የአፍ ዉስጥ ፈንገስ
Author: admin
Date: 2023-02-03
የአፍ ዉስጥ ፈንገስ
🌴ከ ሀኪም ሰለሞን አዳም🌴
፨ምላስ ነጭ መሆን መንስኤው ካንዲዳ ከሚባሉ ዩስት ሲሆን የምላስ መንጣት ደግሞ ካንዲዲያሲስ ይባላል፡፡ ካንዲዳ ለሰውነታችን እጅግ ጠቃሚ ናቸው ነገር ግን ከመጠን በላይ በሚያድጉበት ወቅት ምልክቶችን ማሳየት ይጀምራሉ ።
መንስኤዎቹን
• የበሽታ የመከላከል አቅም መዳከም
• ለረጅም ጊዜ አንቲባዮቲክ መድሀኒቶች መጠቀም
• የወሊድ መቆጣጠሪያ መውሰድ
• ኢንሱሊን (የስኳር በሽታ መድሀኒት)
• እርግዝና መኖር
• ደካማ የአፍ ጤንነት አጠባበቅ
• የአፍ መድረቅ
• ትምባሆ መጠቀም
• አልኮል መጠቀም
• ጣፋጭ ምግቦችን መውሰድ
ምልክቶቹ
• እንደ አይብ የመሰለ ነጭ ነገር ምላስ ላይ መታየት
• የምግብ ጣእም አለመለየት
• በእጅ በሚነኩበት ጊዜ መድማት
• በአፍ ዙሪያ መቅላት
• ለማኘክ ፣ለመዋጥ መቸገር
የቤት ውስጥ ህክምናዎች
፧በደቃቅ ጨው ለአንድ ደቂቃ በጥርስ ብሩሽ ምላስን መቦረሽ፡፡ ከዚያም በሙቅ ውሀ በደንብ መታጠብ፡፡ ሁለት ጊዜ በየቀኑ ይድገሙ እና በሳምንት ውስጥ የሚፈልጉትን ውጤቶች ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም ለብ ያለ ውሀ ውስጥ 1 የሻይ ማንኪያ ጨው ይቀላቅሉ፡፡ በዚህ የጨው ውሀ አፍን በመሙላት ይጉመጥሞጡ ።
ሾርባ ላይ እሬት (አሎቬራ)በመጨመር በአፍ ውስጥ መጉመጥመጥ እንዲሁም 1 ማንኪያ የአሎቬራ ጭማቂ ይጠጡ ይህን መድሀኒት በየቀኑ ማድረግ ለ 2 ሳምንታት ያህል ማድረግ
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna