ስቅታ ምንድን ነው እንዴት ልንከላከለው እንችላለን
Author: admin
Date: 2023-02-27
ስቅታ ምንድን ነው እንዴት ልንከላከለው እንችላለን
🌵ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌵
፨ስርቅታ ድንገተኛ ያለውዴታ ወይም ሳያዙት ከቁጥጥር ውጪ የዲያፍራም ጡንቻዎች መጨማደድ ወይም መሰብሰብ ሲሆን፤ የእነዚህ ጡንቻዎች መሰብሰብ የድምጽ አውታሮችን በመዝጋት ስቅታ እንዲፈጠር ያደርጋል።
፨ዲያፍራም (በሆድ እና ሳንባ መካከል የሚገኝ ጡንቻ) ተጨማዶ ስቅታ እንዲፈጠር ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል:-
»ሆዳችን በምግብ ሲወጠር ወይም ሲለጠጥ
»አልኮል
» አየር
» የጨጓራ የሙቀት መጠን ሲቀየር
» አልኮል ወይም ሲጋራ በብዛት ስንጠቀም ይፈጠራል ማለት ነው።
በተጨማሪም ስንጨነቅ ወይም በጣም
ሲደክመን ይከሰታል። በአብዛኛው ስቅታ ከጀመረን በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚቆም ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ለቀናቶችና ሳምንታቶች ሊቆይ ይችላል።
ይህ ያልተለመደ ሲሆን ሌሎች በሽታዎች እንዳሉብን አመላካች ነው። ከእነዚህ በሽታዎች መካከል:-
» በዲያፍራም አካባቢ በመርፌ ወይም በስለት ነገሮች መወጋት
» የአንጀት መውረድ
» ከጉሮሮ እስከ አንጀት ባሉ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከፍተኛ ህመም መኖር እና
» በደረት ነርቮች መቆጣት ምክንያት የሚፈጠሩ እጢዎች ናቸው።
ከአንድ ወር በላይ የሚቆይ ስቅታ በህክምና የማይድን ስለሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልዋል።
፨መከላከያ መንገዶች
ወደ ህክምና መስጫ ተቋም መሄድ የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ካሉ ከታች ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዱን ቀላል መንገድ መጠቀም ተገቢ ነው:-
🍀በወረቀት ቦርሳ ወይም በካኪ ፖስታ ውስጥ መተንፈስ
🍀ከአፍዎ በተቃራኒ ካለው የብርጭቆ ጠርዝ ላይ ለመጠጣት መሞከር
🍀 ትንፋሽዎን ቆጥበው ወይም ውጠው ሳይተነፍሱ ለትንሽ ጊዜ መቆየት
🍀 ሎሚ መምጠጥ
🍀 ስኳር መቃም
🍀 ጆሮዎን በጣትዎ ደፍነው በስትሮ (Straw) ውሃ መጠጣት
የፀጉርዎን ጫፍ ይዘው ለ1 ወይም 2 ደቂቃ ወደላይ መሳብ (መጎተት)
🍀 በውሃ በተነከረ ጥጥ ላንቃችንን ማሸት ወይም መጥረግ
🍀ምላስዎን በእጅዎ ይዘው ወደ ውጭ ቀጥ አድርገዉ መሳብ ወይም መጎተት ናቸው።
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna