የስንፈተወሲብ ችግር መፍትሔ
Author: admin
Date: 2021-12-22
የስንፈተወሲብ ችግር መፍትሔ
🍀ከሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
፨አብዛኛወች ወንዶች ጠዋት ላይ ብልት አለመቆምን ማስተዋል፣ ብልትን ለማቆም መቸገር ወይም የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ በሚያስችል መልኩ መቆም አለመቻል፣ ወይም የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ አይነት ችግሮችን ያስተውላሉ። እነዚህ የስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ወንዶች ያማረ የወደፊት ህይወት እንዳይኖራቸው እንደሚያደርግ አመላካች ነው።
የስንፈተ ወሲብ ችግር
፨እድሜያቸው ከ20-30 ከሚሆኑት ወንዶች ውስጥ 8% የሚሆኑትን እንደሚያጠቃና እድሜያቸው ከ70-75 ከሆኑት ላይ ደግሞ ወደ 37% ከፍ እንደሚል ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ ስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) በአሁኑ ሰአት በደንብ የሚታወቅና የተለያዩ የህክምና አማራጮችም ያሉት ችግር ነው።
ስንፈተ ወሲብ በምን ይመጣል?
1. የእድሜ መግፋት
2. ዝቅተኛ ቴስቴስትሮን
3. ጭንቀት፣ ፍርሃት ወይም ድብርት
4. በቂ እንቅልፍ አለማግኘት
5. ሲጋራ ማጨስና አልኮል መጠጥ
6. ሌሎች የጤና ችግሮች በተለይ የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ ኮሌስትሮል
ስንፈተ ወሲብን እንዴት ማከም ይቻላል?
፨ የስንፈተ ወሲብ ህክምና እንደ ችግሩ መንስዔ እና እንደችግሩ ክብደት ይለያያል። የህክምና አማራጮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
» የመድሃኒት ህክምና፡ መድሃኒቶች የደም ፍሰትን ይጨምራሉ እንዲሁም የፆታዊ ፍላጎት በሚኖርበት ጊዜ ብልት በምላሹ እንዲቆም የሚያደርጉ ናቸው። አብዛኛዎች የስንፈተ ወሲብ መድሃኒቶች ስራቸውን ለመጀመር 30 ደቂቃ አካባቢ ይወስድባቸዋል። ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችም ራስ ምታት፣ አፍንጫችን ድፍን የማድረግ፣ የቆዳ መቅላት፣ የእይታ መቀየር ወዘተ ሊኖሩ ይችላሉ።
ኤክስትራፖሬሽን ሾክዌቭ ህክምና
፨ ይህ ህክምና ለስንፈተ ወሲብ አዲስ የህክምና አማራጭ ነው። ይህ የህክምና ዘዴ ታካሚው ብልቱን በበቂ ሁኔታና በራሱ ሰዓት መቆም እንዲችል ያደርገዋል። የሾክዌቭ ህክምና ሂደት የደም ዝውውርን በመጨመርና የደም ስሮች በአዲስ መልኩ ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ በማነቃቃት የተሻለ የደም ፍሰት እንዲኖር ያደርጋል ይሄም የፆታዊ ግንኙነት አቅም እንዲመለስ እንዲሁም እንዲሻሻል ያግዛል።
ቴስቴስትሮንን የመተካት ህክምና
፨ ዝቅተኛ የቴስቴስትሮን መጠን ያላቸው ወንዶች ቴስቴስትሮን የመተካት ህክምና በማግኘት ወንዶች የተሻለ ፆታዊ መነሳሳት እንዲኖራቸው ማድረግ ይቻላል። የሆርሞን ህክምና አብዛኛውን ጊዜ ዳሌ አካባቢ በመርፌ መልኩ ይሰጣል። ቴስቴስትሮንን ለመተካት ከሚደረጉ ህክምናዎች በብዛት የተለመዱት የቴስቴስትሮን አይነቶች ‘Cypionate’ እና ‘Enanthate’ ናቸው። ቴስቴስትሮን cypionate የተባለው መድሃኒት ግማሽ ላይፉ (half-life) 2 ሳምንት ሲሆን በአንፃሩ ቴስቴስትሮን enanthate የሚባለው ከ10-12 ሳምንት half-life አለው። ሌላኛው ቴስቴስትሮን የሚተካ መድሃኒት አወሳሰድ መንገድ በሚቀባና ቆዳን ሰርጎ መግባት በሚችል በቅባት መልኩ ነው። ይህም ሆርሞኑ በቆዳችን ሰርጎ ከገባ በኋላ በደማችን ውስጥ ስራውን ያከናውናል።
ባህላዊ ህክምና
»አበሱዳ
»ነጭሽንኩርት
»የጣዝማ ማር አድርጎ በወተት እያፈሉ መጠጣት ወይም የዘርጭእንቦይ ስር ፣ያለብላቢት ስር ወቅጦ በምስር ንፍሮ ውሀ ከወተት ጋር አፍልቶ መጠጣት ..ደጋግሞ ማድረግ ወይም አብላሊትዶግ የሴት ቀስት ችፍርግ ምስርእች እምቦጭ፣ጠሌንጅ ስራቸውን አድቅቆ በጠጅ መጠጣት።