አስደናቂው የአህያ ጆሮ የጤና በረከቶችን 🌿ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌿
Author: admin
Date: 2022-10-10
አስደናቂው የአህያ ጆሮ የጤና በረከቶችን
🌿ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌿
፨ይህን ዕፅ ከሌሎች ዕፀዋቶች ልዩ
የሚያደርገው ከሌሎችዕፀዋቶች በተለየ ሁኔታ
ከ60 በላይ ለሚሆኑ የበሽታ ዓይነቶች አስደናቂ ፈውስ መስጠት መቻሉ ነው፡፡
»ይህን ዕፅ በባህላዊ ህክምና የተለያዩ ሐገራት ይጠቀሙበታል።በተለይ በህንድ ሐገር በሰፊው ጥቅም ላይ ይውላል ።
የዚህ ዕፅ ስያሜ በተለያዩ ቦታዎች የተለያየ ነው በብዛት ሚታወቅባቸው ስሞቹ የሚከተሉት ናቸው።
✔️1ኛ የአህያ ጆሮ
✅2ኛ ቀጠጥና
☑️3ኛ ዕፀእስራኤል
✔️4ኛ ዕፀነቢያት
☑️5ኛ ዳባቀደድ ይባላል ይህ ስያሜ በአማረኛ ነው
»በኦሮሚኛም ጉራ ሃሬ እየተባለ ይጠራል
»የእንግሊዘኛ ስያሜውን ደግሞ ስንመለከት
( donkey's ear plant) ብለው ይጠሩታል
የጤና በረከቶቹን
1ኛ ካንሰርን ጨምሮ ለማንኛውም የቁስል ማድረቂያ ይሆናል
አጠቃቀሙን፦ በሚመለከት ቅጠሉንም ስሩንም በአንድነት ከትክቶ ወቅጦ አድርቆ ዱቄቱን በቁስሉ ላይ መነሥነስ ነው ::እስኪድን ድረስ እየደጋገሙ ማድረግ ነው።
2ኛ ጆሮውን ለዘጋው ወይም መስማት ለተሳነው ሰው
የመድኃኒት አጠቃቀሙ፦የዕፁን ፍሬ ለቅሞ በእርጥቡ ወቅጦ በንፁህ ቅቤ አንጥሮ
በብልቃጥ በማስቀመጥ መጠቀም ሲያስፈልግ
ብልቃጧን የፈላ ውሃ ላይ ዕንደተከደነች
ማስቀመጥ ከትንሽ ደቂቃ በኋላ በቅቤ የተነጠረው መድኃኒት ይቀልጣል
ከዚያ በኋላ 3/2 ጠብታ ጆሮ ውስጥ መጨመር ነው።
3ኛ ለጨጓራ በሽታ አጠቃቀሙ
ሥሩንም ቅጠሉንም አምጥቶ በደንብ አጥቦ
ከትከት በማድረግ ወቅጦ አድርቆ ዱቄቱን 1 የሻይ ማንኪያ ከ2 የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ የተልባ ዱቄት ጋር በመቀላቀል በዕለት ውሃ ልክ ዕንደሽሮ ብጥብጥ በመበጥበጥ ትንሽ ወፈር አድርጎ በጥብጦ ከማንኛውም ምግብ በፊት
በጥቁር ጤፍ እንጀራ መብላት ነው
ለ10 ቀን በተከታታይ ይውሰዱት ፈፅሞ ይድናል
ለ15 ቀን ያክል ቡናና አልኮል መጠጥ
ክልክል ነው።
4ኛ ለዓይን ህመም ደርሶ ዓይኑ ለሚቀላ
ወይም ዓይናር ዕየያዘ ለሚቸገር ሰው
ወይም ለትራኮማ በሽታ ወይም ዓይኑ ላይ እንደጭጋግ ለጣለበት ሰው
ወይም ዳፍንት በሽታ ባስቸገረ ጊዜ
እንዲህ ይጠቀሙታል ልጡንና ቅጠሉን በንፁህ ውሃ አጥቦ በጥንቃቄ ወቅጦ በወፍራም የፋሻ ጨርቅ አጥልሎ በታመመው ዓይን ውስጥ 2:2 ጠብታ መጠቀም ይቻላል።
5ኛ ሖድ ቁርጠት ወይም መጋኛ ላለበት ሰው
አጠቃቀም
ሥሩን ብቻ ቆርጦ በንፁህ ውሃ አጥቦ ከምግብ በፊት ልክ እንደሸንኮራ አገዳ መምጥና ምጣጩን መትፋት ነው ወድያውኑ የመዳን ምልክት ያሣያል
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
መልካም ጤንነት
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna