የአስም በሽታ
      🌿ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌿

፨አስም የአየር ቧንቧዎች በሽታ ሲሆን የአተነፋፈስ ስርዓትን በማዛባት ለመተንፈስ አዳጋች ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

የአየር መተላለፊያ ቧንቧዎችን እንዲቆጡ በማድረግ ወደ ሳንባ ኦክስጂን የሚወስዱ ቧንቧዎችን እንዲጠቡ ያደርጋል፡፡

ይህም እንደ ሳል፣ ሲተነፍሱ ድምጽ ማዉጣት፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የደረት መወጠር እና የመሳሰሉት የአስም በሽታ ምልክቶችን ያስከትላል፡፡
ከባድ የአስም በሽታ ለመንቀሳቀስ እና ለማውራት እስከመቸገር ያደርሳል፡:
የአስም በሽታ ጥሩ የሚባል ህክምና ቢኖሩትም አደገኛና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው በሽታ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም።

#የአስም በሽታ የተለያዩ 3 ገጽታዎች አሉት እነሱም፦

1ኛ  የአየር ቧንቧን በመዝጋት በጤናማ የአተነፋፈስ ስርዓት የአየር ቧንቧዎችን የከበቡት ጡንቻዎች ዘና ይላሉ።

ይህም የአየር ቧንቧ ያለምንም መጨናነቅ እንዲንቀሳቀስ ያደርገዋል፡፡
ነገር ግን የአስም በሽታ ያለባቸው ሰዎች አለርጂ፣ ጉንፋንና የአካባቢያችን ሁኔታዎች የአየር ቧንቧዎችን የከበቡትን ጡንቻዎች እንዲጠብቁ ያደርጋቸዋል። ከዚያም አየር በትክክል እንዳይተላለፍ ያደርገዋል፡፡ ወደ ውስጥ የሚገባው አየር ሲያንስ ሰውየው የትንፋሽ እጥረት ያጋጥመዋል።በጣም በጠበቡት የአየር ቧንቧዎች የሚወጣው አየር ትንፋሻችን ድምጽ እንዲኖረው ያደርገዋል፡፡

2ኛ  የቧንቧዎች መቆጣት አስም ያለባቸው ሰዎች የመተንፈሻ ቧንቧዎቻቸው ያብጡና ቀይ ይሆናሉ፡፡

ይህ የቧንቧዎች መቆጣት ከብዙ ጊዜ ቆይታዎች በኋላ በአስም ምክንያት ለሳንባ መጎዳት ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያደርጋል፡፡

ይህን የቧንቧዎች መቆጣትን ማከም የአስም በሽታን ለመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያደርጋል፡፡

3ኛ  የአየር ቧንቧዎች ማሳከክ/መቆጣት በአስም በሽታ የተያዙ ሰዎች የአየር ቧንቧ ከመጠን በላይ ቁጡና ቶሎ ምላሽ የሚሰጡ ናቸው፡፡
እነዚህ የአየር ቧንቧዎች በጣም በትንሽ ሽታ ለምሳሌ የአበባ ዱቄት፣ የእንሰሳት ሽታ አቧራና የመሳሰሉት በቀላሉ እንዲቆጡና እንዲጠቡ ያደርጋቸዋል፡፡
አስም በአዋቂ ሰዎች ላይ

የአስም በሽታ በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ እድሜያቸው ከ40 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች ላይ የተለመደ ነው፡፡ በአስም የተያዘ የቤተሰብ አባል ያለው ሰው በአስም የመያዝ እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡
አለርጂክ እና አስም አብረው የመከሰት እድል አላቸው፡፡አስም ማንኛውንም ሰው በማንኛውም ጊዜ ሊይዝ ይችላል። ስለዚህ የአስም ምልክቶች ከታዩ በአፋጣኝ የህክምና እርዳታ ያግኙ፡፡

           አሰም በህፃናት ላይ

አስም ህፃናትን በብዛት ይይዛል።
የአሰም ምልክቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በአንድ ህፃን ላይ ሊለያይ ይችላል፡፡
ልናስተውላቸው የሚገቡ የአስም ምልክቶች እነሆ፦

° በተደጋጋሚ መሳል፦ በሚጫወቱበት፣ በሚስቁበትና ማታ ላይ ያስላቸዋል፡፡
በአስም በሽታ ጊዜ ሳል ብቸኛ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡

° በጨዋታ ጊዜ የአቅም ማነስ ወይም በጨዋታ ጊዜ ትንፋሽ ለመሰብሰብ መቆም

° ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
° የደረት መታፈን
° አየር ሲያስወጡ እና ሲያስገቡ ለየት ያለ ድምጽ መኖር
° የትንፋሽ መጨመርና መቀነስ ወይም የተዘበራረቀ አተነፋፈስ
° የትንፋሽ ማጠር
° የአንገትና ደረት ጡንቻዎች መጠንከር
° የድካም ስሜት

የአስም በሽታ መነሻና የሚያባብሱት ነገሮች፦

፨የአስም በሽተኞች የአየር ቧንቧ በአካባቢያችን ለሚገኙ ብዙ ነገሮች በቶሎ መሰማት እና ቁጡ እንዲሆን ያደርጉታል፡፡

ከነዚህ ነገሮች ጋር ንክኪ ሲኖረን የአስም በሽታ ምልክቶች እንዲጀምሩ ወይም እንዲባባስ ያደርጋቸዋል፡፡

የሚከተሉት የአስም በሽታ መነሻ ናቸው።

የሳይነስ፣ ጉንፋንና ፍሉዌንዛ ኢንፌክሽኖች የአበባ ዱቄት(ፖለን)፣ ሻጋታ፣ የቤት እንሰሳት ሽታና አቧራ ነገሮች ጠንካራ ሽታ ያላቸው ሽቶዎች፣ የማጽጃ ፈሳሾች ሽታና የተበከለ አየር የሲጋራ ጭስ/ሲጋራ ማጨስ አንዳንድ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የአየር ሁኔታ፦ የሙቀት ሁኔታ መቀያየር፣ እርጥበታማ አየር፣ ቀዝቃዛ አየር ጭንቀት፣ ሳቅ ወይም ለቅሶ፣ ዉጥረት የተለያዩ መድሃኒቶች(አስፕሪን) ናቸው ።

     የአስም በሽታ መከላከያዎች፦

° የኢንፍሉዌንዛ እና ኒሞኒያ ክትባት መዉሰድ ክትባቶችን በጊዜ መውሰድ ለአስም በሽታ መነሻ ሊሆኑ የሚችሉትን ኢንፍሉዌንዛ እና ኒሞኒያ መከላከል ይችላል።

# ለአስም በሽታ የሚያጋልጡ ነገሮችን ለይቶ ማወቅና ማስወገድ ከቤት ውጪ የሚገኙ እንደ አበባ ዱቄት ፣ ቀዝቃዛ አየርና የአየር ብክለት የመሳሰሉት የአስም በሽታ ሊያስነሱ ስለሚችሉ  ከነዚህ ነገሮች መራቅ ተገቢ ነው፡፡

° የአተነፋፈስ ሁኔታን መከታተል የአስም በሽታ ምልክቶች የሆኑትን ሳል፣ የትንፋሽ እጥረትና የመሳሰሉት ማስተዋልና ህክምና ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
° ቶሎ(በጊዜ) መታከም በቶሎ እርምጃ የምንወስድ ከሆነ በሽታን ስር ሳይሰድ መቆጣጠር እንችላለን፡፡

#መድሃኒቶችን በታዘዙልን መሰረት መዉሰድ/መጠቀም

#የአስም ህክምና በሊቃውንት እና በጠቢባን አንደበት ፦
ሲታዩ:-

#ቀጠጥና፥ ቁጥንጢና፤ጉራ ሃሬ፤ የአህያ ጀሮ፤ዕፀ ደብተራ፤.ዳባቀደድ
እየተባለ የሚጠራው ጥቅመ ብዙ ዕፅ በምስል ከስር አበባውን እና ቅጠሉን እንደምትመለከቱት ከ 60 በላይ የበሽታ አይነቶችን የማዳን ዓቅም ያለው ዕፅ ነው።

#ቀጠጥና የሚበቅልበት መልክዓ ምድር ደጋ ወይና ደጋ እንዲሁም ቆላ አከባቢ የሚገኝ መልካም ዕፅ ነው።

ይህ ዕፅ መርዝ አልባ ወይም ከመርዛማ ዕፀዋት ውጭ የሚመደብ ዕፅ ሲሆን በየአከባቢው ለተለያየ አገልግሎት የሚውል ዕፅ ነው።

#ቀጠጥና ለአስም በሽታ መድኃኒት ሲሆን፦
          በመጀመሪያው 1ኛ
ሳምንት የቀጠጥና ቅጠል ሰባት ዘለላ ቅጠል በመቁረጥ ማታ ማታ በውኃ  በመቀቀል ለሰባት ቀን በልብስ ተሸፍኖ በደንብ ታጥኖ መተኛት!

# ሁለተኛው ድርጊት ደግሞ ቅጠሉ እና ሥሩን  እኩል በመለካት በደንብ አድርቀው ወቅጠው ነፍተው በግማሽ ኪሎ ጣዝማ ማር ሰባት የሾርባ ማንኪያ መድኃኒት ወደ ጣዝማው በመጨመር ጧት ጧት አንድ አንድ የሾርባ ማንኪያ እየበሉ መውጣት።

#2ኛው ሳምንት  የመጀመሪያው ደረጃ እንዳለቀ ማታ ማታ ቅጠሉን ብቻ አድርቀው እንደ ሻይ ቅጠል ሸርከት አድርገው ደቁሰው ሊተኙ ሲሉ ከፈላ ውኃ ጋር አንድ የሾርባ ማንኪያ ቅጠል በመጨመር ሊወጣ ሲል ትንሽ ማር ጠብ አድርገው በትኩሱ እንደሻይ ጠጥተው መተኛት።

በወተትም ማድረግ ይቻላል። ጧት ጧት ደግሞ ቢጫ አበባውን በደንብ በንጽህና በማድረቅ በደንብ ወቅጠው ነፍተው በንፁህ የፀጉር ቅቤ በመለወስ በፀሐይ በማቅለት በሁለቱም አፍንጫ ሶስት ሶስት ጠብታ ያስገቡ ትንሽ ደቂቃ ቀና ብለው ይቆዩ
ይህን ድርጊት
ለሰባት ቀን ያከናውኑ።

ውጤቱን እና ለውጡን ለማየት አንድ ወር  ሙሉ ይጠቀሙ ።

መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ  መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን  ያማክሩ
• አድራሻ ፡-አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202      ወይም ፡- 0911810736