የአረንጓዴ ሻይ የጤና ጥቅሞች
🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳም🍀

🌵አረንጓዴ ሻይ ለመድሀኒትነት ለሺህ አመታት ሲጠቀሙበት ኑረዋል፣ መነሻው ከቻይና ቢሆንም በመላው ኤስያ በስፋት ጥቅም ላይ ውሏል፣ የአረንጓዴ ሻይ ከጥቁር ሻይ አንጻር ይበልጥ የጤና ጥቅሞች ያሉት በምርት ሂደቱ ምክንያት ነው:: የጥቁር ሻይ አመራረት በማብላላት መልኩ ሲሆን የአረንጓዴ ሻይ አመራረት ደግሞ የማብላላት ሂደትን በማስወገድ ነው:: በዚህም ምክንያት፣ አረንጓዴ ሻይ ከፍተኛ የሆነ የአንቲ ኦክሲዳንት እና ፖሊ_ፌኖልስ መጠን አሉት እነዚህም ነገሮች አረንጓዴ ሻይ ብዙ ጥቅሞች እንዲኖሩት ምክንያት ናቸው::

1🍀ክብደት ለመቀነስ: -
አረንጓዴ ሻይ ሜታቦሊዝምን ይጨምራል:: በአረንጓዴ ሻይ የሚገኘው ፖሊፌኖል የስብ ኦክሲዴሽንን የሚያጧጡፍ ስራ የሚሰራና ሰውነታችን ምግብን ወደ ካሎሪ የመቀየሩን ተግባር የሚያለሳልስ ነው::

2🍀 ለስኳር
ምግብ ከተመገብን በኋላ በደማችን ውስጥ የሚጨምረውን የግልኮስ መጠን፤ አረንጓዴ ሻይ ፍጥነቱ እንዲገታ ለማድረግ ይረዳል:: ይህም የከፍተኛ ኢንሱሊን ጡዘትንና የስብ ክምችት ማስከተሉን የሚከላከል ነው::

3🍀ለልብ በሽታ
ሳይንቲስቶች እንደሚያስቡት፣ አረንጓዴ ሻይ በደም ቧንቧ የላይኛው ገጻቸው ያት ነው::

4🍀የጉሮሮ ካንሰር
በጉሮሮ ካንሰር የመያዝ አደጋን የሚቀንስ ነው፣ ግን በስፋት እንደሚታወቀው የካንሰር ሴሎችን መግደል የሚችል እና በዙሪያው በሚገኙት ጤነኛ የሆኑ ቲሹዎች ላይ ጉዳት የማያደርስ ነው::

5🍀ኮሌስትሮል
አረንጓዴ ሻይ በደም ውስጥ ያለን መጥፎ ኮሌስትሮል የሚቀንስና የጥሩውን ኮሌስትሮል ከመጥፎው ኮሌስትሮል የተሻለ የሚያመዛዝን ነው::

6🍀አልዛይር እና ፓርኪንሰን
በአልዛይመር እና በፓርኪንሰን የሚመጡትን ችግሮች የሚያዘገይ እንደሆነ ይነገራል:: ጥናት እንደሚያሳየው አረንጓዴ ሻይ የአዕምሮ ሴሎችን ከመሞት የሚያድንና የተጎዱ የአዕምሮ ሴሎችን የሚጠግን ነው::

7🍀የጥርስ መበስበስ
ጥናቶች እንደሚያመልክቱት በሻይ የሚገኘው “ካቴቺን” የተባለው አንቲኦክሲደንት ኬሚካል የጉሮሮ መመርቀዝ፣ የጥርስ መበስበስ እና ሌሎች የጥርስ ችግሮችን የሚያስከትሉትን ባክቴሪያና ቫይረሶች የሚያወድም ነው፡፡

8🍀የደም ግፊት
አረንጓዴ ሻይን አዘውትሮ መጠቀም የደም ግፊት አደጋን እንደሚቀንስ ይታመናል::

9🍀ድብርት
ቲያኒን በሻይ ቅጠሎች በተፈጥሮ የሚገኝ አሚኖ አሲድ ነው:: ይህ ንጥረ ነገር የሚያዝናና እንዲሁም የሚያረጋጋ ተጽዕኖ ያለው ሲሆን ለሻይ ጠጪወችም ላቅ ያለ ጥቅም ይሰጣል::

10🍀ፀረ-ቫይረስ እና ፀረ-ባክቴሪያል
ጠንካራ ፀረባክቴሪያል እና ፀረቫይረስ ባህርይ ያለው ሲሆን ከኢንፍሉየንዛ እስከ ካንሰር ያሉ በሽታወችን በማከም ውጤታማ ናቸው:: በአንዳንድ ጥናቶችም አረንጓዴ ሻይ የአብዛኞቹን የበሽታወች ስርጭት መግታት እንደሚችል ያመላክታል::

11🍀ለቆዳ ውበት
አረንጓዴ ሻይ የቆዳ መጨማደድንና የማርጀት ምልክትን ለመቀነስ የሚረዳ ነው፣ ለዚህ ምክንያትም ያላቸው ፀረ-ኦክሲደንት እና ፀረ-መመረዝ ተግባር ነው:: በእንስሳት ሆነ በሰው ላይ የተደረጉት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አረንጓዴ ሻይ በጸሀይ የሚመጣ ጉዳትን የሚቀንስ ነው::

ምን ያህል እንጠቀም?

፨በቀን ውስጥ ከአንድ እስከ ሁለት የአረንጓዴ ሻይ ስኒ መውሰድ ይመከራል፡፡

፨ሌላው መጠቀስ ያለበት ጉዳይ በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ ካፊን እንደሚገኝ ነው፡፡ ስለዚህም ለካፊን ስሜታችሁ ስስ ከሆነ አንድ ስኒ በቂያችሁ ነው::

፨አረንጓዴ ሻይ ታኒስ(የብረትን እና የፎሊክ አሲድን ውህደት የሚቀንስ) ይገኝበታል፣ ስለዚህም ነፍሰጡር ከሆንሽ ወይም ደግሞ ለማርገዝ እቅዱ ካለሽ አረንጓዴ ሻይ ለአንቺ አይሆንም::

እናመሰግናለን
           መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna