሉልናል፡፡

5. ቃሪያ ለፀጉራችን እና ለጤናችን ይጠቅማል፡- ቃሪያ መብላት ቆዳችንን ጤነኛ እና ጥሩ ወዘና ያለው እንዲሆን ይረዳል፡፡ ቫይታሚን ሲ የተጎዱ የቆዳችን ሴሎች እንዲጠገኑ እና የቆዳችን መሸብሸብ እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ በተጨማሪም ቃሪያ በሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠረውን መቆጣት እና እብጠቶች ስለሚቀንስ ብጉርን ይከላከላል፡፡

6. ቃሪያ አንታይ ኢንፍላማቶሪ ነው፡- ሰውነታችን ውስጥ ከውስጥም ሆነ ከውጭ እብጠት ወይም መቅላት ወይም መቆጣት ይከሳታል፡፡ ይሄ ኢንፍላሜሽን ይባላል፡፡ ቃሪያ በቫይታሚን ሲ የበለፀገ ስለሆነ ይሄ ችግር እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡ ከተከሰተም ቶሎ እንዲድን ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡

7. ቁስል ቶሎ ያሽራል፡- ቃርያ ውስጥ ያለው ቫይታሚን ሲ በቆዳችን ላይ የሚፈጠሩ ቁስሎችን ቶሎ እንዲድኑ ያደርጋል፡፡ቫይታሚን ሲ ቆዳችን የሚሰራበትን ኮላጅን ቶሎ እንዲመረት ያደርጋል ስለዚህም ቁስሉ ቶሎ እና ጠባሳው ሳይበዛ እንዲድን ያደርገዋል፡፡

8. ቃሪያ ለልብ ይጠቅማል፡- ቃሪያ ካፕሲን ስላለው ለልባችን ጤና የተለያዩ ጥቅሞች ይሰጣል፡፡ በደማችን ውስጥ ያለውን የኮሌስትሮል መጠን ያስተካክላል፡፡በደም ቧንቧችን ውስጥ የተጠራቀመውን ኮሌስትሮል ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የደም እንቅስቃሴ ያሻሽላል ይሄም በልባችን ላይ ያለውን ጫና ይቀንሳል፡፡

9. ቃሪያ በውስጡ ብዙ ካልሲየም ይዟል፡- ቃሪያ በውስጡ ብዙ ካልሲየም እና ቫይታሚን ኬ ስላለው ለአጥንታችን እና ለጥርሳችን ጤና ይጠቅማል፡፡በአደጋ ጊዜ የሚደርሰውን የደም መፍሰስም ይቀንሳል፡፡

እናመሰግናለን
           መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna