የጨጓራ ባክቴሪያ

፨ የጨጓራ ባክቴሪያ ወይም ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ ወደ ሰውነታችን በመግባት የምግብ ትቦ ላይ እና ጨጓራ ውስጥ መኖር የሚችል ነው፡፡ ይህ ባክቴሪያ ሳይታከም ከቆየ አልሰር/ ቁስለት በጨጓራ ላይ እና በትንሹ አንጀት የላይኛው ክፍል ላይ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ አለፈፍ ሲልም ካንሰርንም ሊያስከትል ይችላል፡፡

🌵 በጨጓራ ባክቴሪያ መያዝ በብዙዎች ላይ የሚያጋጥም የተለመደ በሽታ ቢሆንም ባክቴሪያው አንዳንድ ሰዎች ላይ ምንም ምልክት የማያሳይ፣ የቁስለት ሁኔታም የማይፈጥር ቢሆንም ብዙዎችን ግን ለከፍተኛ ለሕመም ይዳርጋል፡፡

ባክቴሪው እንዴት ህመም ይፈጥራል?

🌵 የጨጓራ ባክቴሪያ ወደ ሰውነት ከገባ በኋላ በጨጓራ ውስጣዊ አካል ላይ ጥቃት በመፈፀም ጨጓራችንን ተጋላጭ ያደርገዋል፤ ምክንያቱም ጨጓራችን ምግብ ለመፍጨት አሲድ ይጠቀማል፡፡ ይህ አሲድ በጨጓራ አካል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሚያደርገው የጨጓራ ውስጣዊ አካል ነው፡፡ ይህ አካል ከተሸረሸረ ጨጓራችን ለአሲዱ የተጋለጠ ስለሚሆን ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ጉዳቱ የደም መፍሰስ ጨምሮ አካሉ እንዲቆስል፣ እንዲሁም የበላነው ምግብ እንዳይፈጭና እንዳይረጋ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ይህ ባክቴሪያ ከየት ሊያገኘን ይችላል?

🌵 የጨጓራ ባክቴሪያ ከምንበላው ምግብ፣ ከምንጠጣው ውኃና ከምንጠቀማቸው በባክቴሪው ከተበከሉ ቁሶች ሊያገኘን ይችላል፡፡ በሽታው አብዛኛውን ጊዜ ፅዳት በሚጎድልባቸው አካባቢዎች የሚከሰት ሲሆን ባክቴሪያው በምራቅ ንክኪና ባክቴሪያው ካለበት ሰው ጋር በሚኖር የፈሳሽ ንክኪ ሊተላለፍብን ይችላል፡፡

የጨጓራ ባክቴሪያ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

» የሆድ መነፋት፤
» ግሳት፤
» የረሃብ ስሜት አለመሰማት፤
» ማቅለሽለሽ፤
» ማስመለስ፤
» ቁስለት ከተፈጠረብን በሆዳችን የላይኛው ክፍል የማቃጠልና የመደንዘዝ ስሜት፤
» ያለምክንያት ክብደት መቀነስ ሊታዩ ይችላሉ፡፡

መቼ ወደ ህክምና መሄድ ይኖርብናል?

» የሰገራ መጥቆርና ደም መቀላቀል ካለ፣
» ለመተንፈስ መቸገር ካጋጠመን፣
» ያለስራ የመልፈስፈስና የድካም ስሜት ከተጫነን፣
» የቆዳ መገርጣትና ራስን የመሳት ሁኔታ ከታየብን፣
» የተፈጨ ቡና የመሰለ ነገር የሚያስመልሰን ከሆነ፣
» ከባድ የሆድ ህመም ካለን የጨጓራ ባክቴሪያ ሊሆን ስለሚችል መታየት አለብን፡

ሕክምና
     
🌵 ጸረ - በክቴሪያ መድኃኒቶች
🌵 በጨጓራ ውስጥ አሲድ የሚረጩትን ጥቃቅን ቧንቧዎች በመዝጋት አሲድ የሚቀንሱ መድኃኒቶችን መውሰድ እና
🌵 የአመጋገብ ስርአት ማስተካከለል ይካተቱበታል፡፡

እናመሰግናለን
           መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna