የላሽኝ በሽታ መፍትሔ
Author: admin
Date: 2022-08-31
የላሽኝ በሽታ መፍትሔ
🌿 ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌿
፨ላሽኝ ማለት ምንም ሳይታወቀን የራስ ፀጉራችንን የሚላጭ ክፉ የበሽታ ዓይነት ነው
በዚህ በሽታ ማንኛውም ግለሰብ እንደተያዘ
አልፎ አልፎ በራስ ቅሉ ላይ ብልጭ ብሎ ምልክቱ ይታያል።
»ሆኖም በሽታው እንደተከሰተ ሕክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው::
የላሽኝ በሽታ እና መፍትሔውን
»ላሽኝ የተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅማችን ፀጉር የሚሰሩ ሕዋሳትን በድንገት በማጥቃት የሚከት የበሽታ ዓይነት ነው፡፡
ጥቃቱ በምን ምክንያት እንደሚከሰት ሳይንስ እስካሁን ያልደረሰበት ቢሆንም በመላው ዓለም
በዚህ በሽታ በ10 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በበሽታው እንደተጠቁ ይገመታል ::
» ላሽኝ በአንድ በተወሰነ ቦታ ላይ የፀጉር መርገፍ ሲሆን ቦታው የራስ ቅል ፣ቅንድብ ፣የአይን ሽፋሽፍት ወይም ፂም ላይ ሊሆን ይችላል፡፡
አልፎ አልፎም በደረት በብብትና በብልት አካባቢ ያሉ ፀጉሮችን ሊያጠቃ ይችላል፡፡
» ላሽኝን በሚመለከት ዓለም አቅፍ እውነታዎችን
እንመልከት
1 ከሰው ወደ ሰው አይተላለፍም፡፡
2 በዘረ-መል(Genetically) ሊተላለፍ ይችላል
3 በተለይ የቁጥር አንድ ስኳር ያለባቸው ሰዎች
4 ሕመምተኞችና የአንጓ ብግነት ያለባቸው ሰዎች ለላሽ በሽታ ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡
5 አካባቢያዊ ተፅዕኖዎች አባባሽ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
6 አንዳንድ የላሽ አይነት ሙሉ በሙሉ የራስ ፀጉር መርገፍ ሊሆን ይችላል፡፡
የላሽኝ በሽታ መፍትሔ
ለዚሁ በሽታ መፍትሔ ይሆኑ ዘንድ ኢትዮጵያውያን መፍትሔዎችን ስንመለከት
» የዋጊኖስ ፍሬ
»የእንዳሁላ ሥር
»የእንቧጮ ሥር
» የምሥርች ስርና ቅጠል
»የእንስላል ሥር
አጠቃቀም
እነዚህን ዕፀዋቶች በአንድነት ወቅጦና ሰልቆ
ትንሽ ድኝ ጨምሮ በለጋ ቅቤ ለውሶ የተላጨውን የአካል ክፍል ክብ አድርጎ መቀባት ነው
ይህን ድርጊት ከ 7-12 ቀን ቢቀቡት ሙሉ በሙሉ እንደነበረው ይመለሳል።
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
• አድራሻ ፡-አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736