አንገት ህመም። መንስኤው፣ ምልክቶቹ እና ህክምናው
🌿ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌿

፨አንገታችን ከጀርባው የጀርባ አጥንት ሰረሰር
የሚሄድበት ሲሆን በፊት በኩል ደግሞ የትንፋሽ
ቧንቧ የሚያልፍበት የሰውነት አካል ነው። ከዛ ውጪ የአንገት ጡንቻ፣ የደም ቧንቧ እና ህብለሰርሰር የያዘ ለስላሳ የሰውነት ክፍል ነው።
በተደጋጋሚ የሚፈጠሩት የአንገት ህመም አይነቶች
ጤናችንን ስጋት ውስጥ የማይከቱ ሲሆን አልፎ
አልፎ የሚከሰቱት ህመሞች ግን የከባድ ህመም
ምልክት ሊሆኑ ይችላሉ።
# የአንገት ህመም መንስኤዎች እና ህክምና ፡-
ሌላ ህመም ወይም ጉዳት ሳይኖርብን የአንገት ህመም እና ቁርጥማት በየቀኑ የሚሰማን ከሆነ የሚከተሉት አንዱ የህመሙ መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ።
- ወለምታ ወይም ውጥረት፡- ያልተስተካከለ አቋም ወይም በአንድ ሁኔታ ለረጅም ሰአት መቆየት የጀርባ አጥንት ችግሮች ወለምታ ወይም ውጥረት ከፍተኛ የአካል እንቅስቃሴ ካደረግን በኋላ የሚፈጠር ችግር ነው። ብዙ ግዜ ከረጅም ግዜ በኋላ አዲስ እንቅስቅሴ ስንጀምር ይከሰታል።
- የአንገት ወለምታ ህክምናው እንደማንኛውም
የጡንቻ ወለምታ ነው። ጉዳቱን ያስከተለውን አይነት - እንቅስቃሴ ከማድረግ መቆጠብ
- እረፍት መውሰድ
- ቦታው ላይ በረዶ ማድረግ። የህመም እና ቃጠሎ ስሜቱን ይቀንሳል ወለምታ ከግዜ ጋር በራሱ የሚድን ህመም ሲሆን የዶክተር ክትትል የሚያስፈልገው ነገር አይደለም። ካስፈለገ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች መውሰድ ይችላል። የወለምታው ስሜት በቀናት ውስጥ ለውጥ ካላሳየ እና በ1-2 ሳምንት ውስጥ ካልጠፋ ዶክተር ማየት ያስፈልጋል።
ዶክተር ሌላ ህመም ካላገኘ እና የአንገት ህመሙ
ከቆየብዎ የሚከተሉት ነገሮች ሊረዱ ይችላሉ።
- ቀላል እንቅስቃሴ ማድረግ
- ተክለሰውነትን ማስተካከል
- ቀስ እያሉ መንጠራራት
- አንገት ማሳጅ ማድረግ
- ህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች መውሰድ
# የአንገት ህመም እና ጡንቻ መሳሳብ
የአንገት መዞር ወይም መጣመም አንገት ላይ
የጡንቻ መሳሳብ ያመጣ። ይህም ቢሆን የህመሙ
መንስኤ የአንገት መዞር መሆኑ ከተረጋገጠ በህመም ማስታገሻ መድሃኒት እና ከላይ በተዘረዝሩት የቤት ውስጥ ማስታገሻዎች ህመሙን
መከታተል በቂ ነው።
የዞረ አንገት የሚያመጣው ህመም ከተወሰኑ ቀናት
አያልፍም። አንገት በሙሉ አቅሙ ወደ ቀኝ እና ግራ መታጠፍ ስለማይችል በዚህ ግዜ መኪና መንዳት አይመከርም።
ከመደንዘዝ እና ድካም ስሜት ጋር የመጣ የአንገት
ህመም አንገትን በግማሽ ከፍሎ የሚሰማ ህመም አልፎም ትከሻ እና እጅ ላይ አብሮ የሚሰማ ህመም
መንስኤው የተቆነጠጠ ነርቭ ወይንም ራዲክሎፓቲ
ሊሆን ይችላል። አንገት ላይ
ያለው ቆዳ ስሜት ከተቀየረ ወይም የአንገት ጡንቻዎች ከደነዘዙ የዚህ ህመም ምልክቶች
ሊሆን ይችላል።
ነገር ግን እነዚህ ስሜቶች ታይተውም በሽታው
ራዲክሎፓቲ ሳይሆን የሚገኝበት ሁኔታ አለ።
ዶክተር በማማከር የህመሙን ሁኔታ መረዳት
ተገቢ ነው።
# የአንገት ህመም መቼ ነው አሳሳቢ የሚሆነው?
አንገት ህመም የከባድ ህመም ውጤት የሆነበት
ግዜ አለ።
# ከባድ ህመም
የአንገት ህመም ከሚከተሉት ገጽታዎች ጋር አብሮ
ሲመጣ ለጤናችን አሳሳቢ ነው።
- ህመሙ ከፍተኛ ሲሆን
- ህመሙ ከሌሎች ስሜቶች ጋር አብሮ ሲታይ
- ለውጥ ሳያሳይ ለረጅም ግዜ ሲቆይ
ልብ ድካምን ጨምሮ ከፍተኛ የልብ ህመም አነገት
ህመም ያመጣል።
# ከአንገት ህመም ጋር የሚከተሉት ስሜቶች አብረው ከታዩ በአስቸኳይ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል።
- የደረት ህመም። ደረትን ጥብቅ የሚያደርግ ስሜት።
- ደረት ላይ ከፍተኛ የህመም ስሜት መተንፈስ መቸገር
- የልብ ህመም አልፎም እጅ፣ ትከሻ እና ደረት ላይ
ህመም ስሜት ይፈጥራል።
- ሰውነታችን ላይ የሚፈጠር ከባድ ኢንፌክሽን ሌላ
አንገት ህመም የሚያመጣ በሽታ ነው። ኢንፌክሽን
አስቸኳይ የህክምና ክትትል ያስፈልገዋል። እንደ
ሜኒንጃይተስ አይነት ከባድ ኢንፌክሽን
የሚከተሉትን የህመም ስሜቶች ያስከትላል።
ትኩሳት ከባድ የህመም ስሜት እና ድካም
አንገት ላይ ወይንም ሌላ ቦታ የሚፈጠር
ኢንፌክሽን የአንገት ህመም ሊፈጥር ይችላል።
በቅርብ ቀዶ ጥገና ያደረጉ ወይም ከቁስል
እያገገሙ ያሉ ሰዎች ኢንፌክሽን ሊፈጠርባቸው
ስለሚችል ክትትል ማድረግ አለባቸው።
# ከባድ ጉዳት
አንገታችን ላይ ከባድ ጉዳት ካጋጠመን ህክምና
ማድረግ ይኖርብናል። ህመም ባይሰማን እንኳ
መተው የለብንም። በተለይ የህመም ስሜት
ሳይኖር ግን ለመንቀሳቀስ እና ለመናገር መቸገር
አሳሳቢ ሁኔታ ስለሆነ ህክምና ማግኘት ተገቢ
ነው።
ስፖርት እንቅስቃሴ ላይ የሚፈጠር ግጭት እና
አዛውንቶች ሲወድቁ የሚፈጠር የአንገት ጉዳት
በተደጋጋሚ ይታያል። ሁኔታው ሲፈጠር የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ተገቢ ነው።
- አምቡላንስ እንዲመጣ መደወል
- አስቸኳይ ህክምና የሰለጠኑ ሰዎች ፈልጎ
- እርዳታ እንዲሰጡ ማድረግ
- የአስቸኳይ ግዜ ህክምና ስልጠና ከሌለዎ
ምንም አይነት እርዳታ ከመስጠት መቆጠብ
- አንገት እና ጭንቅላት ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርግ መጠበቅ
- ጉዳት ያስተናገደ ሰው ጭንቅላቱን ማንቀሳቀስ
ከቻለ እና አጥጋቢ ንግግር ማድረግ ከቻለ ጥሩ
ዜና ነው። ቢሆንም ግን ህክምና ማድረግ ተገቢ
ነው።
# ረጅም ግዜ የቆየ የአጥንት ችግር
አንዳንድ ሰዎች እንደ አርትራይተስ አይነት ረጅም
ግዜ የሚቆይ ህመም አለባቸው። ይህ ህመም
የአንገት ህመም ሊፈጥር ይችላል። ለዚህ ህመም
የዶክተር ክትትል ያስፈልጋል።

#እንዴት በቤት ውስጥ ማከም እንችላለን
፡-ሮማን የበሰለውን ውሃውን ፣የፅገሬዳ ቅጠል እና ዘቢብ ከአንድ የሻይ ማንኪያ ማር ጋር በመቀላቀል አፍልቶ በሻይ ስኒ በቀን አንድ መጠጣት ፡፡
፡-ጤናአዳም ፣ የንስላል ውሃ እና የስንዴ ዱቄት በአንድ ላይ በማፍላት በሻይ ብርጭቆ እንድ መጠጣት ፍቱን መድሃኒት ነው ፡፡

እናመሰግናለን

መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
• አድራሻ ፡-አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736