የስጋ መጥበሻ (ሮዝመሪ
Author: admin
Date: 2022-05-23
የስጋ መጥበሻ (ሮዝመሪ)
🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
፨የስጋ መጥበሻ በእንግሊዝኛው አጠራር ሮዝመሪ ሲባል የሳይንሣዊ መጠሪያ ሰሙ ደግሞ (Rosemrainus officinalis L.) ነው፡፡ ሮዝመሪ በሀገራችን ማህበረሰብ ዘንድ የጥብስ ቅጠል ወይም አዝመሪኖ በመባል በስፋት ይታወቃል፡፡ ሮዝመሪ በዕድገት ባህሪው ከቁጥቋጦ ሰብሎች ውስጥ የሚመደብ ሲሆን በዕድገት ዘመኑ ቋሚ ሰብል በመሆኑ በአግባቡ ከተያዘ ምርታማ በመሆን ከ4 እስከ 7 ዓመታት ሊቆይ ይችላል፡፡ የሮዝመሪ ተክል በተፈጥሮው እጅግ የሚማርክ ውበት እንዲሁም ጥሩ መዓዛ ስላለው ከግቢ ማስዋቢያነት እንዲሁም በዕፅዋት መትከያ ዕቃዎች ላይ ተተክሎ እንደ ገና ዛፍም ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡ ከግቢ ውበት ማስጌጫነት በተጨማሪ የሮዝመሪ ርጥብ እና ደረቅ ቅጠሉ እንዲሁም የተነጠረው የመዓዛማ ዘይቱ በርካታ ጥቅሞች አለት፡፡ የሮዝመሪ ርጥብ ቅጠል ለዓሳ እና ለስጋ መጥበሻነት፣ ለሾርባና ለቲማቲም ስልስ ማጣፈጫነት፣ የተለያዩ ምግቦችን ለማጣፈጫነት እና ለሌሎች ተመሳሳይ ነገሮች መስሪያነት ያገለግላል፡፡ የሮዝመሪ ደረቅ ቅጠሉ ከላይ ለተጠቀሱት ግልጋሎቶች ከመዋሉም በላይ ለተለያዩ የባልትና ማዘጋጃነት (ለሽሮ፣ ለበርበሬ ወዘተ.) እንደ ግብዓትነት ያገለግላል፡፡ ከቅጠሉ የሚገኘው የማዓዛማ ዘይት ደግሞ ለተለያዩ ኢንደስትሪዎች ግብዓትነት ያገለግላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ለሥጋ እና ሌሎች ምግቦች ማቀነባበሪያነት፣ የፀጉር ዕድገትን የማፊጠን ባህሪ ስላለው የፀጉር ቅባቶች ማቀነባበሪያነት፣ ያለዕድሜ የመመለጥ ችግርን ለመለኪያነት፣ ለመታሻ የሚውል የማሳጅ ዘይትና ኦይንትመንት መስሪያነት፣ ድብርት እና የመጫጫን ስሜትን ለመቀነስ ወይም ለማስለቀቅ፣ መልካም ያልሆኑ ጠረኖችን ለማስወገጃነት፣ ለመዋቢያ አገልግሎት የሚውል ሽቶዎችን እና ሣሙናዎችን ለማምረት በግብዓትነት ያገለግላል፡፡ ፀረ-ደቂቅ ህዋስ እና ተባይ የማባረር ባህሪ ሰላለው ተፈጥሯዊ (ኦርጋኒክ) ይዘት ያላቸው ፀረ-ተህዋስያን እና ፀረ- ተባይ ኬሚካሎችን ለመስራትም ጭምር እንደ ግብዓትነት ያገለግላል፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736