ለመጥፎ አፍ ጠረን የቤት ውስጥ መፍትሄዎች
Author: admin
Date: 2023-02-24
ለመጥፎ አፍ ጠረን የቤት ውስጥ መፍትሄዎች
🌵 ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌵
፨በተለምዶ መጥፎ የአፍ ጠረን ይምንለው ብሽታ ሃሊቶሲስ በመባል ይታወቃል። በሰዎች መሃል መሸማቅቀን የሚያስከትል ሲሆን በራስ መተማመናችን ላይ ጉዳት አለው። መጥፎ ሽታ ብዙ መንስኤዎች አሉት። ጠረን ያላቸው ምግቦች መመገብ፣ ማጨስ፣ የአፍ መድረቅ፣ የድድ በሽታ፣ የሳይነስ በሽታ እና ሌሎች በሽታዎች የአፍ ጠረን ሊያመጡ ይችላሉ።
፨ዋናው የመጥፎ አፍ ጠረን መነሻ አፋችን ጀርባ ወይም በጥርሶቻችን መሃል የሚገኝ የባክቴሪያ ክምችት ነው። ሽታን ለመከላከል የአፍ ጤንነትን መጠበቅ ይኖርብናል። ጥርስን በየግዜው መቦረሽ ያስፈልጋል።
በቀን ውስጥ በቂ ውሃ መጠጣት ሌላኛው መፍትሄ ሲሆን ምግብ ከተመገቡ በኋላ አፋችንን መጉመጥመጥ በጥርሳችን መሃል ያሉ የምግብ ፓርቲክሎችን ለማስወገድ ይረዳል። ሌሎች ለአፍ ጠረን ልናውላቸው የምንችላቸው የቤት ውስጥ መፍትሄዎች ይከተላሉ።
ቀረፋ
🌿ቀረፋ በውስጡ ሲናሚክ አልዲሃይድ አሲድ የያዘ ሲሆን ይህ ዘይት መጥፎ ሽታን ከመሸፈን አልፎ አፋችን ውስጥ ያለውን የባክቴሪያ መጠን በመቀነስ ይታወቃል። መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመቀነስ እንደሚከተለው ማድረግ ይችላሉ፦
» አንድ የሻይ ማንኪያ የቀረፋ ዱቄት አንድ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ አድርገው ያፍሉ
ውሃውን አጥልለው ይጉመጥመጡበት
የፓርስሊ ቅጠል
🌿ፓርስሊ ውስጥ ያለው ክሎሮፊል መጥፎ የአፍ ሽታን ለመቀነስ ይረዳል። ፓርስሊ ቅጠል አቸቶ ውስጥ ነክረው ማላመጥ እንደ ሌላ አማራጭ የፓርስሊ ቅጠሉን ፈጭተው ጁሱን ቀስ ብለው መጠጣት
የሎሚ ጭማቂ
🌿የሎሚ አሲዳማ ይዘት ጥርስዎ ውስጥ የባክቴርያ እድገት እንዲገታ ይረዳል። የሎሚ ሽታም እራሱ የአፍዎን ጠረን ለመደበቅ ይረዳል።
»ሻይ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ ውሃ ውስጥ ጨምቀው አማስለው ይጉመጥመጡበት። ጨው ጨምረውም ማጉመጥመጥ ይችላሉ። ይህ መፍትሄ የአፍዎን ድርቀት በመቀነስ በአፍ ድርቀት የሚመጣን ሽታ ለመቀነስ ይረዳል።
አፕል ሲደር ቪኔጋር
🌿 ይህ አቸቶ የፒኤች መጠን ማመጣጠን ባህሪው ለመጥፎ የአፍ ጠረን መፍትሄ እንዲሆን ያደርገዋል። ከሁለት አንዱ ምፍትሄዎች መሞከር ይችላሉ፦
»አንድ ሻይ ማንኪያ ፖም አቸቶ ከአንድ ብርጭቆ ውሃ ጋር አቀላቅለው ከምግብ በፊት ይጠጡ።
🌿 አቸቶው ጨጓራዎን ለመፍጨትም ያግዘዋል።አቸቶውን ከውሃ ጋር አቀላቅለው በጉሮሮዎ ያስረቅርቁ
የመጋገርያ እርሾ
🌿የመጋገርያ እርሾ መጥፎ ሽታ በማስወገድ ይታወቃል። መጥፎ ጠረን የሚያስከስተውን የአሲድ አለመመጣጠን በመሻሻል የአፍ ጠረናችንን ይቀንሳል። የአፍ ውስጥ ባክቴሪያ በመዋጋት መጥፎ ሽታን ያስቀራል።
»ግማሽ ሻይ ማንኪያ እርሾ አንድ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ አቀላቅለው በቀን አንዴ ይጉመጥመጡ
»ጥርስዎን በእርሾ መቦረሽ ያፍዎን አሲዲቲ ይቀንሳል። ባክቴሪያ እንዳያድግም ይከላከላል
ሻይ
🌿ኖርማልም ሆነ የቅጠላ ቅጠል ሻይ የአፍ ጠረን ለመከላከል ይጠቅማሉ። አረንጓዴ ሻይ ውስጥ ያለው አንቲኦክሲዳንት ፖሊፌኖልስ ባክቴርያ አፋችን ውስጥ እናዳይድግ ይከላከላል።
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna