ጉድፍ ማለት ምን ማለት ነው?
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
ቫሬሴላ ዞስተር በተባለ ቫይረስ የሚመጣ በሽታ ሲሆን በተለይ በህጻናት ላይ በብዛት ይከሰታል፡፡ በዚህ ቫይረስ የተያዘ
ሰው በሚያስነጥስበትም ሆነ በንክኪ ቫይረሱን ለሌላ ሰው ካስተላለፈ በኋላ ቆዳ ላይ ቀያይ የሚያሳክኩ ብሎም ውሃ የሚቋጥሩ
እብጠቶች ይወጣሉ ፡፡
በሽታ የመከላከል ብቃታችን ሲጨምር ወይም ቫይረሱ በነጭ የደም ሴሎች ተሸንፎ እስኪወጣ ከ አንድ እስከ ሁለት ሳምንት ሊቆይ ይችላል፡፡
ጉድፍ ከፊት እስከ እግር የሚወጡ የሚያሳክኩ ቀያይ የቆዳ ላይ ሽፍታዎች የሚኖሩት ሲሆን እየቆየ ውሀ እየቋጠረና እየደረቀ ይሄዳል፡፡
አንድ በጉድፍ የተያዘ ሰው ሽፍታዎቹ ከመታየቱ ከ 1-2 ቀን በፊትና ከታየ ከ 1-2 ቀን ቫይረሱን ያስተላልፋል ፡፡
ክትባቱን የተከተበ እንዲሁም በቫይረሱ የተያዘ ህጻን አንዴ ከተያዘ በኋላ ሰውነቱ ቀድሞ የመከላከያ ንጥረ ነገር ስለሚያመርት በህይወት ዘመኑ ድጋሚ አያዝም ፡፡
ምልክቶቹ ፡-
ትኩሳት
የምግብ ፍላጎት መቀነስ
የድካም ስሜት መኖር
የሰውነት ሽፍታ
የመተላለፍያ መንገዶች
• በቆዳ ንክኪ
• በምራቅ ወይም በሰውነት ፈሳሽ
• ልብስ በመቀያየር ወይም ቀጥታ ከእብጠቱ ጋ በሚኖር ንክኪ
በጉድፍ የተያዘ ሰው ማድረግ ያለበት ጥንቃቄ
• በቆዳው ላይ እብጠቶቹ በሚወጡበት ሰዓት አለማከክ ወይም በጥፍር አለመነካካት ይህም በቆዳ ክፈተቶቹ በኩል
ባክቴሪያዎች እንዳይገቡና ኢንፌክሽኖች እንዳይፈጠሩ ይረዳል
• በቂ እረፍትና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ይኖርቦታል
• እስኪሻላቸው ድረስ ከሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ቀነስ አድርገው እረፍት እንዲወስዱ ማድረግ
በጤና ባለሙያ መታየት የሚያስፈልገው መቼ ነው ?
• ሽፍታዎቹ አይን ቁቦች ላይ መውጣት ከጀመሩ
• ልጅዎ ከ 1 አመት በታች ከሆነ
• ከ 38.9 ሴንቲግሬድ በላይ የሆነ ትኩሳት ካለ
• ከእብጠቱ የሚወጣው ፈሳሽ ወፍራምና ቢጫ እየሆነ ከመጣ
• ማስታወክ
• ለመተንፈስ መቸገርና
• የሆድ ቁርጠት እና ሳል እንዲሁም ከፍተኛ ህመም ካለ ቶሎ ወደ ህክምና ጣቢያ መሄድ ይኖርቦታል ፡፡
መልካም ጤንነት !!
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
Website: www.hakimsolomon.com
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
https://www.facebook.com
telgram- https://t.me/kidusmikaelhikmna
Email: info@hakimsolomon.com , solomon@hakimsolomon.com & support@hakimsolomon.com