የጨው ጥቅም እና  ጉዳቶች
🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
 
፨ጨው  ለማንኛውም የምግብ ዓይነቶች  የማጣፈጫ  ቅመም ነው ።ጨው  ምግብን   በማጣፈጥ  ረገድ   ከሁሉም ቅመሞች  በተለየ መልኩ ትልቁን  ድርሻ  ይወስዳል።
ጨው በመጽሐፍ ቅዱስ ሳይቀር  ይታወቃል ።
ጨው  በግዕዙ  ፄው ይባላል።በእንግሊዘኛው (salt) በመባል ይጠራል።ጨው ከምግብ ማጣፈጫነቱ በተጨማሪ ብዙ የጤና ጥቅሞችም አሉት ጨው  ወይም በግዕዙ  ፄው ከሚሰጣቸው የጤና ጥቅሞች መካከል፦

🌵የምግብ ጨው ፦መድኃኒትነቱ  ሲተነተን

                    1ኛ

የጥርስ ህመም በሽታን ይፈውሳል።ለተቦረቦረ ጥርስና ለሚነቃነቅ ለሚሸራረፍና  ለሚነቃቀል ከባድ የህመም ስሜትና ጥዝጣዜ ላለው  የጥርስ በሽታ  ፍቱን የሆነ  መፍትሔ ይሰጣል።

          አጠቃቀም

ጥሬ ጨውን  ከቁንዶ በርበሬ ጋር ጨውን  አነስ ቁንዶ በርበሬውን በዛ አድርጎበአንድነት መውቀጥ/መፍጨት ከተፈጨ በኋላ  በሻይ ማንኪያ  አንድ 4ኛ የሚሆነውን ዱቄት ቀንሶ ባዲስ ጨርቅ ወይም  ፋሻ ቋጥሮ በታመመው ጥርስ በኩል ከ5-10 ደቂቃ ነክሶ  መያዝ  የህመሙ ስሜት ብዙም ሳይቆይ ይጠፋል በውስጡ ትልም ካለ መዞ ያወጣዋል።በቀን 2ት ጊዜ ለ3 ቀን ያህል ከተጠቀሙ  በቂ ነው።

     ሁለተኛ አጠቃቀም 
፨ጥሬ ጨውን  ከቀይ ሽንኩርት ጋር በአንድነት  ፈጭቶ  በእሳት ሞቅ  አርጎ  በፋሻ ወይም በስስ ነጠላ ትኩሱን ቋጥሮ በታመመው  ጥርስ በኩል ነክሶ   መያዝ ነው።ምራቅ ከመጣ ወደውጭ መትፋት ይቻላል::ለሁለት ቀን በቀን ሁለት ጊዜ ከተደረገ   በቂ ነው።

🌵ጉዳቶቹ ደግሞ

የምግብ ጨው  የሚያስከትላቸው ጉዳቶች
ጨውን በምግባችን ውስጥ  አብዝተን
የምንጠቀም ከሆነ እነዚህ ችግሮች
ያጋጥሙናል ።

🍀የሰውነት መነፋትና ዕብጠት
🍀ተደጋጋሚ የሆነ የራስ ምትሐት
🍀የውሃ ጥምና የሺንት መብዛት
🍀ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት
🍀 የኩላሊት ዙሪያ ህመም
🍀 የማስታዎስና ትኩረት የማጣት ችግር ያመጣል።

፨ጨውን ከጤና አንጻር በሁለት  መልኩ  ከፍለን
የምግብና የገላ ጨው በማለት ዕናየዋለን።

🍀 የገላ ጨውየሚሰጣቸውን  ጥቅምች
 
1ኛ የማህፀንን ጤንነት ይጠብቃል፡፡ለተለያዩ  ኢንፌክሽኖች ለማያቋርጥ የማህፀን ፈሳሽና ለቆዳ የማሳከክ ችግርም ይሆናል።

2ኛ በሽታን የመከላከል  ወይም የመቋቋም  አቅማችንን ይጨምራል።

3ኛ ለቆዳ ውበት ይሆናል።እጅግ የተዋበና አንጸባራቂ የሆነ የቆዳ ዓይነት  ዕንዲኖረን  ያረጋል።

4ኛ ጉልበት ወይም (Energy)ይሰጣል።
ሰውነታችን  እንዲነቃቃና  ጥሩ ዕንቅልፍ
ዕንዲኖረን  ያደርጋል።በተይ ደግሞ ለመገጣጠሚያ ህመም ለጉልበት  ፤ለቁርጭምጪሚት  የወገብ ህመም ላለባቸው  ሰዎች መፍትሔ  ይሠጣል።

            አጠቃቀም

ከ3--4 የሾርባ ማንኪያ  የገላ ጨው ለብ ያለ ውሃ ላይ በመጨመር ጨው ከሟሟ በኋላ
ፊታችንንና የራስ ፀጉራችንን ዕንዳይነካን በመጠንቀቅ በትልቅ   የውሃ ገንዳ ላይ
ከ10--15 ደቂቃ መዘፍዘፍ ነው።ሰንዘፈዘፍ  ቢበዛ ቢበዛ ከ20 ደቂቃ ማለፍ የለበትም።

       ማስጠንቀቂያ

፨ምን አልባት  የተዘፈዘፍንበት የጨው ውሃ
ተስቶ ፊታችን /ጸጉራችን  ቢረጨን  በሌላ
ንጹህ ውሃ  ወድያውኑ መታጠብ አለብን፡፡
በሣምንት አንዴ ወይም በ15 ቀን 2ት ጊዜ ከተዘፈዝፍን  ይበቃል።ተዘፍዝፈን ስንጨርስ  በሌላ ለብ ባለ ባዶ ውሃ ያለሳሙና መለቃለቅ
ያስፈልጋል።

     እናመሰግናለን
           መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna