የጊዜዋ ተክል ጤና በረከት
Author: admin
Date: 2022-10-05
የጊዜዋ ተክል ጤና በረከት
🌿ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌿
፨የጊዜዋ ተክል የጤና በረከቶችን ከብዙው በጥቂቱ እናካፍላችው።
»በግእዝ ዕፀግዕዝ ተብሎ ይጠራል በአማረኛ ደግሞ ጊዜዋ/ ግዜዋ በመባል ይጠራል።
»በህንድና በኢሮፕ አሽዋ ጋንዳ የሚሰኘው ይህ የተክል ዓይነት በሐገራችን ደግሞ ጊዜዋ/
ግዜዋ እየተባለ ይጠራል።ይሄን የተክል ዓይነት
ከጥንት ጀምሮ የባህል ህክምና አዋቂዎች ይጠቀሙታል።
»ከሦሥት ሺ ዓመታት በፊት ጀምሮ በሽታ የመከላከል አቅምን ለማዳበር ከሰውነት ውስጥ መርዛማ ነገሮችን ለማስወገድ፤ለጭንቀት
፤ለብርታት ትኩረትን ለመሠብሰብ ወይንም ትውስታን ለማሻሻል ያገለግላል።
»ይሄ የተክል ዓይነት በብዛት በህንድና በሰሜን አሜሪካ ታዋቂ ሲሆን በአፍሪካም ይገኛል፡፡
ሥሩና ቅጠሉ ለተለያዩ የበሺታ ዓይነቶች
በመድኃኒትነት ያገለግላል።በሐገራችንም በብዙ
ሊቃውንቶች ይሄ የተክል ዓይነት ፍቱን መድኃኒት ዕንደሆነ ተዘግቧል፡፡
11 ለማመን የሚከብዱ የጤና ጥቅሞችን
1️⃣ኛ > ፀረካንሠር ነው፡፡እንደኢሮፓውያን አቆጣጠር በ2011 የተደረጉ ጥናቶች
ዕንደሚያሣዩት ጊዜዋ የተወሰኑ የካንሠር
ደረጃዎችን ይከላከላል፡፡ጊዜዋ ከሚከላከላቸው የካንሰር ዓይነቶች መካከል።
🌴 የጡት ካንሰር
🌴የሳንባ ካንሠር
🌴የአንጀት ካንሠር
🌴የጭንቅላት ካንሠርና የጡት ካንሠር ተጠቃሾች ናቸው።
2፦ የኮልስትሮን መጠንን በመቀነስል የልብ ጤንነትን ይጠብቃል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ጊዜዋ የደም ውስጥ ስብን ይቀንሣል::
»ለምሣሌ በአንድ ጥናት ላይ ለማዎቅ ዕንደተቻለው፤ጊዜዋ የኮልስትሮን መጠንን
53% ይቀንሣል፡፡
3፦ለጡንቻ ጥንካሬና ኃይል ይሰጣል፡፡
ጥናቶች ዕንደሚያሳዩት ጊዜዋ የካል አደረጃጀትን ያሻሽላል ።ዕንዲሁም የጡንቻ ጥንካሬን ይለግሣል።
➡➜በነገራችን ላይ ስሙም የሚናገረው የኃይልና የጥንካሬ ምንጭ መሆኑን ነው።
(Ashwagandha)የሚለው ስም /ቃል የጥንት
ህንዳውያን ቃል ሲሆን ሲተረጎም አሽዋ ማለት ልክ
ዕንደፈረስ ማለት ነው ።
>>ጋንዳ ማለት ደግሞ ሽታ ማለት ነው።
ተክሉ ልክ ዕንደፈረስ ኃይልና ብርታት የሚሰጣችሁ
ሲሆን ጥሩ የሆነ ሽታም አለው::
4፦ የደም ውስጥ ስኳርን ይቀንሳል ::
ተጨማሪ ሌሎች ጥናቶችም ዕንደሚያሣዩት
ጊዜዋ የስኳር ታማሚ ከሆኑትም ካልሆኑትም ላይ የደም ውስጥ ስኳራቸውን መቀነስ ችሏል::
በሌላ በኩል ለ4 ሳምንት የስኳር ታማሚዎች ጊዜዋን ዕንዲመገቡ ተደርጎ የደም ውስጥ ስኳር ጭማሪ ከስኳር መቆጣጠሪያ ኪኒኖች ይልቅ በተሻለ ሁኔታ ዝቅ ማድረግ ችሏል`። ሲጠቀለል ዓይነት ሁለት የስኳር ታማሚዎች ጊዜዋን ከተጠቀሙ በሚገባ የደም ውስጥ ስኳር ጭማሪያቸውን መግታት ይችላሉ።
5፦ ጊዜዋ ፀረድብርት ነው።
ጊዜዋ በድብርት ለሚሠቃዩ ሰዎች ጥሩ መፍትሔ ነው::ለምሣሌ በአንድ ጥናት ላይ ለማወቅ ዕንደተቻለው ከፍተኛ ድብርት ያለባቸው በሁለት ምድብ ተከፍለው
አንደኛው ምድብ ጊዜዋን ዕንዲጠቀሙ ተደረገ::
ሁለተኛው ምድብ ደግሞ ኪኒን ተሰጣቸው ::
በውጤቱ ጊዜዋን የተጠቀሙት 80 በመቶ ከድብርታቸው መላቀቅ ሲችሉ ::የድብርት ማባረሪያ ኪኒን የወሰዱት ግን 10 በመቶ ብቻ ነው ከድብርት በሽታ መላቀቅ የቻሉት
የጎንዮሽ ጉዳቶቹ፦
»ይሁን ዕንጅ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ዕንዲወስዱት ዓይመከርም::
»ዕነዚህም ዕርጉዞችና ጡት የሚያጠቡ ሴቶች
»ዕንዲሁም ዓይነት አንድ የስኳር ታማሚዎችና
ሰውነታቸው በሽታን የመከላከል አቅም ችግር ያለባቸው ሰዎች ባይጠቀሙት ይመከራል ::
አለበለዚያ ደግሞ ከጤና ባለሙያቸው ጋር መመካከር ተገቢ ነው::
»ብዙውን ጊዜ በሐገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት የሚገኝበትን ቦታ በብዛት ወይናደጋ የአየር ንብረት ባለባቸው አካባቢዎች ይበቅላል በበረሐውም ሖነ በየደጋማ ቦታው ይገኛል ከኛ የሚጠበቀው ጠቃሚ መሖኑን መረዳት ብቻ ነው።
የሚያድናቸውን የበሽታ ዓይነቶች
1🍀 ማንኛውንም ካንሠር በሽታ ይፈውሳል ።
አጠቃቀሙ ፦
>የጊዜዋውን ሥሩንም ዕንጨቱንም ቅጠሉም ሣይቀር በንፅህና ወቅጦ ከደረቀ በኋላ ዱቄቱን
ከዕፀአሜራና ከጎርጠብ ዱቄት ጋር ጧት ከቁርስ በኋላና ማታ ከራት በፊት 1 ብርጭቆ ከግማሽ የሚሆን ውሃ በማፍላት ከፈላ በኋላ 1የሻይ ማንካያ ሙሉ ከመድኃኒቱ ውህድ በመጨመር ቀጥሎ ማሩን 1 በሾርባ ማንኪያ ሙሉ ማድረግ ከዝያ ለ5 ደቂቃ ያክል ማንተክተክ ቀጥሎ ከሳቱ ላይ ማውረድ ከዝያ በኋላ ትንሺ ቀዝቀዝ ሲል አጥልሎ የመድኃኒቱን ውሃ መጠጣት ለ2 ወር ከወሰዱ በቂ ነው።
2🍀 የኮልስትሮን መጠንን በሚገባ ይቀንሣል
አጠቃቀም
መጠጣት የምንችለውንያክል ንፁህ ውሃ ብቻውን ማፍላት ልክ ውሃው ዕንደፈላ የጊዜዋውን ቅጠል ከ1--4 ዘለላ ቅጠል ካፈላነው ውሃ ላይ መጨመር ከዝያ 1 ደቂቃ አቆይተን ማውጣት ትንሽ ሲቀዘቅዝ አጥልለን መጠጣት ለቃናው ትሽ ማር መጨመር ይቻላል ለ1 ወር ያክ ከወሰድን በቂ ነው።
በቀን 2 ጊዜ ጧት ከቁርስ በፊት ማታ ከራት በኋላ ይጠቀሙ።
3🍀 ለጡንቻ ጥንካሬ ለኃይልና ለሠውነት አደረጃጀት ይሆናል
አጠቃቀም
የጊዜዋውን ሥር ዕንጨቱንና ቅጠሉንም ሣይቀር ወቅጦ አድርቆ ዱቄቱን በማር ለውሶ ጧት ጧት በስንዴ በገብስ/በበቆሎ ዳቦ 1 የሾርባ ማንኪያ ያክል መብላት ነው አዘውትሮ ቢጠቀሙት መልካም ነው።
4🍀 የደም ውስጥ ስኳርን
ነቅሎ ይጥላል የዓይነት ሁለት የደም ውስጥ ስኳር ላለባቸው ሰዎች ፍቱን መፍትሔ ነው።
አዘገጃጀት
የጊዜዋውን ቅጠል ከግራዋ ቀጠል ጋር ዕኩል መጥኖበደንብ አጥቦ ወቅጦ 1ማንኪያ በ1ብርጭቆ ውሃ ማታ ዘፍዝፎ በማሣደር ጧት ከምግብ በፊት አጥልሎ መጠጣት ይቻላል ለጣዕም ያክል ትንሺ ስኳር/ማር ይጨመራል ለ3 ወር ያክል ከተጠቀምነው በቂ ነው።
5🍀 ግዜዋ ፀረድብርት ነው ከድብርት ማባረሪያ ዘመናዊ ክኒኖች ይልቅ ለድብርት ፍቱን መፍትሔ ነው፡፡
አዘገጃጀቱ
ቅጠሉን ወቅጠን አድርቀን ዱቄቱን በውሃ ልክ ዕንደዳቦ ቆሎ /ዕንደኪኒን መጠን ያክል አድበልብለን አድርቀን ማስቀመጥ ነው ።
መጠቀም ስንፈልግ ደርቆና ተድበልብሎ የተቀመጠውን የግዜዋ ዱቄት ፈጭተን በውሃ በጥብጠን መጠጣት ዕንችላለን ድብርቱ ከለቀቀን በኋላ መተው ዕንችላለን።ከዚህ በተረፈ የጊዜዋ ተክል ብዙ ተነግረው የማያልቁ በጣም ለማመን የሚከብዱ የጤና በረከቶችን ይዟል።
6🍀 ለወፍ/ለጉበት በሽታ ይሆና
7🍀 የሰው ዓይን/የቡዳ በሽታ ለሚባለው ይሆናል
8🍀 ለሰው ውለሽ
ወይም ለተዋለበት ሰው ፍቱን መፍትሔ ነው
9🍀 ለዓይነጥላ/ገርጋሪ ፍቱን መፍትሔ ነው
10🍀 ለማንኛውም በሰው ሰራሽ ምክንያት ለተዘጋ ነገር ሁሉ አስተማማኝ መፍትሔ ይሰጣል።
11🍀 ለጨብጥ ወይንም ለአባላዘር በሽታ ፍቱን መፍትሔ ነው ።
እናመሰግናለን!!
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
መልካም ጤንነት
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/kidusmikaelhikmna