አማራንተስ
🍀ከሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
፨አማራንተስ ፦ብዙ አይነት ዝርያ አለው በስፋት ጥቅም ላይ የዋለው በመገኛ ሀገሩ ሜክሲኮ ሲሆን በእኛ ሀገር ከትናንሽ አራም እስከ ትላልቁ ዘር ለምግብነት እስከሚውል ድረስ በመላው የሀገሪቱ አካባቢ ይገኛል ።

፨ሀገር በቀል የሆኑት በብዙ የሰሜን አካባቢዎች አሉማ በመባል በአረምነታቸው ይታወቃሉ ። አንዳንድ ቦታ ቅጠሉ ተቀቅሎ እንደ ጎመን ይበላል ነገር ግን አማልተስ እጅግ ምርታማ ሆኖ ከወይናደጋ እስከ ደጋማ ቦታ በቂ እርጥበት ካገኘ መብቀል የሚችል ብዙ አይነት አለ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ አንዳንድ ቦታ ሀምበር ጤፍ በመባል ይጠራል ።

፨በኮንሶ እና ኢሉአባቦር በሌሎች ዳርቻዎች ይዘሩታል ቅጠሉም ጥሩ ምግብ ነዉ። ከየካቲት እስከ ሚያዚያ ወይንም በቂ እርጥበት እንደተገኘ መዝራት ይቻላል። ለመድረስ ከ 7 እስከ 10 ወራት ይፈጃል እስከዚያ ቅጠሉን እንደጎመን ተቀቅሎ ይበላል በጣም እረዣዥም ቀያይ አናቶቹ አንገታቸዉን ወደ መሬት አቀርቅረው ለብዙ ወራት ስለሚቆዩ ለጊቢ ውበት ይሰጣሉ አማራንተስ ፍሬውም ሆነ ቅጠሉ ለብዙ ህመም መድሀኒት ከመሆኑም በላይ ምርታማ ስለሆነ እንደሰብል ቢዘራ ውጤቱ አመርቂ ይሆናል ዘሩ ከጤፍ ወይም ከስንዴ ጋር ተቀይጦ ተፈጭቶ በማንኛውም መልኩ በተለያየ ሁኔታ ተዘጋጅቶ ለምግብነት ሊዉል ይችላል። ዘሩ ተቆልቶ ተፈጭቶ ከተፈላ በሆላ ከማር ወይም ከለጋ ቂቤ ጋር ሲበላ ለተቅማት፣ ለአምቤባ ፣ለጃርዲያ እና ለመሰል ህመም ይጠጣል ቅጠሉም ቀቅለዉ ሲበሉት ለልብ ድካም እና ለጉበት ህመም ይሆናል በእንጀራ ወይም በዳቦ እህል ውስጥ ጨምረው ቢያስፈጩት ምግቡ ያማረ ይሆናል።

ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ

አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736