የኪያር ውሃ በመጠጣት የሚገኟቸውጥቅሞች
Author: admin
Date: 2023-02-28
የኪያር ውሃ በመጠጣት የሚገኟቸውጥቅሞች
🌵ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌵
በቀን ውስጥ ለጤናችን ቢያንስ ከ6 እስከ 8 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት የግድ እንዳለበን የመስኩ ባለሙያዎች አበክረው ይመክራሉ፡፡ ታዲያ በዶ ውሃ ከጉሮሮአችን አልወርድ ለሚለን 8 ብርጭቆ ውሃ፣2 ፍሬ መካከለኛ ኪያር በቀጫጭኑ ከትፈን ግማሽ ማንኪያ ጨው አድርገንበት ሰፋ ባለ ውሃ ማቅረቢያ አንድ ላይ ካዋሀድን በኃላ ከድነነው ለ4 ሰዓት ወይም ለሊቱን ሙሉ በፍሪጅ ውስጥ በማቀዝቀዝ አውጥተን መጠጣት እንችላለን፡፡ አንዴ የሰሩት ከ3 ቀን በላይ መቆየት የለበትም፡፡ ይህን ሲያደርጉ ባዶ ውሃ አልጠጣ ብሎት ያስቸገሮት የመጠጥ ፍላጎቶ በኪያር የውሃ ቃና በርከት ያለ ውሃ እንዲጠጡ ዕድል ሲፈጥርሎት በተጨማሪ የኪያር ውሃ በመጠጣቶ ተከታዮቹን የጤና በረከቶች ያገኛሉ፡፡
1. ክብደት የመቀነስ ውጥን ካሎት የኪያር ውሃን መጠጣት ግንባር ቀደም እንዲደርጉ እንመክራለን፡፡ ምክንያቱም ካሉ ኪያር ከፍተኛ ፋይበር እና አነስተኛ ካሎሪ እንዲሁም ብዙ ውሃ በውስጡ ይዟል፡፡ በሰውነቶ ያለውን የካሎሪ መጠን ይቀንሳል፡፡ የረሀብ እና የመጠማት ስሜት በማጥፋት ተጨማሪ ምግቦች እንዳይመገቡት ይገታዎታል፡፡
2. ኪያር ውሃ በሰውነቶ ውስጥ ያሉ መርዛማ ኬሚካሎችን በመሰባባር የሴል ውድመትን ያዘገያል ብሎም ይከላከላል፡፡ በተጨማሪም ለስኳር፣ ለልብ እና ለመርሳት በሽታ እንዳይጋለጡ ይረዳዎታል፡፡ እንዲሁም የአይን ሕመምን ይከላከላል፡፡
3. የኪያር ውሃ መጠጣት ካንሰርን ይከላከላል፡፡ የኪያር ውሃ ሊግናንስ የተሰኘ ንጥረ ነገር አለው፡፡ ይህ ንጥረ ነገር ካንሰርን ይከላከላል፡፡ በተጨማሪ ፍላቮኖይድ ፊስቲን የተሰኘው ጥረ ነገር ወንዶችን በስፋት የሚያጠቃውን የወንድ የዘር ፍሬ (ፕሮስቴት) ካንሰር ዕድገትን ያዘገያል፡፡
4. የኪያር ውሃ መጠጣት የደም ግፊት መጠንን ይቀንሳል፡፡ ከፍተኛ የደም ግፊት ብዙ ጨው ሶደየም በሰውነታች ውስጥ ሲኖር ነው፡፡ ጨው ብዙ ውሃ ስለሚያስጠጣን የፈሳሽ መጠን በሰውነት ውስጥ ከልክ በላይ በዝቶ የደም ግፊትን ይጨምራል፡፡ የኪያር ውሃ ውስጥ ያለው ከፍተኛ ፖታስየም ይሄን የደም ግፊት በመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፆ አለው፡፡
5. የኪያር ውሃ መጠጣት ጤናማ ቆዳ እንዲኖሮት ያደርጋል፡፡ የኪያር ውሃ ቆዳዎትን ከድርቀትና ከመሰነጣጠቅ ይጠብቃል፡፡ በተለይ በውስጡ የያዘው ቫይታሚን ቢ5 ብጉርን ለማከም ይረዳል፡፡
6. የኪያር ውሃ የአጥንቶን ጤና ይጠብቃል፡፡ በውሰጡ የያዘው ቫይታሚን ኬ የአጥንቶን ጤና ከመጠበቅ ባሻገር ደሞ በአግባቡ እንዲረጋ ያደርጋል፡፡
7. የኪያር ውሃ መጠጣት ለጡንቻ ጥንካሬ ይረዳል፡፡ሴሊካ በኪያር ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ሲሆን ለጡንቻ እድገትና ጥንካሬ ወሳኝ ነው፡፡
8. የኪያር ውሃ መጠጣት ሰውነቶ ከመርዛማ ነገሮች ያፀዳል (Detoxifying) ያደርጋል፡፡ የኪያር ውሃ ሲጠጡ ብዙ ውሃ ስለሚጠጡ ሰውነቶ ውስጥ ያሉ መርዛማ ኬሚካሎችን ሰባብሮ ያስወግዳል፡፡
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna