የእንቅልፍ ማጣት ችግር
Author: admin
Date: 2021-09-26
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና:
የእንቅልፍ ማጣት ችግር
ሰወች ከተኙ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች በተደጋጋሚ ይነቃሉ ፣የየእለት ዉሎ፣አመጋገብ፣ጭንቀት እና መሰል ጉዳዮች ለዚህ ምክንያት ይሆናሉ ::
ባለሙያዎች ደግሞ ጥሩ እንቅልፍ እንዳይኖር የሚያደርጉ ምክንያቶችን ዘርዝረዋል::እነርሱም:-
1.የሰውነት ሙቀት:-በመኝታ ሰአት ሰውነት ከፍተኛ ሙቀት የሚያመነጭ ከሆነ በተደጋጋሚ ለመንቃት ይገደዳሉ::
2.የቀን ውሎ አጋጣሚዎች:-በቀን ውሎዎ የተከሰተ አሳሳቢ ክስተት ፣ያልታሰበ ክፍያ እና ተያያዥ ጉዳዮች ፣ከአእምሮ የማይጠፋ መጥፎ አጋጣሚዎችጭንቀትን በማስከተል በቂ እንቅልፍ እንዳይተኙ ያደርጎታል::
3.የአልኮል መጠጦች:-የአልኮል መጠጥ በፍጥነት እንቅልፍ እንዲተኙ ቢረዳዎትም ሌሊት ላይ እንቅልፍን በመረበሽ የቀን ውሎ እና ስራ ላይ ተፅእኖ ያደርጋል።
4.አነቃቂ ነገሮች፦ብናን ጨምሮ አነቃቂ መጠጦችን በእንቅልፍ ሰአት መዉሰድም ለእንቅልፍ እጦት ሌላኛው ምክንያት ነው::
5.አመጋገብ:-ከመኝታ በፊት የቅባት እና ካሎሪን መጠናቸው ከፍ ያሉ ከባድ ምግቦችን ያስወግድ
6.ጭንቀትና ድብርት:-አእምሮ እረፍት በመንሳት በቂና ጤናማ እንቅልፍ እንዳይኖር መንስኤ ይሆናል።
7:-የአካል ብቃት እንቅስቃሴ:-በመኝታ ሰአት አቅራቢያ የአካል ብቃት ማድረግን ባለሙያዎች አይፈቅድም::
8:-የስልክ አጠቃቀም:-በመኝታ ሰአት ሞባይል ስልኮችን መጠቀም ከእስክሪኑ የሚመጣውን ጨረር አእምሮ እንዲጨናነቅና እንዲነቃ ስለሚያደርገው ለእንቅልፍ እጦት ይዳርጋል።
9:-ረዘም ላለ ጊዜ የሚኖር የሸለብታ ጊዜ፦በስራ ሰአት ድካም ሲሰማ የተወሰነ ደቂቃ ሸለብታ መውሰድ ድካምን ለመቀነስ እጅጉኑ ይረዳል።ለበለጠ መረጃ
0941454593፣0989020202
http://www.hakimsolomon.com