የስኳር ህመም መቆጣጠሪያ ዘዴዎች!!

የስኳር ህመምን ለመቆጣጠር የሚረዱ የተለያዩ መንገዶች አሉ፡-

የሰውነት እንቅስቃሴ

🔹ከስኳር ህመም መቆጣጠሪያ መንገዶች መካል የሰውነት እንቅስቃሴ ዋነኛው ነው፡፡ በሰውነታችን የሚገኘውን የስኳር መጠን ዝቅ በማድረግ የህክምና ጊዜያችንን ይቆጥብልናል፡፡ በተጨማሪም ክብደታችንን እንዲቀንስ ይረዳናል፣ በሰውነታችን የሚገኘው ኢንሱሊን በተሻለ እንዲሠራ ይረዳናል፣ ለጥሩ የልብ ምት እና የደም ዝውውር ይረዳል፡፡
ማንኛውንም እንቅስቃሴ ከመሥራታችን በፊት የጤና ባለሙያ ጋር መመካከር ያስፈልጋል” ፡፡ ለስኳር ህመም ላለባቸው ሰዎች ከሚመከሩ የሰውነት እንቅስቃሴዎች መካከል : - የእግር ጉዞ /በተቻለን መጠም በሳምንት ለ3 ጊዜ በቀን ከ20-30 ደቂቃ/ መጓዝ፡፡ በጉዞ ወቅት የጥጥ ካልሲዎችና ለእግር ጉዞ የተስማሙ ጫማዎችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ከእግር ጉዞ በተጨማሪ ዋና፣ ዳንስ፣ መረብ ኳስ ፣ ቅርጫት ኳስ የመሣሠሉት የሰውነት እንቅስቃሴዎች ጠቃሚነታቸው የጎላ ነው፡፡

ጤናማ አመጋገብ

🔹የሰውነት ክብደት መጨመር፣ የስኳር ህመምን እንዳንቆጣጠር እንቅፋት ስለሚሆን ጤናማ የአመጋገብ ስልት መከተል ያስፈልጋል፡፡ ቅባትና ስኳር ከመጠቀም መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ በአጠቃላይ

🔹በእያንዳንዱ የምግብ ክፍለ ጊዜ ኃይል ሰጪ ምግቦችን መመገብ፡፡

🔹አትክልት በብዛት ይመገቡ፤

🔹የሚመገቡትን የቅባት መጠን ይቀንሱ( የማይረጉ ቅባቶችን ለምሳሌ የሱፍ፣ የኑግና የወይራ ዘይት ወዘተ ይጠቀሙ፡፡ ቅቤና ክሬሞችን አይጠቀሙ፡፡


ሲጋራ አለማጨስ

🔹ሲጋራ የሚያጨሱ የስኳር ታማሚዎች በይበልጥ እድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ አጫሾች ለከፍተኛ ደም ግፊትና የሰውነት ቅባት/ኮሌስትሮል/ መጨመር በከፍተኛ የተጋለጡ ናቸው፡፡ ሲጋራ ማጨስም ለተለያዩ ሕመሞች፣ አልሰር፣ ጋንግሪንና እግር መቆረጥ አደጋ አሳልፎ ይሰጣል፡፡

የደም ግፊት መጠንን መቆጣጠር
የደም ግፊት መጨመር ለከፍተኛ ችግርና ስትሮክ ስለሚዳርገን ሁልጊዜ በመለካት የደም ግፊት መጠን መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

🔹በምግብ ውስጥ የጨው መጠንን መቀነስ፣
🔹የታዘዘን መድኃኒት በአግባቡ መውሰድ

🔹የስኳር እና የደም ግፊት መጠንነ በየጊዜው መለካት አስፈላጊ ናቸው፡፡

በሀኪም የታዘዙትን መድኃኒቶችን በአግባቡና ሳያቋርጡ መውሰድ መወጋትና ማስቀመጥ፥ ኢንሱሊን ከታዘዘለን በየቀኑ የምንወጋበት ሥፍራ ቦታ በመቀያየር /ተመሣሣይ ቦታ ከሆነ ስለሚደድርና ኢንሱሊኑ እንዳይሰራ ስለሚያደርግ/ እና በተገቢው ቦታ በማስቀመጥ፤ በአፍ የሚሰዱ መድኃኒቶች ከታዘዘሉን ደግሞ የጤና ባለሞያ በሚነግረን መሠረት መውሰድ እና ማስቀመጥ ተገቢ ነው፡፡

ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736