ወርቅ በሜዳ
Author: admin
Date: 2022-12-15
ወርቅ በሜዳ
🌴ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌴
፨ወርቅበሜዳ ማለት የዕፅ ስም ሲሆን
አብዛኛውን ጊዜ በወይናደጋና በበረሐ በድንጋያማ ቦታዎች ይበቅላል ።
በብዛት ከመሥከረም ወር ዕስከጥቅምት
30 በብዛት አፍርታና አብባ የምትገኝበት ወር ነው።
የወርቅ በሜዳ ዓይነቶች
1ኛው የሥሩ ፍሬ ዕንደኳስ ድቡልቡል ሆኖ
በጣም ትንንሽ ነው።
2ኛው ዕንደአገው ድንች ፍሬው ሞላላ ነው።
3ኛውና የመጨረሻው ልክ ዕንደዝንጅብል ነው።
ከሶስቱም ዓይነቶች ዝንጅብል የሚመስለው ይበልጣል።
ከተቆፈረ በኋላ ደርቆ ዕንደትዛዙ ዕስኪቀመም
ድረስ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ።በጣም የማቃጠል ስሜት ስለአለው
ለዓይን ፣ ለአፍንጫ፣ለፊት ቆዳ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። መድኃኒቱን ነክተን ምንም መንካት የለብንም
የወርቅ በሜዳ ጠቀሜታዎች
1ኛ ለማንኛውም የሆድ ውስጥሥራይ
የወርቅበሜዳ ዱቄቱን ግማሽ የሻይ ማንኪያ
ለክቶ በነጭ ማር ለውሶ ከምግብ በፊት መብላት
በ5 ቀን ልዩነት ለ3 ጊዜ በቂ ነው በሽታው የጠነከረ ከሆነ ካልሆነ ግን ለ1ጊዜ በቂ ነው።
2ኛ ለራስ ምታት /ራሱን ለሚያመው ለዘወትር ራስ ምታት 1የሻይ ማንኪያ ዱቄቱን በፍየል ቅቤ በእሳት/በፀሐይ አንጥሮ 3.3 ጠብታ እስኪድን ድረስ መጠቀም ነው ተቀርፍቶ/ትሉ ይወጣል።
3ኛ ለልብ በሽታ/ለጨጓራ ህመም ግማሽ የሻይ ማንኪያ በ1የውሃ ብርጭቆ አጓት ዘፍዝፎ አሳድሮ ከምግብ በፊት ጧት መጠጣት ነው።
፨ ምንአልባት ካደከመን መሻሪያው ዕርጎ
መጠጣት ነው።
4ኛ ራሱን ለሚያዞረው ሰው ልክ ዕንደሲጋራ ጢሱን በአፍና በአፍንጫ መሣብ ያድናል በቀን 2ጊዜ ለ10 ተከታታይ ቀናቶች።
5ኛ ነርቭን ጨምሮ ለማንኛውም የወገብ
ህመም የወርቅ በሜዳ ሥሩን ወቅጦ በንፁህ
ቅቤ አንጥሮ በጥቁር ጤፍ ገንፎ/ቂጣ
ለ15 ተከታታይ ቀናቶች መመገብ ነው።
6ኛ ለሣል በሽታ ለነቀርሣ በሽታና ለማንኛውም ሰውነት ለሚያሳክክ መጥፎ በሽታ 1 የሻይማንኪያ የወርቅበሜዳ ሥሩን ከነጭ ሽንኩርት ጋር ፈጭቶ በ1የውሃ ብርጭቆ አጓት አፍልቶ መጠጣት ነው ።
7ኛ ጉሮሮው ዕያበጠ ለሚሠቃይ ሰው
ሥሩን ከዕፀመናሄ ሥር ጋር በአንድነት
ወቅጦ በንፁህ ቅቤ ለውሶ ጣቱን አስገብቶ
መቀባት ነው ቶሎ ካልዳነ መደጋገም ይቻላል።
8ኛ ራሱን ለሚያዞረውና የደማነስ ችግር
ላለበት ሰው
» የጅብ ሽንኩርት
» ነጭሽንኩርት
» ቀይ የሐበሻ ሽንኩርት
» የወርቅበሜዳውን ሥር ጨምሮ
ዕኩል ዕኩል አድርጎ በ1ወቅጦ በነጭ ማር ለውሶ በባዶ ሆዶ 1ማንኪያ አኝኮ መዋጥ ነው።
፨ መድኃኒቱን ወስዶ በጣም ከደከመው ሻይ/ቡና ደጋግሞ ይጠጣበት አስፈላጊ ነው ።
ስትቀምሙም ሆነ ለመውሠድ ስታስቡ ከማብዛት ማሳነሱ ይመከራል በትእዛዙ መሠረት ቢዘጋጅ ደግሞ ይበልጥ ይመረጣል።
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna