ደም የቀላቀለ ሰገራ
🌴ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌴

፨ደም የቀላቀለ ሰግራ ማለት በየትኛውም የአንጀት ክፍል መድማት ሲያጋጥም በሰገራ መልኩ ደም ሲታይ ነው። ከተቀመጡ በኋላ ሰገራው ላይ እና የሽንት ቤት ወረቀት ላይ ደም ሲታይ ደም ሰገራ ላይ እንዳለ ይታወቃል ።

ምክንያቶቹ

🌿 የአንጀት ክፍል ላይ የወጣ ቀዳዳ መሰል ነገር
🌿 የፊንጢጣ ኪንታሮት
🌿 የፊንጢጣ መሰንጠቅ
🌿የአንጀት መለብለብ
🌿 የአንጀት አካባቢ ደም ስሮች ላይ ችግር ሲኖር
🌿የጨጓራ ቁስለት
🌿 አንጀት ላይ ትርፍ ስጋ መሰል ነገር ሲያድግ
🌿 አንጀት ካንሰር
🌿 የምግብ ትቦ ላይ ችግር ካለ
🌿 የአንጀት ላይ ኢንፌክሽን

ምልክቶቹ
፨አብዛኛው ሰው ምልክቶቹን ላያስተውል ይችላል ።በሌላ በኩል ደግሞ ከሚከሰቱ ምልክቶች ውስጥ
🌿የሆድ ህመም
🌿ማስመለስ
🌿ድካም
🌿ለመተንፈስ መቸገር
🌿ተቅማጥ
🌿ራስን መሳት
🌿የሰውነት ክብደት መቀነስ የማሳሰሉት ናቸው።

ህክምናው
»ያመጣውን ነገር በምርመራ ከተረጋግጥ ወይም ከታወቀ በኋላ መንሰኤውን ማከም

»በህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡ መድሀኒቶችን በአግባቡ መውሰድ

»በፋይብር የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ፣ ሙቅ ውሀ ላይ መዘፍዘፍ(የፊንጢጣ ኪንታሮት፣የፊንጢጣ መሰንጠቅ ከሆነ ያመጣው)
እንደማጠቃለያ ደም የቀላቀለ ሰገራ በትንሽ (በቀላል) እንዲሆም ከበድ ባሉ ምክንያቶች በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ የሚከሰት እና ምልክቶቹ ቶሎ የማይስተዋሉ ሰለሆነ እንዳወቁ የጤና ባለሙያ ያማክሩ።

እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna