ስኳር ድንች መመገብ የሚያስገኛቸው 9 ጥቅሞች
🌴ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌴

1. የልብ ድካም ተጋላጭነትን ይቀንሳል

ስኳር ድንችን መመገብ ቫይታን 6 የሚያስገኝ ሲሆን ይህ የቫይታሚን አይነት ደግሞ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ለልብ ድካም የሚያጋልጥ የሆሞሳይስታይን ኬሚካል ያስወግዳል፡፡

2. የቆዳን ውበት እና ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል

ቫይታሚን ሲ እንደ ጉንፋን ያሉ በሽታዎችን ለማከም እና ለመከላከል የሚረዳ ሲሆን ስኳር ድንች ውስጥም ይገኛል፡፡

ቫይታሚን ሲ ለአጥንት እና ለጥርስ ጤንነት፣ ለምግብ መፈጨት እንዲሁም ለደም ህዋስ መመጣጠን የራሱ ጥቅም አለው፡፡

ከዚህም ባሻገር የቆዳን ውበት እና ጤንነት የሚጠብቅ ሲሆን ሰውነታችን ከካንሰር ጋር ለተያያዘ የበሽታ ስጋት እንዳይጋለጥ ያደርጋል።

በመሆኑም በውስጡ ቫይታሚን ሲ የያዘውን ስኳር ድንችን መመገብ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡

3. የአጥንት ጤንነትን ይጠብቃል

በስኳር ድንች ውስጥ የምናገኘው ቫይታሚን ዲ ለሰውነታችን የበሽታ መከላከል አቅም እና ለአጠቃላይ ጤንነታችን ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው፡፡

ከቫይታሚን ዲ የሚገኙት ንጥረ ነገሮች በዋናነት ምንጫቸው የፀሐይ ብርሃን ነው፡፡

ቫይታሚን ዲ ሃይልን፣ መነቃቃትን፣ የአጥንት፣ የቆዳ እና የጥርስ ጥንካሬን ያመጣል፡፡

በመሆኑም ከፀሐይ ብርሃን በተጨማሪ ከስኳር ድንች የሚገኘው ቫይታሚን ለሰውነታችን ጤና ወሳኝነት አለው።

4. በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል

ስኳር ድንች በውስጡ የአይረን ንጥረ ነገርን የያዘ መሆኑ ለሰውነታችን የበሽታ መከላከል አቅም ከፍ ማለት ጥቅም እንዲኖረው አድርጎታል።

አይረን ሰውነታችን በቂ ሃይል እንዲኖረው የሚያግዝ ንጥረ ነገር ሲሆን የነጭ እና የቀይ የደም ህዋሶችን በማጠናከር የበሽታ መከላከል አቅም እንዲጨምር ያደርጋል፡፡

5. ጭንቀትን ለማስወገድ ይረዳል

ስኳር ድንች በውስጡ የማግኒዥየም ንጥረ ነገር ክምችት ያለው በመሆኑ አዕምሮን በማነቃቃት ድብርትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ማግኒዥየም ለደም ቅዳ፣ ለደም፣ ለልብ፣ ለጡንቻ እና ለነርቭ ተግባራት መፋጠን ቀላል የማይባል ጠቀሜታ አለው።

6. የልብ ምትን ለመቆጣጠር ይረዳል

ፖታሺየም የተሰኘው ንጥረ ነገር የልብ ምትን እና የነርቭ መልዕክቶችን ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡

የጡንቻ መሸማቀቅ እንዳያጋጥም፣ የኩላሊትን እንቅስቃሴ የተስተካከለ እንዲሆንና የሰውነት እብጠትን በመቀነስ ረገድ ጉልህ ፋይዳ አለው፡፡

7. በደም ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን እንዲጨምር አያደርግም

ስኳር ድንች ጣፋጭ ምግብ ቢሆንም ወደ ደማችን የሚቀላቀለው ተፈጥሯዊ የስኳር መጠናቸው እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡
ይህም ለውፍረትም ሆነ ላልተፈለግ ክብደት የሚዳርግ የስኳር መጠን በደማችን ውስጥ ጭማሪ ሳይከሰት የሰውነት ሃይላችን እንዲስተካከል ያደርጋል፡፡

8. እርጅናን እና የካንሰር ህመምን ለመቋቋም ይጠቅማል

የስኳር ድንች ውስጣቸው በብርቱካናማ ቀለም የበለጸገ መሆኑ ከፍተኛ የካርቶኖይዶች መገኘት ማሳያ ነው፡፡

እነዚህ ካርቶኖይዶች ደግሞ ሰውነታችን ቫይታሚን ኤ እንዲያገኝ የሚያደርጉ ናቸው፡፡

ካርቶኖይዶች እይታችን የተስተካከለ እንዲሆን የበሽታ መከላከል አቅማችን ከፍ እንዲል እንዲሁም የካንሰር ህመም ተጋላጭነትን እና እርጅናን ለመቀነስ ጠቃሚ ናቸው፡፡

የሴቶችን ጤናማ አመጋገብ እና አኗኗር በተመለከተ በተደረገ አንድ ጥናትም ከዘወትራዊ አመጋገባቸው በተለየ ስኳር ድንችን ጨምሮ ካርቶኖይዶች የሚገኙባቸውን ሌሎች ምግቦችን የተመገቡት ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ዝቅተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

9. ለአመጋገብ እና አበሳሰል አመቺ ነው

ስኳር ድንች በማንኛውም መንገድ አብስሎ መመገብ ይቻላል፡፡

ለአብነትም ቀቅሎ፣ ጠብሶ፣ ከትፎ ወይም ፈጭቶ መመገብ የሚቻል መሆኑ ለአመጋገብ አመቺና ለማብሰልም ቀላል መሆኑን ያሳያል፡፡

ከተለያዩ አትፍክል እና ፍራፍሬዎች ጋር በማቀላቀልም አብስሎ መመገብ እንደሚቻል ነው የስነ ምግብ ባለሙዎች የሚያስረዱት።

እናመሰግናለን
           መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna