የወይባ ጢስ ጥቅሞች
Author: admin
Date: 2023-02-21
የወይባ ጢስ ጥቅሞች
🌵ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌵
፨የወይባ ጢስ ጥሩ ገፅታና መልካም ጠረን እንዲኖር ያስችላል ተብሎ ስለሚታመን አዘውትረው የሚታጠኑ በርካቶች ናቸው፡፡ ሰውነትን በተለይም ወገብና ማህፀንን ለማጠንከር እንደሚረዳ ይነገራል፡፡ የወር አበባ ወቅት ያለ ሕመምን ለመቀነስ፣ መሀኖች መውለድ እንዲችሉ ለማድረግም የወይባ ጢስ አገልግሎት ላይ ይውላል፡፡
ያላገባች ሴት የወይባ ጢስ የምትገባው አምራ ለመታየትና ትዳር ለማግኘትም ነው፡፡ የታጨች ሴት ደግሞ ውበቷን ለማጉላት ትጠቀምበታለች፡፡ የወለዱ እናቶች ሰውነታቸው እንዲጠነክር፣ ከወለዱ ከጥቂት ቀናት በኋላ ጢስ ይገባሉ፡፡ አግብታ የፈታች ሴት ጢስ ስትገባ በትግርኛ ‹‹ዕጣን ግብኣ›› እየተባለ ይነገርላታል፡፡ ቀትር ላይ ፀሐዩ ሰውነት እንደሚጐዳ ስለሚታመን የወይባ ጢስ መታጠን የሚካሔደው ምሽት አካባቢ ነው፡፡ ከታጠኑ በኋላ ሰውነታቸው እንዲቀዘቅዝ ለጥቂት ደቂቃዎች ከቤት አይወጡም፡፡
የታጨች ሴት አንዴ ታጥና ትወጣለች፡፡ የወለደች ሴት ግን እየገባችና እየወጣች ትታጠናለች፡፡ ቅቤ አናቷ ላይ ይደረግላታል፡፡ ገንፎና ወተትም ይሰጣታል፡፡ ከግማሽ ሰዓት ጀምሮ ረዘም ላለ ጊዜ መታጠን ይቻላል፡፡
የሚታጠኑበት እንጨት የሚገባው ከከብት እዳሪ በሚሠራ ጐድጐድ ያለ ቦታ ነው፡፡ ከጉድጓዱ በላይ ሴቲቷ በምትታጠንበት ወቅት የምትለብሰው ሸማ የሚያርፍበት ከፍታ አለ፡፡ ሸማ ጢሱ እንዳይወጣ አፍኖ የሚይዝ ወፍራም ጨርቅ ነው፡፡ ከሸማው በላይ ደግሞ ከከብት ቆዳ የተሠራ ቁርበት ይለበሳል፡፡ አንድ ሴት ከመታጠኗ በፊት መላ ሰውነቷን ቅቤ ከተቀባች በኋላ ልብሷን አውልቃ ሸማና ቁርበት ደራርባ ጐድጐድ ባለው ቦታ ትቀመጣለች፡፡ ቅቤው ጢሱ ሰውነቷን እንዳይጐዳው ይከላከልላታል፡፡ በዕድሜ ከፍ ያሉና ልምዱ ያላቸው ሴቶች ረዘም ላለ ጊዜ ይታጠናሉ፡፡
ገጠር አካባቢ በብዙዎች መኖሪያ ቤት የወይባ ጢስ ያለ ሲሆን፣ ከተማ ውስጥ ለወለደች ሴት ብቻ የሚያዘጋጁም አሉ፡፡ በአካባቢው አንዲት ሴት በተደጋጋሚ ጢስ መግባቷ ጥንካሬዋንም ያሳያል፡፡ ወይባ ጢስ ለመገጣጠሚያ ጥንካሬ በተለይም ለማህፀን ከፍተኛ ጥቅም እንደሚሰጥ ይነገራል፡፡
ሴቶች ከጢሱ በተጨማሪ እንሶስላ ይቀባሉ፡፡ ያልታጨች ሴት እጇን ብቻ ትቀባለች፡፡ ያገባች ሴት እጇንና እግሯንም እንሶስላ ትቀባለች፡፡ በአካባቢው ሰዎች የሚተጫጩት በተለያየ ጊዜ ቢሆንም፣ በአዲስ ዓመትና በጥምቀት በዓል ያመዝናል፡፡ ወንዶች የሴቶች ፀጉር ላይ ሣር በመሰካት ወይም ሎሚ በመወርወር ፍላጐታቸውን ካሳዩ በኋላ ሽማግሌ ይልካሉ፡፡
የወይባ ጢስ አገልግሎትን በዘመናዊ መንገድ በማዘጋጀት የሚሠሩ ተቋሞች እየተበራከቱ ነው፡፡ ወይባ ጢስን ስቲምና ሳውናን ከመሰሉ በጢስ ኃይል ለውበትና ለጤና እንክብካቤ የሚውሉ መንገዶች ጋር የሚያነጻጽሩም አሉ፡፡
ስለቱሪስት መስህቦች የሚያትቱ ድረ ገጾችም የወይባ ጢስን እንደ አንድ መስህብም ያስቀምጣሉ፡፡ ከእነዚህ አንዱ ኢትዮጵያ ቱሪዝም ቲፕስ ዶት ኮም፣ በተለያዩ አካባቢዎች በባህላዊ መንገድ የሚካሔዱ መዋቢያዎች በሚል ከሚያስቀምጣቸው መካከል የወይባ ጢስና ቆቆባ ጡሽ (ጢስ) ይገኙበታል፡፡
ከወይባ ጢስ ጋር አያይዘው ብዙዎች የሚጠቅሷቸው ሳውናና ስቲም ከኢትዮጵያ ውጭም ዓመታትን አስቆጥረዋል፡፡ ከውበት በተጨማሪ ሰውነትን ለማፍታታትና ለደም ዝውውር፣ ፍቱን መድኃኒት እንደሆኑም ይነገራል፡፡
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna