የፎረፎር በሽታ መንስኤውና መፍትሔዎቹ
Author: admin
Date: 2022-09-06
የፎረፎር በሽታ መንስኤውና መፍትሔዎቹ
🌿ከ ሀኪም አዳሙ🌿
፨ፎረፎር ማለት ከራስ ቅል ቆዳ ላይ እየተጋገረ አብዛኛውን ጊዜ ፀጉር በሚበጠርበትወቅት፣የጤፍ እብቅ መስሎ ስፍር ቁጥር የሌለው ብናኝ እየበነነ በፀጉሮች ላይ** ሰፍሮ ይታያል
ፎረፎር በማበጠሪያም ሆነ በልዩ ልዩ ነገሮች እየበነነ ከአንዱ ወደአንዱ የሚጋባና ጥንቃቄ ካልተደረገበት በቀላሉ የሚዛመት የበሽታ ዓይነት ነው ።
የፎሮፎር በሽታ መነሻ ምክንያቶች
1ኛየቆዳ ድርቀት
የቆዳ ድርቀት ብዙዉን ጊዜ ለፎረፎር መከሰት አይነተኛ ምክንያት ነዉ፡፡ ከደረቀ ቆዳዎ የሚራገፉ ነገሮች በጣም መጠኑ ትንንሽ የሆኑ ብናኝና ወዝነት የሌለዉ ሲሆን ምናልባትም ከራስ ቆዳዎ ዉጪ በሌላ የሰዉነት ክፍልዎ ላይ ድርቀት ሊታይ ይችላል፡፡
2ኛ ሴቦሪክ ደርማታይትስ (የተቆጣ፣ወዛማ ቆዳ)
ይህ ብዙዉን ጊዜ ለፎረፎር መከሰት ምክንያት ከሆኑት ዉስጥ አንዱ ሲሆን ዋና መለያዉ ቀይ፣ ወዛማ ቆዳ ሆኖ የተፈረፈረ ነጭ ወይም ቢጫማ ቅርፊት መሳይ ያለዉ የቆዳ መልክ ነዉ፡፡ ሴቦሪክ ደርማታይትስ ቅባትነት ያለዉ ፈሳሽ የሚያመነጩ ዕጢዎች( oil glands) በብዛት በሚገኙበት የራስ ቆዳን ጨምሮ እንደ ቅንድብ፣ የአፍንጫ ግራና ቀኝ፣ የጆሮ ግንድ፣ በጡት መካከል በደረት ላይ ባለዉ አጥንት ላይ፣ ብሽሽትና አንዳንዴ ብብት ስር በብዛት ይከሰታል፡፡
ብዙውን ጊዜፀጉርዎን ተከታታይነት ባለዉ መልኩ የማይታጠቡ ከሆነ የራስዎ ቆዳ የሞቱ ሴሎችና ወዝ በላይ በላዩ ስለሚደራረብ ለፎረፎር ሊያጋልጥዎ ይችላል፡፡
• ሌላ የቆዳ በሽታ ሲኖር፡-
ኤክዜማ ወይም ሶሪያሲስ የሚባሉትን የቆዳ ችግር ያለባቸዉ ሰዎች ፎረፎር ሊኖራቸዉ ይችላል፡፡
• ፈንገስ(ማላሴዚያ)፡-
ማላሴዚያ የሚባለዉ የፈንገስ አይነት በአብዛኛዉ ሰዎች የጭንቅላት ቆዳ ላይ የሚኖር ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ላይ የጭንቅላት ቆዳን የመቆጥቆጥ ባህሪይ አለዉ፡፡ ይህ ቆዳን የመቆጥቆጥ ባህሪይ ብዙ የቆዳ ሴሎች በጭንቅላት ቆዳ ላይ እንዲያድጉ ስለሚያደርግ እነዚህ በገፍ ያደጉት ሴሎች ሲሞቱ ነጭ፣ ወዛማ ነገር ሆነዉ በፀጉርና ትከሻዎ ላይ ይራገፋሉ፡፡
ኮንታክት ደርማታይትስ
አንዳንድ ለራስ ለፀጉር መዋቢያነት የሚጠቀሙባቸዉ ነገሮች ወይም ቀለሞች አንዳንድ በዉስጣቸዉ ያሉ የተሰሩባቸዉ/የተቀመሙባቸዉ ነገሮች (ለምሳሌ ፓራፌኒይልኢንዳሚን) በራስ ቆዳዎ ላይ የመቅላት፣ የማሳከክና መቀረፍ ባህሪይ እንዲኖረዉ ያደርጋል፡፡ በጣም በተደጋጋሚ መታጠብ ወይም የፀጉር ዉበት መጠበቂያ ዉጤቶችንም አብዝቶ መጠቀም የጭንቅላት ቆዳዎን በመቆጥቆጥ ለፎረፎር ሊያጋልጥዎ ይችላል፡፡
» ለዚሁ የፎረፎ በሽታ የሚረዱ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንቶች በምርምር ያገኟቸው ለመድኃኒትነት የሚሆኑ የዕፀዋት ዓይነቶች
1ኛ የግራምጣ ስር
2ኛ አደስ ከነቅጠሉ
3ኛ የወይራፍሬ
4ኛ የጌሾ ቅጠልና ፍሬ ዕነዚህን ዕፀዋቶች በአንድነት ወቅጦ አዋህዶ በቅቤ መቀባት ነው
ከ1----10--ቀን በቀን ሁለት ጊዜ ሽታ በሌለው ሳሙና ዕየታጠቡ ይቀቡት ፍቱን መድኃኒት ነው ።
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
• አድራሻ ፡-አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736