# ጡት # ላይ # የሚፈጠር # ውሃ # የቋጠረ # እባጭ
🌿 ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌿

# ይህ እባጭ በውስጡ ውሃ የቋጠረ ሲሆን በአብዛኛውን ካንሰርን የማያስከትል ነው ፡፡እባጩ አንድ ወይም ከአንድ በላይ ሊሆን ይችላል፡፡ በማንኛውም እድሜ የሚያጋጥም ቢሆንም ብዙ
ጊዜ ከ50 አመት በታች ያሉ ሴቶች ላይ ይስተዋል
በተጨማሪም ይህ ውሃ አዘል እባጭ በአንዱ ወይም በሁለቱም ጡት ላይ ሊፈጠር ይችላል፡፡

# ምልክቶቹ
»ለስለስ ያለ ክብ እባጭ መታየት
»ከጡት የሚወጣ ፈሳሽ ( ውሃ መሰል፣ ቢጫ ወይም ጥቁር ቡኒ መሰል)
»እባጩ ያለበት ቦታ ላይ መደደር/ህመም መሰማት

# መንስኤው
ትክክለኛ መንስኤው ይህ ነው ተብሎ
ባይረጋገጥም የወርሃዊ የሆርሞን ለውጥ አጋላጭ እንደሚሆን ባለሙያዎች
ይጠቅሳሉ ፡፡ በዚህም ምክንያት ጡት ላይ የሚገኙ እጢዎች ላይ ውሃ ይጠራቀማል፡፡ ይህም ለሁለት ይከፈላል ፡-

# ማይክሮሲስት ፡- አነስተኛ የሆነ ሲሆን ሊታይ የሚችለው በምስል ምርመራ ( ማሞግራፒ፣ አልትራ ሳውን በመሳሰሉት ..)

# ማክሮሲስት ፡- ይህ ደግሞ በመጠኑ ከፍ ያለ ሲሆን
መታየት የሚችል ነው በሴንቲ ሜትርም ከ2.5- 5 ይደርሳል ፡፡

# ህክምና
በመጠናቸው አነስተኛ የሆኑና ህመም ምልክት ያላሳዩ ህክምና አያስፈልጋቸውም አንዳንዴም በራሳቸው ይጠፋሉ ነገር ግን ክትትል ይፈልጋሉ
በስሪንጅ መጦ ማውጣት የሆርሞን ህክምና
ቀዶ ህክምና

# የቤት # ውስጥ # ማስታገሻ # መፍትሄዎች
ጡትን የሚደግፉ መያዣዎች ማድረግ
ህመም ሲኖር ሙቅ ውሃ መያዝ / በረዶ መያዝ
ቡና መጠጣትን መቀነስ የህመም ማስታገሻ መጠቀም ናቸው፡፡

መልካም ጤንነት!!
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736