የወባ በሽታ / malaria ምንድን ነዉ??
         🌿ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌿

፨በኢትዮጲያ በዋናነት ሁለት አይንተ የወባ በሽታ አሉ ፡፡ የወባ በሽታ ወቅትን ጠብቆ በተድጋጋሚ ና በስፋት የሚከስተ ወረርሸኝ በሽታ ሲሆን በሴት ወባ ትንኝ ንክሻ ወቅት ከምራቅዋ ጋር ወደ ደም ዝዉዉራች የሚገባ በአይን በማይታይ ጥቃቅን ፕሮቶዞአል ዝርያ ነዉ ፡፡ የወባ በሽታ በኢትዮጲያ ብዙ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ቀዉስ እና ሞት በማስከተል ቀዳሚ በሽታ ነዉ፡፡ በኢትዮጲያ በዋናነት ሁለት አይንተ የወባ በሽታ አሉ ፡፡

1.የጭንቅላት ወባ (P. falciparum )፡- በአብዛኛዉ በኢትዮጲያ ቆላ ቦታዎች የሚከሰት ሲሆን ከፍትኛ ጉዳት እና ብዙ ሞት ያስከትላል

2.ትንሽዋ ወባ(በአርባ ምንጭ አካባቢ አጠራር) (P. vivax ) ፡-በአብዛኛዉ በኢትዮጲያ ጋምቤላ አካባቢ አና በአነስተኛ መጠን በቆላ ቦታዎች የሚከሰት ሲሆን በተደጋጋሚ በመነሳት ታማሚዉን በማሰቃየት ትታወቃለች ፡፡
            የወባ በሽታ ምልክቶች፡-

፨ፕሮቶዞአል ደም ዝዉዉራችን ዉስጥ ከገባ በኋላ ለመራባት እና ለማድግ የቀይ ደም ህዋስን አካል( intracellular proteins) በመብላት እና የቀይ ደም ህዋስን ቅርጽ በመቀየር ቶሎ እንዲሞቱ ያደርጋል፡፡ከዚህም በተጨማሪ አና የሰዉንታችን ተፈጥሮአዊ መከላከል ሂደት ጋር በተያያዘ ብዙ ምልክቶችን ይፈጠራል፡፡

»ጤና ያለመሆን ስሜት
»እራስ ምታት
»ድካም
»የሆድ ህመም
»የጡንቻ ህመም
»ትኩሳት ከዛ ብርድ ብርድ ማለት አና »ማንቀጥቀጥ
»ማቅለሽለሽ አና ማስመልስ
»ፈጣን የልብ ምት
»ደም ማነስ ምልክት (jaundice)
»ጣፊያ ማደግ
»ደም ዉሰጥ ስኳር ማንስ / የረሀብ ምልክት
»ቶሎ ህክምና ካላገኘ ደሞ በጣም መዝለፍለፍ
»የህይወት ምልክቶች መዛባት/ የሰዉነት »ሙቀት አተነፋፈስ ልብ ምት እና ደም ግፊት መዛባት
»እራስን መሳት
»የኩላሊት ብቃት መቀነስ /ሽንት በደንብ »አለመእጣራት እና ትንሽ ሽንት መዉጣት
»የደም መርጋት መፍሰስ አና ደም ማነስ
»የጉበት ብቃት መቀነስ/አሲድ በሰዉነታችን ዉሰጥ መከማቸት አና መዳኒት አጠቃቀም መዛባት
               
              መከላከያ መንገዶች

ዉሃ ያቆሩ ቦታዎቹን ማፋሰስ
በ ኬሚካል የተነከረ አጎበር መጠቀም(በተለይ ቅድሚያ ለእርጉዞች እና ህፃናት)ወባማ አካባቢ ሲሄዱ መከላከያ መዉሰድወባ ማባረሪያ ቅባቶች መጠቀምተባይ ማጥፊያ ቤት ላይ መርጨት።
                   ህክምናዉ

እንደ በሽታዉ የህመም ደረጃ የሚዋጥ ወይም በመርፌ የሚሰጥ ይሆናል።

መዳሀኒቶቹን በአግባቡ እንዲወስዱ ከማድረግ እና ከመምክር በተጨማሪ ተያያዠና የተወሳሰቡ ችግሮችን እንደ ደረጃቸዉ ትኩረት ሰጥቶ ማየት እና አፋጣኝ እርምጃ መዉሰድ ያስፈልጋል፡፡

🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴

መልካም ጤንነት

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna