የሪህ ህመም የዕፅዋት መፍትሔ
Author: admin
Date: 2022-10-07
የሪህ ህመም የዕፅዋት መፍትሔ
🌿ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌿
፨ሪህ(Gout) በመገጣጠሚያ ላይ በተለይ ደግሞ በእግር ትልቁ ጣት ላይ በድንገት የሚጀምር ከፍተኛ ህመም ስሜት፣እብጠትና መቅላት የሚመጣ የህመም አይነት ነው ፡፡ሪህ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ላይ በብዛት የሚከሰት ቢሆንም ሴቶች ካረጡ በኋላ ለህመሙ ተጋላጭነታቸው እየጨመረ ይመጣል፡፡
🌿የህመሙ ምልክቶች
የሪህ የህመም ምልክቶች ብዙውን ጊዜ ያለማስጠንቀቂያ በድንገት የሚከሰት ሲሆን በብዛት የሚጀ ምረው ማታ ላይ ነው፡፡
• ከፍተኛ የሆነ የመገጣጠሚያ ላይ ህመም፡- ምንም እንኳ ሪህ በአብዛኛው የሚከሰተው የእግር አውራ ጣት ላይ ቢሆንም በእግር መዳፍዎ፣በቁርጭምጭሚትዎ፣ በጉል በትዎ፣ በእጅዎ መገጣጠሚያዎች ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ ህመሙ ከጀመረ የመጀመሪያዎቹ ከ4 እስከ 12 ሰዓታት ውስጥ በጣም ሊባባስ ይችላል፡፡
• ቀጣይነት ያለው ህመም/ምቾት ያለመሰማት ስሜት፡- ከፍ ያለው ህመም ካለፈ በኋላ የተወሰነ ህመምና ምቾት ያለመሰማት ከቀናት እስከ ሳምንታት ድረስ ሊቀጥል ይችላል፡፡
• የመቆጥቆጥና የመቅላት ስሜት፡ – በህመሙ የተጎዳው መገጣጠሚያ የማበጥ፣ ሲነካ የማመምና መሞቅ ስሜት እንዲሁም የመቅላት ባህሪ ይኖረዋል፡፡
• እንቅስቃሴ መገደብ፡- ህመሙ እየፀና ሲመጣ መገጣጠሚያው መታዘዝ/ መንቀሳቀሱን ይቀን ሳል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት የህመም ምልክቶች ካሉት ህክምና ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ ህመሙ ከመጣ በኋላ ህክምና ሳይደረግ በራሱ ጊዜ ከጠፋ ህመሙ እየተባባሰና መገጣጠሚያውን ስለሚጎዳው መታከም ያስፈልጋል፡፡
የህመሙ ምክንያት
ሪህ የሚከሰተው ዩሬት ክሪስታል የሚባለው ኬሚካል መገጣጠሚያ ውስጥ ተጠራቅሞ የመቆጥቆጥ ስሜት/inflammation/ እንዲጀ ምር ወይም እንዲነሳ በማድረግ የህመሙ ምልክቶች እንዲመጣ ያደርጋል፡ ፡ ዩሬት ክሪስታል የሚመጣው በደማችን ውስጥ የዩሪክ አሲድ መጠን ከሚፈለገው መጠን በላይ ከፍ ሲል ነው፡፡
ሰውነታችን ዩሪክ አሲድን ፕዩሪንስ የሚባሉ ኬሚካሎችን በሚሰባብርበት ወቅት የሚመረት ሲሆን ፕዩሪንስ በተፈጥሮ በሰውነታችን ውስጥና በተወሰኑ እንደ ስጋና የባህር ምግቦች ውስጥ ይገኛል። በተጨማሪም ከፍ ያለ ዩሪክ አሲድ በሰውነታችን እንዲኖር ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አልኮሆል(በተለይ ቢራ) እና እንደ ፍሩክቶስ ባሉ የፍራፍሬ ስኳር የጣፈጡ መጠጦች መጠጣት ናቸው፡፡
ዩሪክ አሲድ በደምዎ ውስጥ በመሟሟት ከሰውነትዎ በኩላሊት አማካይነት እንዲ ወገድ ይደረጋል፡፡ ነገር ግን ሰውነታችን ከሚፈለገው መጠን በላይ ዩሪክ አሲድን ካመረተ አሊያም ኩላሊትዎ ከሚገባው በታች ከሰውነታችን እያስወገደች ከሆነ የዩሪክ አሲድ መጠን በሰውነታችን ውስጥ በመጨመር ዩሬት ክሪስታል በመገጣጠሚያ ውስጥ እንዲፈጠር በማድረግ የህመም ስሜቶች እንዲከሰት ያደርጋል፡፡
ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች
በሰውነትዎ ውስጥ በጣም ብዙ ዩሪክ አሲድ ካለዎ ሪህ ሊከሰት ይችላል፡፡በሰውነትዎ ውስጥ የዩሪክ አሲድ መጠን እንዲጨምር ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ፤-
• አመጋገብ፡- አመጋገብዎ ውስጥ ስጋ፣ የባህር ምግቦችን/sea food/፣ በፍሩክቶስ የፍራፍሬ ስኳር የጣፈጡ መጠጦች፤ አልኮሆል (በተለይ ቢራ) ማዘውተር የዩሪክ አሲድ መጠን እንዲጨምር ስለሚያደርጉ ለሪህ ህመም ተጋላጭነትዎን ሊጨምር ይችላል፡፡
•ውፍረት፡- ክብደትዎ ከመጠን በላይ ከሆነ ሰውነትዎ ብዙ ዩሪክ አሲድ እንዲያመርት ስለሚያደርግና ኩላሊትዎ ላይ ጫና ስለሚፈጥር ለሪህ ያጋልጥዎታል፡፡
• የውስጥ ደዌ ችግሮች፡- የስኳር ህመም፣ የልብ ችግር፣ ያልታከመ የደም ብዛት፣ ሜታቦሊክ ሲንድረምና የኩላሊት ችግር ካለዎ ለሪህ ተጋላጭነትዎ ይጨም ራል፡፡
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
መልካም ጤንነት
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna