ደም ማነስ (Anemia) ምንድን ነው?

🍀ከሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀

- "ደም ማነስ" የምንለው ችላ መባል
የሌለበት ፣ አደገኛ ፣በደም ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ሴሎች ቁጥር መሆን ከሚገባው በታች ሲያንስ ወይም በቀይ የደም ሴል ውስጥ የሚገኘው የ ሄሞግሎቢን የተባለው የደም ፒግመንት ከመጠን በላይ ማነስ ነው።

-ሄሞግሎቢን የምንለው በደም ሴል ውስጥ የሚገኝ ብረትን (iron) የያዘ እና ኦክሰጅን ከአንዱ የደም ክፍል ወደ ሌላው የሰውነታችን ክፍል ተሸክሞ የሚያጓጉዝ ነው። ስለዚህ የሄሞግሎቢን እጥረት ሲኖር የሰውነት አካሎቻችን በትክክል ለመስራት የሚፈልጉትን ያህል ኦክስጅን ስለማያገኙ ነው።

ማንን ያጠቃል?
- ለአቅመ ሄዋን የደረሱ ሴቶችን በተለይም በብረት እጥረት ምክንያት (iron deficiency) የምንለው አይነት የደም ማነስ በተለየ ሁኔታ የተጋለጡ ናቸው።

ይህም የሚሆነው በወር አበባ ጊዜ የደም መፍሰስ ስለሚኖር እና በእርግዝና ጊዜ ደግሞ የደም ፍላጎት ስለሚጨመር ነው። ለዚህም ነው እናቶች በእረግዝና ክትትል ወቅት የብረት (iron) እንክብል የሚሰጠው።

ምክንያቱም አንድ ነፍሰጡር እናት ለከፍተኛ የደም ማነስ ከተጋለጠች ፅንሱ የሰውነት መቀጨጭ እና ያለ ጊዜ መወለድ ሊከሰት ይችላል።ከዚህም በተጨማሪ ህፃኑ ከተወለደ በዃላም ለደም ማነስ ተጋላጭ ይሆናል።

-እንደ WHO ከሆነ በአለም ላይ 45% የሚሆኑ እድሚያቸው ከአምስት አመት በታች ያሉ ህጻናት እንዲሁም 40% የሚሆኑ ነፍሰጡር እናቶች ለደም ማነስ ተጋላጭ ናቸው።

-ከባድ በሽታ ያላቸው እና እድሜያቸው የገፋ ሰዎችም ተጋላጭ ናቸው።

መንስኤዎቹስ?
-ከ400 በላይ የደም ማነስ አይነቶች ሲኖሩ መንሰኤዎቹን በ3 ከፍለን ማየት እንችላለን።

1.የቀይ የደም ሴሎች ምርት መቀነስ (decreased RBC production) በተለያዩ ምክንያቶች ለምሳሌ በብረት እጥረት ምክንያት (iron deficiency) ፣ ቫይታሚን ቢ12 እና ፎሌት እጥረት ፣ የኩላሊት ችግር ፣ ካንሰር

2.የቀይ የደም ሴሎች ውድመት (increased RBC destruction)

3.በደም መፍሰስ (blood loss)

አይነቶቹስ?
-ጥቂቶቹን ለማየት ያክል
1. በብረት ምክንያት የሚመጣ (iron deficiency) ይህም በአመጋገብ ችግር ፣ በከፍተኛ የደም መፍሰስ ፣ ሲኖር ባልተለመደ ሁኔታ ወረቀት ፣ ቆሻሻ ለመመገብ መፈለግ ፣ የጥፍሮቻችን መሰባበር፣የአፍ መሰነጣጠቅ እና መቁሰል ሊኖር መፍሰስ ።

2. በቫይታሚን ቢ-12 ምክንያት የሚከሰት የደም ማነስ በእጅ እና እግር ላይ መርፌ የመወጋት እና የመጠዝጠዝ ስሜት ፣ የምላስ ህመም ስሜት መኖር ፣ የመዳሰስ ስሜት ማጣት ፣ መነቀጥቀጥ፣ ለመራመድ መቸገር ፣የአስተሳሰብ መለዋወጥ ይኖራል

3.በሊድ መመረዝ የሚከሰት የደም ማነስ ሲኖር ሰማያዊ ወይም ጥቁር መስመር በድድ ላይ መኖር፣ የሆድ ህመም ፣ ድርቀት አና ማሰታወክ ሊኖር ይችላል

4.ሲክል ሴል (sickle cell anemia) የድካም ስሜት ፣ ለኢንፌክሽን መጋለጥ ፣ በህፃናት ላይ እድገት መዘግየት፣

5. ሄሞላይቲክ (hemolytic anemia) ሲኖር የሽንት መጥቆር ፣ የአይን ቢጫ መሆን ፣ የጣፊያ እና የጉበት እብጠት

እንዴት ማወቅ ይቻላል?
- የደም ምርመራ በማድረግ የደም ሃሞግሎቢን መጠን እና የተለያዩ ከደም ላይ የሚሰሩ ምርመራዎች ለምሳሌ peripheral morphology, reticulocyte index ፣ የደም ብረት መጠን እና የመሳሰሉትን እንዳስፈላጊነቱ በማድረግ ማወቅ ይቻላል።

ምልክቶቹስ?
-እንደ የደም ማነስ አይነቶች የሚለያይ ሲሆን የጋራ የሆኑ ምልክቶች የምንላቸው
*የድካም ስሜት
*በእቅስቃሴ ጊዜ ያልተለመደ ፈጣን የልብ ምት
*እራስ ምታት
*የማዞር ስሜት
*ትኩረት ማጣት
*የቆዳ መገረጣት
*ትንፋሽ ማጠር
*ጆሮ ላይ የመጮህ ስሜት
*የምግብ ፍላጎት መቀነስ

ህክምናውስ?
-እንደ ደም ማነስ አይነት የሚወሰን ሲሆን በተለይ የደም ማነሱን ያመጣውን ችግር ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ማወቅ እና ማከም ተገቢ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አመጋገብ ላይ ትኩረት በማድረግ በብረት የበለፀጉ ምግቦች ለምሳሌ ቀይ ስጋ ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ለምሳሌ ካሮት ፣ አቮካዶ ፣ ጉበት ፣ አሳ ፣ የጥራጥሬ እህሎች ፣ ባቄላ ፣ አተር እና የመሳሰሉትን መመገብ አንዱ የህክምና አካል ነው።

-በብረት እጥረት ምክንያት ከሆነ በአመጋገብ ስርአት ድክመት ፣ በደም መፍሰስ ፣ የአንጀት ቁስለት ፣ ሁክ ዎርም ፣ የጨጓራ መድማት ፣ የአንጀት እና የጨጓራ ካንሰር ፣ የወር አበባ በብዛት የደም መፍሰስ ሊከሰት ስለሚችል የደም ማነሱን ያመጣውን በሽታ ማከም ይጠበቅብናል።

-በቫይታሚን ቢ12 እጥረት የሚከሰት ከሆነ በትንሹ አንጀት እና በጨጓራ ችግር እንዲሁም አትክልት ብቻ ተመጋቢዎች ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ። ቫይታሚን ያላቸው ምግቦች ወይም ቫይታሚን ቢ 12 ረዘም ላለ ጊዜ መውሰድ ሊጠበቅብን ይችላል።

ሌላው ፎሌት እጥረት (folate deficiency) ሲኖር ደካማ የአመጋገብ ስነ ሰርአት ፣ መጠጥ በብዛት መጠጣት ፣ የሚጥል በሽታ መድሀኒቶች የሚወስዱ ሰዎች ተጋላጭ ሊሆኑ ስለሚችሉ folic acid እንክብል ሀኪም ሊያዝልን ይችላል።

በቫይታሚን ቢ12 እና በፎሌት እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ አይነት እንለዋለን።

-ከዚህ በተጨማሪ የደም ልገሳ እና የአጥንት መቅኔ ንቅለ ተከላ ፣ ጣፊያችን በቀዶ ጥገና ማሰወገድ ፣ የደም ማጣራት ህክምና ፣ እንዲሁም ቀይ የደም ሰህዋሰ እንዲመረት ሚያደረግ ሆርሞን ህክምና ሊያስፈልግ ይችላል።

N.B.ከፍተኛ የሆነ የደም ማነስ ሲኖር ተገቢውን ህክምና ካልወሰድን ለልብ ችግር ፣ ኢንፌክሽን ፣ የእድገት ችግር እንዲሁም ለሞት ሊዳርግ ይችላል።

መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ

አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736