የሳማ የጤና ጠቀሜታዎች
Author: admin
Date: 2022-12-06
የሳማ የጤና ጠቀሜታዎች
🌴ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌴
፨የሳማ ቅጠል ስለሚለበልብ በጥንቃቄ መሰብሰብ ያስፈልገጋል፡፡ሳማ በአገራችን በደጋ አካባቢ በእንጀራ ማባያነቱ ይታወቃል፡፡ለጋው ቅጠል ተቀንጥሶ ለአምስት ደቂቃ ያህል በፈላ ውሃ ይቀቀላል፡፡ የተቀቀለበት ውሃ ይጠለላል፡፡ ከዚያም በጭልፋ ወይም በእጅ ከገብስ ዱቄት ጋር ይታሻል ፡፡ መልሶ ከጥላዩ ውሃ ጋር ተለምሶ ጨው ተደርጎበት ይንተከተክና ይበስላል፡፡ ይህ ለእንጀራ ማባያ ይሆናል፡፡
ለመድኃኒት ሲሆን በዚሁ አይነት ከተዘጋጀ በኋላ ጨው ሳይሆን ማር ይጨመርበታል፡፡ ብቻውን መጠጣት ነው፡፡ ሌላው ለመድኃኒት ነት የዝግጅቱ ሥልት ሳማው ከማበቡ በፊት ቅጠሉ፣ሥሩ እና ዘንግ መሳይ ቀጫጭን እንጨቱ ተለቅሞ ይደርቅና ይወቀጣል፡፡ይህን ዱቄት በመጠጥ መልክ ከማር ወይም ከቅቤ ጋር አዘጋጅቶ መጠቀም ነው፡፡
ሳማ ከሚሰጣቸው የህክምና ጠቀሜታዎች መካከል
1. ለኩላሊት ችግር
2. የደም ስኳርን ለመቀነስ
3. ለጣፊያ መድማት
4. ለሰውነት ውስጥ ቁስለት ወይም ደም ፍሰት
5. ለምግብ መፍጫ የሰውነት ክፍሎች
6. ለኪንታሮት ቁስለት
7. ለማህጸንና ለሽንት ቧንቧዎች
8. የደም ግፊትን ለመቀነስ
9. ለጨጓራና አንጀት ቁስለት
10. ለደረት ህመም
11. በሰውነት ውስጥ ለሚገኝ አላስፈላጊ ፈሳሽ
12. ለልብ ድካም
13. ለፊኛ ህመምና ለሽንት ማስማጥ
14. ለኩላሊት ጠጠር እና
15. ለጉበት ሕመም ለዚህ ሁሉ በፈላ ትኩስ ውሀ ውስጥ ተጨምሮ ከማር ጋር ተበጥብጦ ይጠጣል፡፡ ለብርድ ቁርጥማት ወይም ለነርቭ ህመም በቅቤ ተለውሶ ይታሽበታል፡፡ ለቁስል በባዝሊን ተለውሶ ይቀባል፡፡
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna