ትንታ በምን ምክንያት ይከሰታል መፍትሄውስ
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ

ምግብ በሚዋጥበት ወይም ፈሳሽ በሚጠጣበት ጊዜ ጡንቻዎች ቧንቧ እፍያን(Epiglottis) ወደ ታች በማድረግ ምግብም ሆነ መጠጥ ወደ ሳንባ እንዳይገባ አቢይ የአየር ቧንቧን(Trachea/windpipe)ይዘጋል፤ ላንቃ(Soft palate) ደግሞ ወደ ላይ ከፍ በማለት ምግብና መጠጥ ወደ ሰርን(Nasal cavities) እንዳይገባ ያደርጋል፡፡
ትንታ የሚፈጠረው ምግብ ወይም መጠጥ በድንገት በአየር ቧንቧ(Trachea/windpipe) ወይም በሰርን(Nasal cavities) በኩል ብን ብሎ ሊገባ ሲሞክር ነው፤ የትንታው ሂደትም ሊገባ የሞከረው ነገር ተገፍትሮ እንዲወጣ የሚያደርግ ነው፡፡ ስንተነፍስ ቧንቧ እፍያ(Epiglottis) ወደ ላይ ከፍ በማለት አየር በአቢይ የአየር ቧንቧ(Trachea/windpipe) በኩል ወደ ሳንባ እንዲገባ ያደርጋል፡፡
#መከላከያ #መንገዶች
በትንሹ መጉረስ
ውሀን ቁጭብሎ መጠጣት
በሚያወሩበት ወቅት በዝግታ መዋጥ
#መንስኤው
ማንኛውም ቁስ የአየር ቧንቧ ላይ የሚያቆም ከሆነ
እየተመገቡ ማውራት
የአሲድ ወደ ኋላ /ገሮሮ መመለስ
ተኝቶ መመገብ
ጉሮሮ ላይ ቁስለት፣እባጭ እና ሌሎች ችግሮች ካሉ
የነርቨ ችግር ካለ
በከፍተና ሁኔታ አልኮል መጠቀም
የመተንፈሻ ክፍሎች ችግር እና አለርጂ ካለ
#መፍትሄ
ቀና ብሎ መተኛት
በጀርባ ከመተናት ይልቅ በግራ ጎን መተኛት
የአልኮል መጠጥን መቀነስ
ማኘክ የሚፈልጉ ምግቦችን አኝኮ መዋጥ
ምግብ እየበሉ ነው እንበል፣ ድንገት ትን ቢሎ አጠገቦ ማንም ሰው ባይኖር ምን ያደርጋሉ?
እኔስ ምን ላድርግ? አጠገባችን የሚረዳን ሰው በማይኖርበት ወቅት ማድረግ ያለብን ነገር
፡፡ ነገሩ ቀላል ነው,
እንደ ወንበር ዓይነት ጠርዝ ባለው የቤት ዕቃ ላይ ሆዳችንን( ከእንብርታችን ከፍ ብሎ ከደረት አጥንታችን ዝቅ ብሎ ካለው የሆድ ክፍላችን ላይ) አድርገን ወደ ታች ዘቅዘቅ እንላለን፡
ከዛም በኃይል ወደ ውስጥና ወደ ላይ በአንድ ጊዜ ሆዳችንን በወንበሩ ጠርዝ መጎሰም ወይም
መግፋት፡፡
ይህንን ጉሮሮአችን የዘጋው ነገር እስኪወጣ በተደጋጋሚ መፈጸም ይኖርብናል፡፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com